======ቡኢ=====
የቀበሌው ማህበረሰብ ለረዥም ጊዜ ሲጠይቁት የነበረውን የመብራት ተጠቃሚነት ምላሽ ለመስጠት ከተማ አስተዳደሩ ልዩ ትኩረት በመስጠት ከ5.2 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ክፍያ መፈፀሙንና አስፈላጊውን የትራንስፎርመር አክሰሰሪዎች ወደ ከተማ ማስገባት እንደተጀመረ የገለፁት ከንቲባው በዛሬው ዕለትም የመጀመሪው ምዕራፍ የሆነው የኤሌክትሪክ መስመር መዘርጊያ ምሰሶ (ፖል) ለቀበሌው ማቅረብ መቻሉን ተናግረዋል።
አክለውም ከንቲባው ነጌሳ ቀበሌ ወደ ከተማ አስተዳደሩ ከተካለለ አጭር ጊዜ ቢሆንም ለቀበሌው የቅድሚያ ቅድሚያ በመስጠት በ40/60 የማህረሰብ ተሳትፎ ይሸፈን የነበረው ወጪ ሙሉ በሙሉ በከተማ አስተዳደሩ ወጪ በመሸፈን የኤሌትሪክ ሀይል ተጠቃሚ ለማድረግ በልዩ ትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝም ገልፀዋል ።
የተጀመረው ስራ ተጠናቆ ወደተሟላ አገልግሎት እስኪገባ ድረስ መላው የቀበሌው ማህበረሰብ አስፈላጊውን ሁሉ እገዛና ትብብር በማድረግና በትዕግስት እንዲጠብቁ ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ዘገባው የቡኢ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው ።
ለተጨማሪ መረጃዎች ገፆቻችን ይከታተሉይ