መንግስት የግብርናውን ዘርፍ ለማዘመን ባመቻቸው የአርሶ አደሮች የብድር አቅርቦት ተጠቃሚነትን በተመለከተ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለከተማው ጠቅላላ አመራርና የብድር ሞዳሊቲ ተጠቃሚ ለሚሆኑ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሄደ።

መንግስት የግብርናውን ዘርፍ ለማዘመን ባመቻቸው የአርሶ አደሮች የብድር አቅርቦት ተጠቃሚነትን በተመለከተ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለከተማው ጠቅላላ አመራርና የብድር ሞዳሊቲ ተጠቃሚ ለሚሆኑ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሄደ።

ጥር 15/2018 ዓ.ም

=====ቡኢ======

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አነስተኛ ማሳ ላላቸው አርሶ አደሮችና በግብርና ዘርፍ ለተሰማሩ አካላት ያዘጋጀውን የቡድር አገልግሎት በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሂዷል።

የቡኢ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ በለጠ ጫካ ከኢትዮጽያ ንግድ ባንክ የቡኢ ቅርፍ ስራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን ሞላ ጋር አንስተኛ ማሳ ላላቸው አርሶ አደሮችና በግብርና ዘርፍ ለተሰማሩ አካላት የብድር አገልግሎት ለማቅረብ የሚያስችል የግብ ስምምነት ተፈራርመዋል።

የብድር አቅርቦት መጀመሩ በግብርና ላይ ትልቅ ለውጥን የሚፈጥር መሆኑን አንስተው አርሶ አደሮች የዕድሉ ተጠቃሚ መሆን እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።

አክለውም ሀብት ሲሰራጭ ለአገልግሎት እንዲውል እንደመሆኑ መጠን በፍጥነት ወደ ተግባር ገብቶ በመስራት በተቀመጠለት ጊዜ ገደብ ውስጥ መመለስ ያስፈልጋል ብለዋል።

የቡኢ ከተማ አስተዳደር የብልፅግና ፅ/ት ቤት ኃላፊና ዋና የመንግስት ተጠሪ የሆኑት አቶ ደበበ አዳነ ገዢው መንግስት የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ለማሳደግ የግብርናው ዘርፍ ለማዘመን የተለያዩ ፖሊሲዎች ነድፎ እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

አክለውም ለዚህ ተጠቃሚ ለሚሆኑ አርሶ አደሮች የተቀመጡ የተለያዩ መስፈርቶች አሟልተው መገኘት እንዳለባቸው ለአብነትም የፋይዳ መታወቂያ እንደ ዋና መስፈርት በመሆኑ ሁሉም ፋይዳ መታወቂያ በማውጣትና ሌሎች ባንኩ የሚጠይቃቸውን መስፈርቶች በሟሟላት ተጠቃሚ መሆን እንደሚችሉ አመላክተዋል ።

የኢትዪጵያ ንግድ ባንክ ቡኢ ቅርንጫፍ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን ሞላ የፋይናንስ ማነቆን ለመፍታት የባንክ ብድር መመቻቸት መቻሉን በመግለፅ የብድር አማራጮችን እና ይዘታቸውን የሚገልጽ ሰነድ አቅርበዋል።

የብድሩ አላማም ሁሉንም ማህበረሰብ ያካተተ የፋይናንስ አገልግሎት ተደራሽ ማድረግ ፤ ዘላቂ የግብርና ምርታማነትን የሚያሳድጉ እና የአካባቢ ለምነትን የሚጠብቁ ዘላቂ ግብርናን የሚፈጥሩ ሁኔታዎች ለመደገፍ እንዲሁም የገጠር ማህበረሰብን የኢኮኖሚ አቅም በማጎልበት ሁለንተናዊ ብልፅግናን ማምጣት እንደሆነ ገልጸዋል ።

የግብርና ብድር አይነቶች ለተለያዩ ፍላጎቶች የተዘጋጀ የፋይናንስ መፍትሔዎች ያሉ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ ዋናዎቹ ተብለው የተቀመጡት የሰራ ማስኬጃ ብድር ፣ ፕሮጀክት ፋይናንሲንግ እና የማሽነሪ ብድር እንደሆኑ በሰነዱ ገልፀዋል ።

ስራ አስኪያጁ የብድር አመላለስ ጊዜን በተመለከተም እንደ ሽያጭ ሁኔታው በ3 ወር ፣ በ6 ወር ፣ በ9ወር እንዲሁም በ1 አመት በመዘጋጀቱ ተጠቃሚዎች ምቹ የሆነውን ጊዜ ከተቀመጡት አማራጮች በመምረጥ መወሰን እንደሚችሉ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቡኢ ቅርንጫፍ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ተሰማ አንድ አርሶ አደር ብድሩን ለማግኘት ምን መስፈርቶችን ማሟላት አለበት በሚል መነሻ ሀሳብ ሰፊ ማብራሪያ ሰተዋል።

ከእነርሱ ውስጥም በመንግሥት አካላት የሚቀርቡ የድጋፍ ደብዳቤ ፣ የብድር ማመልከቻ (ቅፅ) ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲም ነምበር/ ፣ ፋይዳ መታወቂያና ሌሎች ባንኩ የሚጠይቃቸውን መሰል መስፈርቶች ማሟላት እንደሚኖርባቸው ተናግረዋል።

ለመንግስት ሰራተኞች በ CBE Birr በኩል የብድር አገልግሎት በማመቻቸቱ CBE Birr በመክፈት የብድር አገልግሎቱን ለማግኘት ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነም አመላክተዋል።

ከዚህ ቀደም በተለያዩ አማራጮች በወለድ የብድር አገልግሎት ስንወስድ ነበር ያሉት የመድረኩ ተሳታፊዎች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሁን ያዘጋጀው የብድር አገልገሎት በዝቅተኛ የወለድ መጠን እንደመሆኑ ለተሻለ ስራ እንደሚጋብዛቸው ተናግረዋል።

ዘገባው የቡኢ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት

0 0 votes
የመረጃው አጥጋቢነት
0 አስተያየት መስጫ
ቆየት ያሉ
የቅርብ ጊዜ Most Voted
Inline Feedbacks
View all comments
0
Would love your thoughts, please comment.x
()
x