የቡኢ ከተማ አስተዳደር ግብርና ጽ/ቤት

gibrna_getachew (Small)

የተቋሙ ኃላፊ የአቶ ጌታቸው ፍቅሩ መልዕክት

የቡኢ ከተማ እና በዙሪያው ያሉ አካባቢዎች ከፍተኛ የሆነ የከተማ ግብርና ክምችት ያለው እንደመሆኑ መጠን ዘርፉን ውጤታማ የሚያደርጉ የተለያዩ ተግባራቶች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡ የተገኙ ወጤቶች ሲመዘኑ አርቢው አ/አደሩ ብሎም ከተማው በዘርፉ ማግኘት የሚገባውን ጠቀሜታ እያገኙ እንዳልሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

ስለዚህም እንደ ምክንያት የሚጠቀሱትእንደ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት የግብርና ምርት ምርታማነት  አናሳ መሆኑ ፤ የሰብልና የጓሮ አታክልት፤የሰብል ግብዓት አቅርቦት አናሳ መሆን ከእንስሳትና ዓሳ ሀብት አንፃር የመኖ ልማትና አጠቃቀም የእንስሳትን ምርታማነት ማሳደግ በሚቻል ዘመናዊ በሆነ መልክ ያለመጠቀም ፤የእንስሳት እርባታ ግብዓት አጠቃቀም አናሳነት፤የእንስሳት እርባታ የተሸሻሉ ቴክኖሎጂዎችን አሰራሮችን ያለመጠቀም፤ በእንስሳት ላይ የሚከሰቱ የተለያዩ ተዛማችና ወረርሽኝ በሽታዎች  መከላከያ ክትባትና ህክምና ተጠቃሚነት አናሳ መሆን እንዲሁም የእንስሳት እርባታ አዋጭነት ያለመገንዘብ ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

በተለዩ ችግሮች ላይ ትኩረት በማድረግ  ችግሮቹን መቀነስ የሚያስችል  ተግባሮችን በመፈፀም ህ/ሰቡን እንዲሁም ከተማውን ከዘርፉ ማግኘት የሚገባቸውን ጠቀሜታ ማግኘት እንዲችሉ በትጋት መስራት ይገባል፡፡ በ2016 ዓ.ም በጀት አመት አፈፃፀም  በከተማ ግብርና  በጓሮ አታክልት፤ በሰብል ጥበቃ፤ በወተት ምርት ማሻሻያ፤ በማር ምርት፤በስጋ ምርት ማሻሻያ፤በዶሮ እንቁላልና ስጋ ምርት ማሻሻያ፤በመኖ ልማት፤ በእንስሳት ጤና የሚከናወኑ እቅድ ለማሳካት የሚያስችሉ ግቦችን ከግምት ውስጥ በማስገባት እና በ2016 እቅድ ዓመት ክንውን የነበሩ ጥሩ ጎኖች በማጎልበትና ደካማ ጎኖችን ደግሞ በማረም በ2017 ዓ.ም እቅድ  የሚከናወኑ ዝርዘር ተግባራት የሚያመላክት እቅድ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

gibrna_getachew (Small)

የቡኢ ከተማ አስተዳደር ግብረና  ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌታቸው ፍቅሩ

ተልእኮ

የተሻሻሉ ቴክኖሎጂዎችን መሰረት ባደረገ መልኩ የህብረተሰቡን አቅም በስልጠናና በቴክኖሎጂ በማሳደግ እንዲሁም የማህበራትን ቁጥርና ጥራት በመጨመር ፣ በማጠናከርና በማስፋፋት የግብርና ምርት እና ምርታማነትን ማሳደግ

ራዕይ
የከተማው ህብረተሰብና ወደ ከተማው የተካለሉ አርሶ አደሮችን የግብርና ተግባራትን ተጠቅመው የምግብ ዋስትናውን የጠበቀና የገቢ ምንጩ ያደገ ሆኖ ማየት

እሴቶች

  1. አሳታፊነት
  2. ተጠያቂነት
  3. ፍትሐዊነት
  4. ቶሎ ምላሽ መስጠት
  5. የህግ የበላይነት ማክበር
  6. ግልፀኝነት
  7. ቀልጣፋነትና ውጤታማነት

ዓላማ

    • የከተማ ግብርና በሁለተኛው ትራንስፎርሜሽን የእቅድ ዘመን አገልግሎቱን በማሻሻል በሁሉም ዘርፍ የምግብ ዋስትና ማስጠበቅና በግብርናው ዘርፍ የኢኮኖሚ ምንጭ ማድረግ
    • ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ

የተቋሙ ተግባርና ሃላፊነት