የቡኢ ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ህፃናት ጽ/ቤት

setoch_hitsanat_simegn (Small)

የተቋሙ ኃላፊ የወ/ሮ ስመኝ ሻንቆ መልዕክት

ባለፉት አምስት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዓመታት በየዘርፉ ታቅደው ግቦቻቸውን ያልመቱ ተግባራት በዝርዝር ተገምግመው ጉድለቶችና ለመልካም ተሞክሮ የሚሆኑ ውጤቶች ተለይተው እና በ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም መነሻ በማድረግ በ2017 በጀት ዓመት የሚከናወኑ ተግባራት የተዘጋጁ ሲሆን ይህም የሁለተኛውን አምስት ዓመት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድን ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡ ይህም ዕቅድ በመንግሥት ቁርጠኝነትና የቅርብ አመራር ሰጭነት ፣ በባለሙያው ድጋፍና ክትትል እንዲሁም በህብረተሰባችን የተሟላ ተሳትፎና በቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት በየሥራ ዘርፉ የተገኙ ምርጥ ተሞክሮ በማስፋት ስትራቴጂ የሚፈጸም ሲሆን በመንደር ሆነ በከተማ ድህነትን ለማስወገድ በሚያስችል መልኩ የጋራ ርብርብ ይደረጋል ፡፡ ባለፉት ዓመታት ታቅደው ላልተከናወኑ ተግባራት በምክንያትነት የሚቀርቡ በርካታ ጉዳዩች ቢኖሩም በዋናነት የሚጠቀሱት የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባር፣የአስፈጻሚና የፈጻሚው አቅም ውስንነትና ቴክኖሎጂን በተሟላ ሁኔታ ያለመጠቀም ችግሮች በዋናነት የሚጠቀሱ ሲሆኑ በ2016 የበጀት ዓመት እነዚህን ችግሮች በሚቀርፍ አግባብ የመንግሥትና የህዝብ አቅም አቀናጅቶ በየደረጃው የለውጥ ሠራዊት በመገንባት ቀጣይ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ለማሳካት የሚያስችሉ ሥራዎች ትኩረት ተሰጥቷቸው ይከናወናሉ፡፡

በዚሁ መሠረት በሁሉም ሥራ ዘርፎች ዕቅዶች አተገባበር ላይ በየደረጃው ባለው አመራርና ፈጻሚ ድጋፋዊ ክትትል የሚደረግ ሆኖ በዋና ዋና የሥራ ዘርፎች ማለትም በሴቶች አቅም ማጎልበት በህጻናትና ትኩረት ተሰጥቷቸው ይከናወናሉ፡፡ ስለሆነም ከላይ በተጠቀሱትና በሌሎችም የሥራ ዘርፎች በ2017 በጀት ዓመት እንዲከናወኑ የታቀዱ ዋና ዋና ግቦች እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

setoch_hitsanat_simegn (Small)

የቡኢ ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ህፃናት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ስመኝ ሻንቆ

ተልእኮ

በከተማ አስተዳደር የሚገኙ ሴቶችና ህፃናት  ንቅናቄ በመፍጠር እንዲያደራጁ ምቹ ሁኔታዎችን በማመቻቸትና በማጠናከር፤ አቅማቸውን በማጎልበት ፤በሁሉም አካላት እቅድና ፕሮግራም ውስጥ ጉዳያቸው እንዲካተት በማድረግ ፤በመከታተልና በማስተባበር ፤የህፃናትን መብትና ደህንነት በማስጠበቅ በልማት ፤በሰላም በዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታና በመልካም አስተዳደር ጉዳዮች እኩል ተሳታፊና ተጠቃሚነታቸውን ማረጋገጥ፡፡

ራዕይ

ሴቶች በመልካም አስተዳደር የዲሞክራሲ ስርዓት ሰፍኖና በኢኮኖሚ እራሱን የቻለ ህብረተሰብ ና መካከለኛ ገቢ ያለው ለክልሉ ኢኮኖማዊና ማህበራዊ እድገት የበኩሉን አስተዋፆ የሚያደርግ ወጣት እውን ሆኖ

እሴቶች

  1. የሴቶችና ህፃናትን መብቶችን ለማስከበር በቁርጠኝነት እንሰራለን ፤እናስከብራለን፤
  2. የፆታ እኩልነትን ለማስፈፀም እንሰራለን፤
  3. በውጤት እናምናለን፤
  4. ግልፀኝነትን፤ ተጠያቂነትን ፍትሃዊነትን እናሰፍናለን፤
  5. ተሳታፊነትንና ቅንጅታዊ አሰራርን እናጠናክራለን፤
  6. ተገልጋዮችን ለማርካት እንሰራለን፤

የሴክተሩ የትኩረት አቀጣጫ

  • የሴክተሩን ተገልጋዮች፣ አመራሮች፣ ፈፃሚዎችና ባለድርሻ አካላትን አቅም በማጎልበት የመፈፀምና የማስፈፀም ብቃታቸውን ማሳደግ፣
  • ሶስቱን የልማት አቅሞች በመጠቀም፣ የተደራጅ የልማት ሰራዊት በመፍጠርና የለውጥ አስተሳሰብን በማጎልበት የሴክተሩን የልማት ግቦች ማከናወን፤
  • የከተማ ሥራ አጥ ሴቶች ዘመናዊ ቴክኖሎጂን እንዲጠቀሙ በማብቃት በተሰማሩበት የስራ መስኮች ምርትና ምርታማነትን እያሳደጉበከተማ የቴክኖኖሎጂ ሽግግር ማዕከል እንዲሆኑ ማድረግ፤
  • የከተማ ስራ አጥ ሴቶች በከተማ ግብርናና በ4ቱ ዘርፎች የሥራ ዕድሎች ራሳቸዉን እንዲችሉ፣ የኑሮ ደረጃቸውን ለማሻሻል ገበያ ተኮር በሆኑና  እሴት የሚጨምሩ ምርቶች ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እንዲሰማሩ ማስቻል፤

የተቋሙ ተግባርና ሃላፊነት