የቡኢ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት

የተቋሙ ኃላፊ የአቶ አርጋዬ ወልዴ መልዕክት

ትምህርት የልማትና የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ መሰረታዊ ግብዓት እንደመሆኑ በሃገር ደረጃ ፖሊሲና የሴክተር ልማት መረሀ ግብር ተቀርጾለት ክልላዊ ብሎም ዞናዊና ወረዳዊ በሆኑ ስትራቴጂክ እቅዶች እየተመራ ጥራቱ፣ ፍትሀዊነቱና ብቃቱ እንዲጠበቅና ምቅተ ዓመቱ እና የሁለተኛው እድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ግቦች ለማሳካት ሰፊ ርብርብ ሲደረግ ቆይቷል.፡፡ በመሆኑም ባለፉት አምስት አመታት በከተማችን በትምህርት ፍትሃዊ ተደራሽነት፣  የትምህርት ጥራትና የትምህርት ውስጣዊ ብቃትና ተገቢነት ለማረጋገጥ የተቀመጡ ግቦች ምን ያህል እንደተሳኩ ዝርዝር ግምገማ ተደርጓል፡፡ በመሆኑም በዕደረትና ትራንስፎረሜሽን ዕቅዳችን ላይ ብለን የጣልናቸው ግቦች በአብዛኛው ስኬታማ መሆናቸው ተገምግሟል፡፡

የ2017ዓ/ም የትምህርት ሴክተር እቅድ ከ2ኛው እድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ተመንዝሮ የተዘጋጀ ሲሆን 4 ዋና ዋና ክፍሎች ይዟል፡፡ ክፍል አንድ የነባራዊ ሁኔታዎች ግምገማ የትምህርት ልማት ሰራዊት አደረጃጀት ያለበት ደረጃና እና የ2ኛው ዓመት እድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ አፈጻጸም ግምገማ ይዟል፣ ክፍል ሁለት የተቋሙ አላማ፣ራዕይ፣ተልዕኮ፣የትኩረት አቅጣጫዎች፣ ማስፈጸሚያ ስልት (ስትራቴጂ) ዋናና ዝርዝር ግቦች እና ዝርዝር ተግባራትን ያካተተ ሲሆን ሶስት ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች አሉት፡፡ አንደኛው የትኩረት አቅጣጫ የትምህርት ጥራት ማረጋገጫ 50% ተሰጥቷል፣ 2ኛው የትኩረት አቅጣጫ የትምህርት ውስጣዊ ብቃትና ተገቢነት ማረጋገጥ 30% እንዲሁም ሶስተኛው የትኩረት አቅጣጫ የትምህርት ፍትሃዊ ተደራሽነት ሲሆን 20% ተሰጥቷል፡፡ በእያንዳንዱ የትኩረት አቅጣጫ ስር የተዘረዘሩት ግቦች በአራቱ እይታዎች የተከፋፈሉ ሲሆን ለተገልጋይ እረካታ 20% ለውስጥ አሰራር 50% ፣ ለፋይናንስ 15% እና ለመማርና እድገት 15% በመስጠት ተዘጋጅቷል፡፡

BUEE2966 (Small)

የቡኢ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አርጋዬ ወልዴ

ተልእኮ

ፍትሀዊ፤ አካታች እና ተደራሽ የሆነ ጥራቱና አግባብነቱ የተረጋገጠ በመልካም አስተዳደር ላይ የተገነባ የህይወት ዘመን ትምህርትና ስልጠና አካል የሆነ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ትምህርት ከቅድመ አንደኛ እስከ  ሁለተኛ ደረጃ ለዜጎች ማቅረብ!!

ራዕይ

በ2020 ዓ.ም በከተማው ፍትሀዊነቱና ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት በማድረስ በእውቀት፣ በክህሎትና በአመለካከት የተስተካከለና ለልማት፣ ለፍትህ፣ ለሠላምና ለዲሞክራሲ ግንባታ የላቀ ሚና የሚጫወትና በገበያ ላይ ብቁ ተወዳዳሪ የሆነ ትውልድ ተፈጥሮ ማየት፡፡

እሴቶች

  1. ሃገር ወዳድነት
  2. የባለቤትነት ስሜት
  3. ብቃትና ዉጤታማነት
  4. ፍትሃዊነት
  5. ግልጸኝነትና ተጠያቂነት
  6. የሃይማኖት እኩልነት
  7. የህዝብ ጥቅም ማስቀደም/ለህዝብ ጥቅም ቅድሚያ መስጠት
  8. መከባበር፣ሀቀኝነት፣መቻቻል
  9. ሁሌም ለትምህርት ጥራት፣ መስራት
  10. የላቀ ተሳትፎአዊነት
  11. በጋራመሥራት፣ /በአገራዊ ራዕይ ላይ መግባባትና ከዚያም በየተቋማቱ ራዕይና በሚተገበሩ ፖሊሲዎች፣ስትራቴጂዎችና ዕቅዶች ላይ የጋራ ስምምነት ላይ መድረስ
  12. ለለውጥዝግጁመሆን፣
  13. ለተገልጋይየላቀአክብሮትመስጠት፣
  14. በእውቀትናበእምነትመምራት፣
  15. ፈጠራናችግርፈቺነት አቅም ማጐልበት፣
  16. የሁሉም ዜጎች መብቶችና ጥቅሞች በእኩልነት የሚጠበቁበት የዲሞክራሲያዊ ስርዓት መገንባት፣
  17. ሠራተኞች በየሥራ ሂደቱ የተሠጠውን ዕቅድ መሬት የማስነካት ሚና እንዲጫወቱ እያንዳንዱ ሠራተኛ በቅንጅታዊ አሰራር ማስተሳሰር፡፡

ዓላማ

የትምህርት ጥራቱን፣ ሽፋኑን፣ ፍትሀዊነቱንና ብቃቱን ቀጣይነት ባለው መልኩ በማሻሻል በሁለንተናዊ ስብዕናው የታነጸው ትውልድ በመፍጠር ለከተማው ዘላቂ ልማት ተገቢውን አስተዋጽዖ ማድረግ ሲሆን ዝርዝር አላማዎቹ ፡-

  • በትምህርቱ ሴክተር ጠንካራ የትምህርት ልማት በመገንባት፣ በተደራጀ አኳኋን በመምራት፣ በማሰማራት እና በማንቀሳቀስ የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ፓኬጁን ሙሉ በሙሉ በመተግበር የተማሪዎች ውጤትና ስነምግባር እንዲሻሻል ማድረግ
  • የትምህርት ሽፋንና ተደራሽነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራትን ማከናወን
  • በየደረጃው የሚታየውን የአመለካከት፣ የክህሎትና የግብአት አቅርቦት ማለቆዎችን መፍታት
  • ሶስቱም የክትትልና ድጋፍ መስተጋብሮችን ወይም በሪፖርት፣ በአካል በመገኘትና ግብረ መልስ በመስጠት በመጠቀም ተከታታይነት ያለው የክትትልና ድጋፍ የግብረ መልስ ስርአት ተዘርግቶ ተግባራዊ በማድረግ ተቋማትን ማብቃትና በአፈጻጸም ማቀራረብ ናቸው

የተቋሙ ተግባርና ሃላፊነት

  • የማስፈጸሚያ ስልቶች/ስትራቴጂ/

ለትምህርት ዘመኑ ያስቀመጥናቸውን እቅዶች ስንፈጽም በዋናነት የሚከተሉትን ስልቶች/ስትራቴጂዎች/ እንከተላለን፡-

  • የተሟላ ቁመና ያለው የትምህርት ልማት ሰራዊት በሁሉም ትምህርት ተቋማት መገንባቱን ማረጋገጥና በተገቢው በመሰማራት
  • በየደረጃው የተጀመረውን የለወጥ ሰራዊት ግንባታ አጠናክሮ በማስቀጠል የተሟላ ቁመና እንዲኖራቸው ማብቃት
  • በከተማው ልዩ /ተጨማሪ ድጋፍ የሚፈልጉ ት/ቤቶች ለይቶ የማብቃት ስራ ይሰራል
  • ተጨማሪ ግብአት ማቅረብ፣ ተጨማሪ ት/ቤቶች መገንባት፣ ተጨማሪ ክፍሎች መገንባት ወዘተ
  • የት/ባለሙያዉና አመራሩ በየደረጃዉ የማብቃት ሚናቸዉን አንዲወጡ ማስቻል
  • የት/ት ስልጠና ጥራት ማስጠበቅ
  • እድሜያቸዉ ለትምህርት የደረሱ ህጻናት በፍታሀዊነት ወደ ትምህርት ገበታ እንዲገቡ ማስቻል
  • ተ.ተ.ተ የጎልማሶች ትምህርት እንዲተገበር ትኩረት አድርጎ መስራት
  • ምርጥ ተሞክሮ በመቀመር የ ማስፋት ስራ መስራት
  • የሴቶች ትምህርት ተሳትፎ ተወዳዳሪነት ማጎልበት
  • የትምህርት ቤቶች የሀብት አጠቃቀም ኢዲት ማድረግ
  • በሳይንስና ሂሳብ ትምህርቶች ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት
  • በሁሉም የትምህርት መስክ የሲፒዲና ኢንዳክሽን እንዲጠናከር ትኩረት አድርጎ መስራት

1.2 የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማረጋግጫ ፓኬጅ አፈጻጸም ያለበት ሁኔታ

1.2.1 የትምህርት አመራር፣ አሰራርና አደረጃጀት ማሻሻል መርሃ ግብር

በየደረጃው ያለው የትምህርት አመራር ለታችኛው አካል አቅም በመሆን እስከ ትምህርት ቤት ድረስ የዘለቀ ድጋፍ በመስጠት የመማር ማስተማሩን ሂደት  ማጎልበት ይጠይቃል፡፡ በዚህም መሰረት የትምህርት አመራር እስከ ትምህርት ቤት ድረስ የማጠናከርና የማሟላት ስራ ካለፉት ጊዜያት በተሻለ ሁኔታ መሰራቱ የሚያበረታታ ነው፡፡ አመራሩ ፓኬጁንና ሌሎች የትምህርት ዋና ዋና ጉዳዮችን አውቆ ማወቅ ያለባቸውን አካላትና ግለሰቦች አሳውቆ የማያቋረጥ፣ ተከታታይነት ፣ጥልቀትና ስፋት  ያለው ክትትል፣ ድጋፍና ግብረ መልስ በመስጠት በኩል አበረታች ስራዎች ተሰርተዋል፡፡ በተለይም በ2016ዓ/ም አካባቢዎችን(ተቋማትን) በውጤት ለማቀራረብ ተጨማሪ ድጋፍ የሚሹ ተቋማት (ት/በቶች) ተለይቶ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ የተሰራው ስራ ጥሩ ውጤት እያስገኘ በመሆኑ በ2017ዓ/ም ይህንኑ አጠናክረን የምንቀጥልበት ይሆናል፡፡ ከሌላው ጊዜ በተሻለ የራስን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበ እቅድ የማቀድ፣ የተለያዩ የሃብት ምንጮችን አሟጦ የእቅዱ አካል ማድረግ፣ ህብረተሰብን አሳምኖ ለትምህረቱ ስራ አቅም አድርጎ መጠቀም፣ አደረጃጀቶችን ማጠናከርና አቅም አድርጎ መጠቀም የሚጠቀሱ ጠንካራ ጎኖች ናቸው፡፡ የተዘረጉ አደረጃጀቶችና የአሰራር ስርዓቶችን በተጠናከረ ሁኔታ በዘላቂነት ሁሉም ከመጠቀም አንጻር አሁንም በተለይ ውጤትን ታሳቢ ያደረገ ደረጃ አዳዲስ ስልቶች (ምርጥ ተሞክሮዎች) አነፍንፎ የራስ እቅድ አድርጎ የመተግበር ውስንነት ፣በትንሽ ውጤት መርካት የመሳሰሉ ችግሮች ከከተማ እስከ ት/ቤት ባሉ አመራሮችና ፈጻሚዎች ይታያሉ፡፡ ስለዚ በቀጣዩ አመት እነዚህን ችግሮች የሚፈታ እቅድ አዘጋጅቶ መንቀሳቀስ ይገባል፡፡ ት/ቤቶች በኢንስፔክሽን እና በተለያዩድጋፍና ክትትል ወቅት በዝቅተኛ አፈጻጸም ደረጃ የተመደቡ ት/ቤቶች ለይቶ ተጨማሪ ሀብትና ድጋፍ አድርጎ ደረጃ የማሻሻል ሁኔታ ጉድለቶች ነበሩ፡፡

1.2.2 የትምህርት ቤት መሻሻል መርሀ ግብር

የዚህ መርሀ ግብር ዋና አላማ የተማሪዎችን ውጤትና ባህሪ ማሻሻል ነው፡፡ በዚህም መሰረት መርሀ ግብሩ የሚመራበት መመሪያና ማዕቀፍ እንዲሻሻል ተደርጓል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ት/ቤቶች የመማር ማስተማሩን ስራ እንዲያጎለብቱ የድጎማ በጀት /school grant/ እንዲመደብላቸው ተደርጓል የትምህረት ቤት ብሎክ ግራንት በጀትን በተመለከተ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሸለ መጥቶ አሁን አበረታች በሚባል ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡

በሌላ በኩል ት/ቤቶች አቅም በፈቀደ መጠን በስታንዳርዱ መሰረት ለመማር ማስተማር ስራ ምቹና ሳቢ ማድረግ አቅጣጫ የተቀመጠ በመሆኑ ት/ቤቶች ለህጻናት ምቹ የማድረግ ስራ እየተሰራ ቢሆንም አሁንም በስፋት መሰራት እንዳለበት ይታመናል፡፡ በብዙ ት/ቤቶቻችን በስታንዳርዱ መሰረት ሲታዩ በርካታ ጉድለቶች ያሉባቸው ሆነው ተገኝተዋል፡፡ የተማሪዎች ውጤት ሲታይ የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ማለፊያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች በ 2016ዓ/ም ወደ 28.6% ዝቅ ማለቱ፣በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት የደረጃውን ማጠናቀቂያ ፈተና ከወሰዱት ተማሪዎች ውስጥ 50% እና ከዛ በላይ ውጤት ያመጡት ሲታይ በ2016ዓ/ም ወደ 8.5% ከፍ ቢልም ከጊዜ ወደ ጊዜ ወጤቱ እየቀነሰ መምጣቱን ያመለክታል፡፡ በመሆኑ ይህንን ውጤት ለማሻሻል መምህራን፣ ተማሪዎች፣ ወላጆች፣ ር/መምህራን፣ ሌሎች ባለድርሻ አካላት የተማሪዎች ውጤትና ባህሪ በማሻሻል አተኩረው መስራት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ለዚህም በየደረጃው  ያለው አመራር ተገቢውን ግብዓት ማለትም መምህር፣ መጻህፍት፣ ፕላዝማ፣ ለቤተ ሙከራ ኬሚካልና አፓራተስ፣ የማጣቀሻ መጽሃፍት፣ የመጠጥ ውሃ፣ መጸዳጃ ቤት (ለወንዶችና ለሴቶች በመለየት)፣ ወዘተ ማሟላትና እንዲሁም ለተማሪዎች ውጤት መሻሻል በስራ መዋላቸውን በተለያዩ መንገዶች ማረጋገጥ ይገባዋል፡፡ ት/ቤቶቻችን ያሉበት ሁኔታና ደረጃ በተቀመጠው ስታንዳርድና በተዘጋጀው የት/ቤት ደረጃ ምደባ (ኢንስፔክሽን) መመሪያና ማኗል መሰረት መለየት እና ከስታንዳርዱ (ከደረጃ 3 በላይ) የሆኑትን የከላስተር ማዕከላት እንዲሆኑና ሌሎችን እንዲያበቁ የማድረግ አቅጣጫ መከተል አስፈላጊ ነው፡፡

 

በዝቅተኛ ክፍል የተማሪዎችን የንባብ ክህሎት ማሳደግ ለቀጣይ ትምህርታቸው መሰረት በመሆኑ ህጻናቱን የሚመጥን የንባብ መጽሃፍት በስፋት ማቅረብ እንዲያነቡ መትጋት ሊተኮረበት ይገባል፡፡ ይህንን ተግባር በማሳካት ረገድ በኩል መልካም የሚባሉ ጅምር ስራዎች ቢኖሩም ይህንን በማስፋት በስትራቴጂው መሰረት ተግባራትን በጥንቃቄ ፈጽሞ በሁሉም ትምህርት ቤቶቻችን የተመጣጠነ የውጤትና የስነ ምግባር መሻሻል እንዲኖር ከማድረግ አኳያ እጥረቶች የሚስተዋል በመሆኑ በቀጣይ ልዩ ትኩረት በመስጠት ሁሉንም ወደ ተመጣጠነ ደረጃ ማምጣት ይገባል፡፡ ለዚህም በተዘጋጀው ኤንስፔክሽን ማዕቀፍ መመሪያ መሰረት ት/ቤቶችን በውስጣዊና ውጫዊ ግምገማ ለይቶ ደረጃ በመስጠት እና ከዚህ የመነጨ ዕቅድ በማዘጋጀት ብዙዎች ወደ ተመጣጠነ ደረጃ እንዲመጡ አጥብቆ መስራት ይጠይቃል፡፡

1.2.3 . የመምህራን ልማት መርሃ ግብር

ተማሪዎች ተገቢውን እውቀት፣ ክህሎትና አስተሳሰብ ጨብጠው እንዲያድጉ መምህራን የማይተካ ሚና ስላላቸው፡፡ ይህ ወሳኝ ተግባር ውጤታማና የተሳካ እንዲሆን በየደረጃው የሚያስተምሩ መምህራንን በስታንደርዱ መሰረት ለደረጃው በማብቃት የትምህርት ጥራትን ማረጋገጥ ይገባል፡፡ በዚህም መሠረት የመጀመሪያ ደረጃ መምህራንን በዲፕሎማ ደረጃ በተለይም የመጀመሪያ ሣይክል መምህራን ስታንደርድ ከሰርተፊኬት ወደ ዲፕሎማ ደረጃ ከፍ እንዲል ለማድረግ በከተማው ለሚገኙ ሁሉም ነባር የሰርተፊኬት መምህራን ለደረጃው ብቁ ለማድረግ ሥልጠና ተሰጥቷቸዋል፡፡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርትን በተመለከተ የመጀመሪያ ሳይክል /9-10/ አዲስ የመምህራን የአሰለጣጠን ሥርአት በመዘርጋት መምህራን በመጀመሪያ ዲግሪ ከተመረቁ በኋላ የማስተማር ስነ ዘዴ በመስጠት ወደ ስራ የማሰማራት ሥራ እየተሰራ ነው፡፡ በሃገር አቀፍና በክልል በተዘረጋው ፕሮግራም መሰረት የተመደበልንን የሁለተኛ ደረጃ ሁለተኛ ሳይክል /11-12/ መምህራንን ለደረጃው ብቁ ለማድረግ በሁለተኛ ዲግሪ የሚሰለጥኑ መምህራንን ወደ ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች የመላክ ተግባር ስናከናውን ቆይተናል፡፡ አዲስ እጩ መምህራንን ለመመልመል የሚያስችል መመሪያ ተዘጋጅቶ ተግባራዊ መደረጉ የተሻሉ መምህራን ለማግኘት የሚያስችል ጅምር ታይቷል፡፡ የተከታታይ ሙያ ማሻሻያ አዲስ ማእቀፍና ቱልኪት ተዘጋጅቶ ተግባራዊ ሆኗል፡፡ የመምህራን የሙያ ፍቃድና እድሳት ሥርአት ተዘርግቶ ተግባራዊ መሆን ጀምሯል፡፡ ይሁንና እየተሰጡ በሉ የስራ ላይ ስልጠናዎች በተለይም በተሙማ ተጠቅሞ መርሃ ግብሩን በተቀመጠው ስታንዳርድ መሰረት በመተግበር የተማዎችን ውጤትና ባህሪ በስፋት ለማሻሻል ከማዋል አኳያ ብዙ መስራት ይጠበቅብናል ፡ ሌላው ደግሞ መምህራን በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለማድረግ የሙያ ፍቃድ ላይሰንስ እንዲኖራቸው በማሰብ በየዓመቱ በጽሁፍ ፈተና እንዲፈተኑ የተቻለ ሲሆን በ2016ዓ/ም ፖርቲፎሊዮ የተመዘኑ ሲሆን ፖርቲፎሊዮ ከ20% ተመዝኖ ወደ ዞን መላክ ችለናል፡፡

ፖርትፎሊዮ ያደራጁ መ/ራን ቁጥር ብዛት ወ 49 ሴ 47 ድ 96

በተጨማሪም መምህራኑ በሀገር ግንባታ ሂደት ውስጥ ያላቸው ሚና ከፍተኛና የማይተካ ሚና መሆኑን ተረድተው፤ ለሙያው ፍቅር አዳብረው፣ ባላቸውና በያዙት የእውቀት ደረጃ ከመፈጸም አንጻር ያልተሻገርናቸው ችግሮች መኖራቸው፤ አመራሩም መምህራኑ በትምህርት ስራ ውስጥ የማይተካ ሚና ያላቸው መሆኑን በመረዳት ተገቢውን እገዛና ድጋፍ አድርጎ በተማሪዎችና በትምህርት ሥርአቱ ላይ ለውጥ ለማምጣት ከመስራት አንጻር እጥረቶች መኖራቸው የሚስተዋሉ ችግሮች ናቸው፡፡

1.2.4. የሥርአተ ትምህርት መሻሻል መርሃ ግብር

የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የአገራችንና ዓለም አቀፋዊ ተጨባጭ ሁኔታዎችን ያገናዘበ በአዲሱ ፍኖተ ካርታ ሥርአተ ትምህርት ተቀርጾ በዚህም መነሻነት በበቂ ሁኔታ መጻሕፍት በማዘጋጀት የመማር ማስተማሩን ሂደት ለመምራት አዲስ በተቀረጸው ሥርአት ትምህርት መሠረት ከምንጊዜውም በተሻለ መብቃት ላይ በመመሥረት ጥራታቸውን የጠበቁ መፅሐፍት ተዘጋጅተው ተግባራዊ እየተደረጉ ይገኛሉ፡፡ በመሆኑም የመጽሃፍ ተምሪ ጥምርታውን ወደ ተቀመጠው ስታንዳርድ ለማምጣት ሰፊ ስራዎች ቢሰሩም ከ1ኛ - 8ኛ ክፍል ያሉ የትምህርት አይነቶች በፍኖተ ካርታው መሰረት መጽሐፍ እየታተመ ይገኛል ሌሎቹ ከ9ኛ - 12ኛ ክፍል መጻሕፍት በአዲሱ ስርዓተ ት/ት ታትመው የመጡትን መጽሐፍት ለ9ኛ እና ለ10ኛ ክፍል ተማሪዎች 1ለ1 የደረሰ ሲሆን ከ11ኛ-12ና ክፍል ላሉ ተማሪዎች 1ለ7 ማሰራጨት ተችሏል፡፡ ለተማሪዎች ማሠራጨት ያለባቸው አመቱ ከተጀመረ በኋላ ሳይሆን አስቀድሞ ባለው አመት ዝግጅቱ ተጠናቆ ት/ቤቶች ለእረፍት ከመዘጋታቸው በፊት ለተማሪዎች እንዲደርስ ከማድረግ አንጻር የሚስተዋሉ ክፍተቶችን መቅረፍ ይጠበቅብናል፡፡

 

ሌሎች ደጋፊ መጻሕፍትን ማዘጋጀት፣ የመጻሕፍት ግምገማ ማካሄድ፣ እንዲውም ስርአተ ትምህርት ዝግጅትና ትግበራ በሚጠይቀው ሥርአት መሠረት ተገቢውን ግምገማዎችን ማካሄድ የተጀመሩ ስራዎች ቢኖሩም አጠናክሮ መፈጸም ይጠበቅብናል፡፡ በአንዳንድ ት/ቤቶች የደረሱ መጽሃፍት ቶሎ በተማሪዎች እጅ ከማድረስ አንጻር ጉድለቶች ይታያሉ፡፡ ስለሆነም በ2017ዓ/ም እነዚህንና መሰል ችግሮችን የሚቀርፍ ስልት ቀይሶ መተግበር ይጠበቅብናል፡፡

1.2.5 የሥነዜጋና ሥነምግባር ትምህርት

ወጣቱን ትውልድ በጥሩ ስነምግባር፣ በዲሞክራሲና መልካም አስተዳደር ዙሪያ አውንታ አመለካከት በማስረጽ እንዲሁም በአገራችን ሁለንተናዊ እድገት ላይ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆን ለማድረግ የሥነዜጋና ስነምግባር ትምህርት ወሳኝ ሚና ይጫወታል፡፡ በዚህ መሰረት ተማዎች በት/ቤታቸው በተለያዩ አደረጃጀቶች በማደራጀት በክፍልና በት/ቤት ደረጃ ተሳትፏቸውን በማጠናከር የመማር ማስተማሩን ሂደት በሰከነ ሁኔታ እንዲካሄድ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እያበረከቱ ይገኛሉ፡፡ ይሁንና አሁንም ቢሆን የሰለጠኑ መምህራንን በተሟላ መልኩ ከመመደብ፣ ትምህርቱን ከት/ቤት ጊቢ በማውጣት እሴቶችን ወደ ህብረተሰቡ እንዲዘልቁ ለማድረግ፣ ትምህርቱ መጪው ትውልድ እውቀትና ክህሎት እንዲሁም ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብና መልካም ስነምግባር ያለው እንዲሆን ለማድረግ ያለውን አስተዋጽኦ በውል ተገንዝቦ ከመተግበር፣ ከተግባራዊ እውነታዎች ጋር አስተሳስሮ ትምህርቱን ከመስጠት፣ መምህራንም ትምህርቱን በእውቀት ባቻ ሳይሆን በአለካከትና በበሀሪ ለውጥ ለማምጣት የሚያስችላቸውን ሰነ ዘዴ በበቂ ሁኔታ ከመተግበር አኳያ አሁንም ችግሮች ይስተዋላሉ፡፡ በመሆኑም እነዚህን ችግሮች በመፍታት ትምህርቱን ትውልድን የመቅረጽ ተልእኮውን እንወጣ ለማድረግ የሰለጠኑ መምህራን መመደብ እዲሁም በየደረጃው የሚሰጠውን ትምህርት በአካባው ተጨባጭ ሁኔታ ጋር እንዲተሳሰሩ ከፍተኛ ጥረት ማድረግ  ይገባናል፡፡ ለዘላቂ ልማትና የዲሞክራሲ ግንባታ የማይለያዩና የማይነጣጠሉ በመሆናቸው ለሀገራችንም ህልውናና እድገት ወሳኝ በመሆናቸው ያገኘናቸውንም ውጤቶች በእኩል ተጠቃሚነት ማጣጣም የምንችለው ይህ ሲረጋገጥ ብቻ ነው፡፡ ከዚህ በተጫማሪ አሁን እየተስፋፋ የመጣውን የአክራሪነት አዝማሚያን ተገንዝቦ መቋቋም የሚችል አቅም፣ በተለይም የሌላውን መብት አክብሮ የሚኖር ትውልድ መቅረጽ ይገባል፡፡ ለዚህም የተጠናከረ ስራ መስራት ይጠይቃል፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ ተማሪው ጠንካራ ተሳታፊና ፈጻሚ እንሆን በከተማው ት/ቤቶች የተጀመሩ የተማሪ ፓርላማዎችን በዲሞክራሲያዊ መንገድ የማደራጀትና ተግባራዊ እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ የማድረግ አሰራር ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባዋል፡፡

1.2.6. የኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ማስፋፋት መርሃ ግብሮች 

በየደረጃው የሚሰጠውን ትምህርት በቴክኖሎጂ በመደገፍ የትምህርት ጥራትን ለማጎልበት የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡ ከዚህም አንዱ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ትምህርት አሰጣጥ የሳተላይት ፕሮግራሞችን በፕላዝማ አማካኝነት ማእከል አድርጎ የሚሰጥ ነው፡፡ የዚህ ትምህርት ውጤታማነት አንደኛ በፕላዝማ የሚቀርበው ፕሮጊራም ደረጃውንና ጥራቱን ጠብቆ ቴክኖሎጂውን አሟጦ መጠቀም ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ሁለተኛው የክፍል መምህሩ በፕሮግራሙ በተቀመጠው ስታንዳርድና መመሪያ መሰረት ተገቢውን ዝግጅት በማድረግ ራሱን በብቃት አዘጋጅቶ መሥራት ይጠይቀዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ትምህርት ቤቶቹ መብራት በሌለበት ጄኔሬተር፣ ተገቢው ኔትወርክ እንዲሁም የፕላዝማ ግብአቶች ማሟላት የግድ ይላል፡፡ እነዚህ የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎች ጥንቃቄ ይሚሹ ስለሆኑ መምሪያዎችን መሰረት አድርጎ መተግበር ወሳኝ ነው፡፡ ሲበላሹም ከቀላል እስከ ከባድ ብልሽቶችን ማስተናገድ የሚችል አቅም እንዲኖር ማድረግ የግድ ይላል፡፡  የሳተላይት ፕላዝማ ትምህርት ፕሮግራሞች በሲዲ ተቀርጾ ወደ ትምህርት ተቋማት እንዲሰራጩ መደረጉ ፕሮግራሙ ሳይቋረጥ ተግባዊ እንዲሆን ረድቷል፡፡ አይ.ሲ.ቲ ያለ ኢንተርኔት ሊታሰብ የማይችል መሆኑ እየታወቀ አብዛኞቹ የመሰናዶ ት/ቤቶች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ አለመሆናቸውና መሰረተ ልማቱ ባለባቸውም ቢሆን የኢንተርኔት አገልግሎት ክፍያን የመሸፈን አቅም ዝቅተኛ መሆን፣ በአንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች የሬዲዮ ትምህርት ፕሮግራሙን በተሟላ መልኩ አለመተግበር፣ የተገኙ ምርጥ ተሞክሮዎች በሁሉም አካባቢ እንዲሰፉ በዞን ደረጃ አቅጣጫ ቢቀመጥም በተፈለገው መጠን ማስፋፋት አልተቻለም፡፡ አቅም በፈቀደ መጠን የኮምፒዩተር እና የኢንተርኔት ጅምር ስራዎችን ለመስራት ግብአት አለሟሟላትና የተሟሉትንም በሚገባ ባለመጠቀም በቀላሉ እንዲፈላሹ የሚያደርጉ አሰራሮች ላይ ትኩረት አለመስጠት፣ የአይ.ቲ መምህራንን በበቂ ሁኔታ አለማቅረብ፣ ጎልቶ ይታያሉ፡፡ ስለዚህ ቴክኖሎጂውን አሟጦ ለመጠቀም ባለድርሻ አካላት ተቀናጅተው፣ ትኩረት ሰጥተው በጋራና በተናጥል የሚጠበቅባቸውን በተደራጀ መልኩ መወጣት ይኖርባቸዋል፡፡ ከተማ፣ ት/ቤት፣መምህር፣ተማሪ፣እና ባለድርሻ አካለት ግልጽ የሆነ ድርሻ ኖሯቸው የየራሳቸውን ሃላፊነት እንዲወጡ የተደራሽና የተቀናጀ አመራር መስጠት ያስፈልጋል፡፡ የኢንተርኔት አገልግሎትን የት/ቤቶች ተደራሽና ተጠቃሚ ከማድረግ አኳያ የታዩ ችግሮች ለመፍታት የሚያስችሉ ስልቶችን ቀይሶ መተግበር ይጠበቃል፡፡ በሚቀጥለው የክረምት ጊዜ ያሉ የኢኮቴ መሳሪያዎችን የመጠገን፣ የጎደሉትን የሟሟላትና በአጠቃላዩ ለቀጣዩ የት/ት ዘመን የማዘጋጀት ስራ መስራት ይገባዋል፡፡ በት/ቤቶች ያለበቂ ምክንያት በአመለካከት ችግር ጭምር የፕላዝማ ትምህርት ሲቆራረጥ ቆይቷል፡፡ ስለሆነም እነዚህን ችግሮች በ2017ዓ/ም መቀረፍ አለባቸው፡፡