ተልእኮ
በከተማው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ጉልህ አስተዋጽኦ የሚያደርጉ የሳይንስና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ስራዎችን ለህብረተሰቡ በአግባቡ በማልማት፣ በመተግበርና በማስፋፋት መዋቅራዊ ብሎም አገራዊ የተወዳዳሪነት አቅምና በቴክኖሎጂ የዳበረ የአሰራር ስርዓት መፍጠር ነው፡፡
ራዕይ
በ2030 በከተማው ውጤታማ የሆኑ የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂዎችን በፍጥነት የመማር፣የማልማት ፣የመፍጠር ፣የማላመድ እና የመጠቀም አቅም ተገንብቶ ማየት፡፡
እሴቶች
- በጎ ህሊናና ቅንልቦና፣
- የስራ ፍቅር ናትጋት፣
- ያልተገደበአስተሳሰብና ምናባዊ ጉዞ፣
- ለለውጥ በጋራ መስራት፤
- ውጤታችንም ሆነ ውድቀታችን የጋራችን ነው፤
- ችግርፈቺነት፤
- የማይረካ የመማር ጥማት፤
- ለትውልድ የሚተላለፍ መሠረት፣
- ቀልጣፋና ውጤታማ አሰራርና ቀጣይነት ያለው መሻሻል፣
ዓላማ
ጽ/ቤቱ የተሰጠውን ኃላፊነትና ተግባር ማለትም በከተማው ዘመናዊ የሆኑ ቴክኖሎጂዎችን በመመርመር፣ በመቅዳት፣ በማላመድና ያለዉን አቅም አሟጦ ለመጠቀም የሚያስችል የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የመዘርጋትና የማስፋፋት ሥራዎችን በስትራቴጂያዊ አስተሳሰብ ለመምራት፣ በሁሉም ደረጃ ባሉ ፈጻሚዎች መካከል ተግባቦትን ፈጥሮ የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ የልማትና የለውጥ ዘመን ዕቅድ ያለውን ሥራዎችን ቴክኖሎጂያዊ ድጋፍ መስጠት ነዉ፡፡
በአጠቃላይ በ2016 በጀት ዓመት የነበረን የዕቅድ አፈጻጸም ሁኔታ በመገምገም በጠንካራና በደካማጎን በመለየት የ2016 ድክመት በማረም ጥንካሬ አጎልብተን የዕቅድ አካል በማድረግ ለ2017 በጀት ዓመት የተቀመጡ ስጋቶችን ቀድመን በማወቅ መልካም አጋጣሚዎች እንደ ግብዓት በመጠቀም ባለፉት በ2016 አመታት ያልተፈጸሙትን ተግባራት በሚክስ መልኩ የዳበረ ዕቅድ በማዘጋጀት የየተግባሩን አላማ ለማሳካት ከወትሮው በተሻለ ሁኔታ የመፈጸም ወኔ ሰንቀን መገኘትና ይህንን የሚያረጋግጥ ዕቅድ ማዘጋጀት ይኖርብናል የሚል ስምምነት ላይ በመድረስ ከዚህ በታች ለሰፈረው ለ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ እንደ አስፈላጊነቱተ ወስዷል፡፡.