የቡኢ ኮንስትራክሽንና ኢንደስትሪያል ኮሌጅ

photo_2025-06-17_06-09-01
photo_2025-06-17_06-09-10
photo_2025-06-17_06-09-15
photo_2025-06-17_06-09-19
photo_2025-06-17_06-09-24
photo_2025-06-17_06-09-28
photo_2025-06-17_06-09-59
photo_2025-06-17_06-09-53
photo_2025-06-17_06-09-46
photo_2025-06-17_06-09-42
photo_2025-06-17_06-09-36
photo_2025-06-17_06-09-30
photo_2025-06-17_06-10-36
photo_2025-06-17_06-10-28
photo_2025-06-17_06-10-24
photo_2025-06-17_06-10-11
photo_2025-06-17_06-10-05
previous arrow
next arrow

የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ስርዓት ውጤትን መሰረት ያደረገ / ውጤት ተኮር እና ፍላጎትን መሰረት ያደረገ ሲሆን የሚጠናቀቀውም ወደ ሥራ ዓለም ሲቀላቀሉ በሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ነው፡፡

በ2017 ዓ/ም. የሥልጠና ዘመን በመደበኛ ፕሮግራም እየሰጠን ያሉ የሙያ መስኮች ዝርዝር፤

  1. BUILDING CONSTRUCTION SECTOR  (የግንባታ ሥራ ሙያ)
  2. METALS ENGINEERING AND MANUFACTURING SECTOR

(የማኒፋክቸሪግ ሙያ እና አጠቃላይ የብረታ ብረትና የመገጣጠምና ብየዳ ሥራ ሙያ)

  1. INFORMATION COMMUNICATION TECHNOLOGY SECTOR

(የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የኮምፒዩተር ሙያ)

  1. SURVEYING DEPARTMENT (የቅየሳ ሙያ)
  2. BUILDING ELECTRICAL INSTALATION-BEI (በህንፃ የኤሌክትሪክና ውሃ መስመር ዝርጋታ)
  3. GARMENT TECHNOLOGY (የልብስ ስፌትና ፋሽን ዲዛይን ቴክኖሎጂ)
  4. AUTOMOTIVE TECHNOLOGY SECTOR (የተሸከርካሪዎች ሙያ)

እነዚህ የተጠቀሱት የሙያ መስኮች ከመደበኛው ፕሮግራም በተጨማሪ መሠልጠና ለሚፈልጉ ሁሉ በማታ ፕሮግራም፤ በዊኬንድ ፕሮግራም እና በአጫጭር ጊዜ ሥልጠና የሚሰጥ ይሆናል፡፡

ኮሌጁ የአካባቢውን ማህበረሰብ ችግር ለመቅረፍ የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ተቋም ማለትም የሞተርና የባጃጅ ሥልጠና በመሥጠት መንጃ ፈቃድ እንዲያገኙ ያደረገ ሲሆን  የውጭ ሀገር ሥራ ሥምሪት ሥልጠና ከፍቶ በአጫጭር ጊዜ ሥልጠና እየሰጠ ይገኛል።

ስልክ ቁጥር- 0468830119, 0468830178, 0468830469,

አድራሻው በዚህ ይያዝ የሚቀየር ካለ ኢዲት እንደሚደረግ ይመቻች።

👉Telegram:- የቡኢ ኮን/ኢን/ኮሌጅ መረጃ መለዋወጫ ገፅ

👉E-mail:- mulugetamolla93@gmail.com

👉facebook- Buee construction and industrial college 13

BUEE2980 (Small)

የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኮሌጆች የበቃ የሰው ሀይል፤ ተነሳሽነትና የፈጠራ ክህሎት ያላቸው በዝቅተኛና በመካከለኛ ደረጃ ለኢንዱስትሪው ማቅረብ እና ቴክኖሎጂ በመቅዳትና በማላመድ ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ማቅረብና ኢንተርፕራይዞችን በገበያ ተወዳዳሪ ለማድረግ በመደገፍ የሥራ አጥነት ችግር በመቅረፍና የማህበረሰቡን ኑሮ እንዲሻሻል ወሳኝ ተልዕኮዎች ተሰጥቶት እየሰራ የሚገኝ ዘርፍ ነው፡፡

አንድ ሀገር በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለመሆን የሚያስፈልጉት ዋናዎቹ ብቁ የሰው ሀይል እና ምርጥ ቴክኖሎጂዎች ናቸው፡፡

የቡኢ ኮንስትራክሽንና ኢንደስትሪያል ኮሌጅ በ2007 ዓ/ም. በአካባቢው ማህበረሰብ እና በአካባቢው በ3ቱም የመንግስት መዋቅሮች፣ በሶዶ ክስታኔ ጉራጌ ልማት ማህበር፣ የጉራጌ ልማትና ባህል ማህበር  እና በመንግስት ትብብር የተመሰረተና ሥልጠና የጀመረ ኮሌጅ ሲሆን ለተከታታይ ዓመታት በተለያዩ ገበያ ተኮር በሆኑ የሙያ መስኮች ብቁና ተወዳዳሪ የሆኑ ባለሙያዎችን እያስመረቀ የሚገኙ ሲሆን በግል የራሳቸውን ሥራ ፈጥረው በመስራት፣ ተደራጅተው እየሠሩ፣ ትምህርታቸውን በማሻሻል፣ በመንግስትና የግል መ/ቤቶች በመቀጠር፣ እንዲሁም ወደ ኢንደስትሪው በመቀላቀል ላይ ይገኛሉ፡፡

የቀድሞው ደቡብ ክልል ቴክ/ሙያ ትም/ስል/ቢሮ ከጅምሩ በመረከብና እውቅና በመስጠት ለሥልጠና አስፈላጊ የሆኑ የሥልጠና ማቴሪያል፣ የሜቴክ ማሽነሪዎች፣ ፈርኒቸሮች፣ ቋሚ ዕቃዎች፣ ተሸከርካሪ፣ ትራንስፎርመር በከፍተኛ ወጪ በመመደብ የተደራጀ ሲሆን ኮሌጁ በማህበረሰብ የተመሠረተ እንደሆነ ስለሚታወቅ የማስፋፊያ ፕሮጄክት ከ28.5 ሚሊዮን ብር በላይ በመጀመሪያው ዙር በመመደብ የተለያዩ ህንፃዎች ማለትም ዘመናዊ ወርክሾፖች፤ ላይብረሪ፤ መሰብሰቢያ አዳራሽ፤ G+1 መማሪያ ክፍሎች ሌሎችም እየተሰሩ ሲሆን ሰኔ ወር 2015 ዓ/ም. የማስፋፊያ ፕሮጄክት ርክክብ ተደርጓል።