የቡኢ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት የ2017 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ የበይነ መረብ( online) ፈተና በስኬት እንዲጠናቀቅ ላቅ ያለ አስተዋፅኦ ላደረጉ አካላት የእውቅና እና የምስጋና ፕሮግራም አካሄደ።
=====ቡኢ=====
በምስራቅ ጉራጌ ዞን የቡኢ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ የበይነ መረብ(Online) ፈተና በስኬት መጠናቀቁን አስመልክቶ ተግባሩ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድርስ ድጋፍ ላደረጉ አካላት የእውቅና እና የምስጋና ፕሮግራም አካሂዷል።
የቡኢ ከተማ አስተዳደር ትምህርትቤቶች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አርጋዬ ወልዴ እንደገለፁት የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ የበይነ መረብ ፈተና እንደ ሶዶ ቡኢ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በስኬት እንዲጠናቀቅ ትልቅ አስተዋፅኦ ያደረጉት የኢፌድሪ ትምህርት ሚኒስተር ከ570ሺህ ብር በላይ ለሰርቨር አገልግሎት፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ ከ300ሺህ ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉን ፣ ቡኢ ከተማ አስተዳደር ከቁርጠኝነት ጀምሮ በብር ከ600 ሺህ ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉን ገልፀዋል።
አክለውም ኃላፊው ተግባሩ በስኬት እንዲጠናቀቅ በባለቤትነት ስሜት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱት ማለትም ለትምህርት ቤቱ አይሲቲ ዲፓርትመንትና መምህራን፣ ለቡኢ ከተማ አሰሰተዳደር ሳኢቴ ጽ/ቤት፣ ለሶዶ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤትና ሴክተር መስራያ ቤቶች፣ ለፖሊስና ለፀጥታ አካላት፣ ለቡኢ ኮንስትራክሽንና ኢንደስትሪያል ኮሌጅ፣ ለቡኢ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት፣ ለቡኢ ኢቲ 208 ፕርጀክት ፣ለመብራት አገልግሎትና ለኢትዮ ቴሌኮም ቡኢ ቅርንጫፍ ፣ለዳዲሞስ ኮሌጅና ለረጂ ድርጅቶችና ትልቅ ሚና ለተወጡ ለመላው ለከተማው ማህበረሰብ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
እንዲሁም ለዚህ ሁሉ ስኬት መሰረት ለጣሉት የትምህርት ቤቱ የቀድሞ ተማሪዎችና ወዳጆች ህብረት ኮሚቴ እና ለመላው የሶዶ ባለሀብት እንዲሁም የኮሚቴው ሰብሳቢ የነበሩት ፅጩ ዶ/ር ድንቁ ጌቱን አመስግነዋል።
በምስጋና ፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የቡኢ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ በለጠ ጫካ እንደገለፁት የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ፈተና ተቀናጅቶ መስራት ምን ያክል ውጤት እንደሚያመጣና የይቻላል መንፈስን ያላበሰን የበጀት ዓመቱ ትልቁ ስኬታችን ነው ብለዋል።
አክለውም ከንቲባው ለዚህ ሁሉ ስኬት እንደመነሻ የሚወሰደው የቀድሞ ተማሪዎችና ወዳጆች ህብረት ትምህተር ቤቱ አስተባብረው በመገንባታቸው ነው ብለው ለዚህም በሶዶ ማህበረሰብ እና በከተማው መንግስት ስም ትልቅ አምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።
ቀጥሎም ተግባራ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ትልቅ አስተዋፅኦ ላቀረከቱት አካላት እና በተለይም ለትምህርት ቤቱ አይሲቲ መምህራን እና የከተማው ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት የዲጂታል ላይብረሪ ከመገንባት በተጨማሪ ፈተናው ብስኬት እንዲጠናቀቅ ትልቅ አስተዋፅኦ አበርክተዋልና ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።
ክቡር ከንቲባው ተግባሩ እንዳይሳካ በተቃራኒው ሲሰሩ የነበሩ አካላት እንደነበሩ ገልፀው ከፀጥታ መዎቅርና በተሰራው ቅንጅታዊ አሰራር እኩይ ተግባራቸው ከሽፎ ተግባሩ ያለምን ችግር በስኬት ማጠናቀቅ ችለናል ብለዋል።
ለዚህም የድካማችን ሁሉ ውጤት የሚለካው በተማሪዎቻችን ውጤት ነውና ብለው ለተፈታኝ ተማሪዎች መልካም ውጤት እንዲገጥማቸው መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።
በምስጋና ፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የቡኢ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊና ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ደበበ አዳነ በበኩላቸውም እንደምንግስት የተጀመረው ፈተና በሰላም እንዲጠናቀቅ ትልቅ ምኞታችን ነበረ ብለው ለዚህም ፈተናው በስኬት መጠናቀቁን የተሰማቸውን ደስታ ገልፀው ድጋፍ ያደረጉ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
አክለውም ዋና የመንግስት ተጠሪው በክልላችን ደረጃ ሙሉ በሙሉ ግብዓት በራሱ ደረጃ አሟልቶ ማስፈተን የቻለው ብቸኛው ትምህርት ቤት የሶዶ ቡኢ ከፍተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መሆኑን ገልፀው ተግባሩን በበላይነት ለመራው ትምህርት ጽ/ቤት አመስግነዋል።
በመጨረሻም ለተግባሩ መሳካት አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት የእውቅ ሰርተፊኬትና የዋንጫ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
ዘገባው የቡኢ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው ።
ለተጨማሪ መረጃዎች ገፆቻችን ይከታተሉይ