ተልእኮ
ግልፀኝነትና ተጠያቂነት በሰፈነበት አሰራር ዘመናዊ የልማት ዕቅድና መረጃ፣ በመዘርጋት፣ የልማት አጋሮችን በማስተባበርና የሕዝብ ቁጥር ዕድገት ከኢኮኖሚ እድገት ጋር እንዲጣጣም በመስራት በከተማዉ ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ልማት እንዲረጋገጥ ማስቻል፡፡
ራዕይ
ፍትሃዊ የሀብት ድልድልና አጠቃቀም በማረጋገጥ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኀበራዊ ዕድገትን በማስፈን የከተማዉ ሕዝብ ከድህነት ተላቆ "ኢትዮጵያ አፍሪካዊት የብልፅግና ተምሳሌት" ሀገራዊ ራዕይ ተሳክቶ ማየት፡፡
እሴቶች
- ቆጣቢነት
- ወቅታዊና አስተማማኝ መረጃ
- ፍትሃዊነት
- ውጤታማነት
- ግልፀኝነትና ተጠያቂነት
- ተቆርቋሪነት
- ቀልጣፋ አገልገሎት
- በእቅድ መመራት
- ሕጋዊነት
የቡኢ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት በቡኢ ከተማ አስተዳደር ጊዜያዊ አማካሪ ምክር ቤት ተጀምረዉ ሳይጠናቀቁ ላደሩና ለአዳዲስ ካፒታል ፕሮጀክቶች 49,272,040 ብር በማፀደቅ በርካታ መሰተ ልማቶች መገንባት ተችሏል፡፡ ከተሰሩት በርካታ ካፒታል ፕሮጀክቶች ዉስጥ ለአብነት የጤና ጣቢያ ግንባታ ተጨማሪ ብሎኮች ግንባታ፣ ዲች ግንባታ፣ ካልቨርትና ፕሪካስት ግንባታ፣ አረንጓዴ መናፈሻ አጥር ግንባታ፣ ከተማ አስተዳደሩ የራሱን ኳሪሲ ሳይት እንዲኖረዉ ካሳ በመክፈል ባለቤት ሆኗል በዚህም በርካታ ሜ/ኪ የገረጋንቲ ምርት ማምረት ተችሏል፣የነጌሳ ቀበሌ መብራት ተጠቃሚ እንዲሆን የመብራት ዝርጋታ ወጪ ግምት ለመብራት አገልግሎት ዲስትሪክት 100% ተከፍሏል፣ ለመጠጥ ዉሃ ግንባታ ያለበትንና የሚጠበቅበትን የማችንግ ፈንድ ገንዘብ 100% ከፍሏል ግንባታዉ ከነበረበት ችግር በፍጥነት አሰፈላጊዉን ዉሳኔ እንደ ከተማ አስተዳደር በመወሰን ከችግር በማዉጣት የሲቪል ሥራዉና ቧንቧ ዝርጋታ በማጠናቀቅ ወደ ኤሌክትሮ መካኒካል ስራ ማስጀመርና ማፋጠን ተችሏል፣ለአዳሪ ት/ቤት ግንባታ የሚዉል 10 ሄ/ር መሬት ተገቢዉን ካሳ አስራ ሚሊዩን ብር የሚቆጠር በመክፈል ከይገባኛል ነፃ የማድረግ ሥራ ተሰርቷል፡፡