በተፈጥሮ መብረቅ ምክንያት ተበላሽቶ የነበረው የቡኢ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ሙሉ በሙሉ ተጠግኖ ወደቀድሞ ተሟላ አልግሎት ተመለሰ።

የቡኢ ከተማ አስተዳደር በ2017 በጀት ዓመት ዓመት የከተማው ማህበረሰብ የኑሮ ሁኔታ ምቹ ለማድረግ ካከናወናቸው ግራንድ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱና ትልቁ የነበረው የቡኢ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ነው ።

ይህ የውሃ ፕሮጀክት ምንም እንኳ ተመርቆ ለማህበረሰቡ ለ4 እና 5 ተከታታይ ወራት አገልግሎት ቢሰጥም ወቅቱ የክረምት ወቅት እንደመሆኑ መጠን ሐምሌ 25-2017 ዓ.ም በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት የውሃ ፕሮጀክቱ በከፋተኛ ሀይል ወደ ሪዘርቫየር እየገፉ የሚልከው የወልዲያ ጉድጓድ ትራንስፎርመር በመብረቅ ተመቶ ከአገልግሎት ውጭ ሆኖ ቆይቷል።

በዚህም የከተማ አስተዳደሩ አንገብጋቢ የማህበረሰቡ የውሃ ችግር ከግምት ውስጥ በማስገባት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ከክልል እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ትብብር በማድረግ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተቃጥሎ የነበረውን ትራንስፎርመር ተለዋጭ በማድረግ በተሟላ መልኩ ወደቀድሞ አገልግሎቱ መመለስ ችሏል።

አዲሱ የውሃ ፕሮጀክትም የትራንስፎርመር ቃጠሎ ብቻም ሳይሆን ቴክኒካል ችግሮች ገጥመውት የነበረ እንደሆነ እና አሁን ላይ ገጥሞት የነበረውንም ቴክኒካል ችግሮች ሙሉ በሙሉ ተጠግኖ ዛሬ ላይ ወደ ሁለቱም የውሃ ማሰራጪያ ሪዘርቫየሮች ውሃ የገባ ሲሆን ከአሁኑ ሰዓት ጀምሮ የውሃ ፕሮጀክቱ ወደ ቀድሞ ተሟላ አገልግሎቱ እንደተመለሰ የቡኢ ከተማ አስተዳደር ያስታውቃል።

ለቀጣይም የውሃ አገልግሎት ተቋምም እራሱን ችሎ ማስተዳደር እና ማዘመን እንዲችል የውሃ ታሪፍ ማሻሻያ ያደረገ ሲሆን የተደረገው የውሃው የታሪፍ ማሻሻያ ዝርዝር መረጃ በዚሁ ገፃችን የምናጋራችሁ ይሆናል።

ከተማ አስተዳደሩም በእስካሁኑ መላው የከተማው ማህበረሰብ የገጠመውን የውሃ ብልሽት ተጠግኖ ወደቀድሞ አገልግሎቱ እስኪመለስ ድረስ ላሳየን ትእግስትና ትብብር ላቅ ያለ ምስጋናውን ያቀርባል።

ዘገባው የቡኢ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው ።

ለተጨማሪ መረጃዎች ገፆቻችን ይከታተሉይ

0 0 votes
የመረጃው አጥጋቢነት
0 አስተያየት መስጫ
ቆየት ያሉ
የቅርብ ጊዜ Most Voted
Inline Feedbacks
View all comments
0
Would love your thoughts, please comment.x
()
x