3ኛው የምስራቅ ጉራጌ ዞን ልዩ ልዩ የስፖርት ሻምፒዮናና የባህል ስፖርቶች ውድድር ማስጀመሪያ ፕሮግራም እየተካሄደ ነው።
ጥር 14/2018
የምስራቅ ጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ አዘጋጅነት የሚካሄደው 3ኛው የዞኑ ልዩ ልዩ የስፖርት ሻምፒዮናና የባህል ስፖርቶች ውድድር ማስጀመሪያ ፕሮግራም እየተካሄደ ይገኛል።
በቡታጅራ ከተማ የሚካሄደው ዞናል ሻምፒዮና በስምንት ዘመናዊና በአምስት ባህል ስፖርት አይነቶች እንደሚካሄድ ተመላክቷል።
በአሁኑ ሰዓት የከተማ አስተዳደርና የወረዳ መዋቅር የስፖርት ሉዑክ ቡድኖችን የተለያዩ ትርኢት በማሳየት ወደቡታጅራ ከተማ መሰናዶ የእግር ኳስ ሜዳ እያመሩ ይገኛል።




