የምስራቅ ጉራጌ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ በቡኢ ከተማ አስተዳደር በመገኘት ድጋፍና ክትትል አደረገ።

የምስራቅ ጉራጌ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ በቡኢ ከተማ አስተዳደር በመገኘት ድጋፍና ክትትል አደረገ።

የካቲት 10/2018 ዓ.ም

የምስራቅ ጉራጌ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ቤተልሔም ታደሰ የዚህ ድጋፍና ክትትል ዋነኛ ዓላማ በከተማው ውስጥ የሚደረጉ ህገ-ወጥ ንግዶችን እና አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ ነጋዴዎችን ከመቆጣጠር አንፃር ሲሰራ የቆየውን ክንውን ለመገምገም እና ያሉ ጠንካራ ጎኖችን ለማስቀጠል ፣ የታዩ ክፍተቶችንም በመለየት ለቀጣይ ጊዜያት በማስተካከል የተሳካ ስራ ለመስራት እንዲያግዝ ለማድረግ እንደሆነ ተናግረዋል።

በነበራቸው ድጋፍና ክትትል ወቅትም ኃላፊዋ እንደ ዞን ጠንካራ የንግድ አደረጃጀት የሚገኙት ቡኢ ከተማ ውስጥ እንደሆነ ገልፀው የግብረ ሀይሉ ጠንካራ የሆነ ጥብቅ ቁጥጥር ባለማድረግ ዘርፉ በተፈለገው መጠን ውጤት እንዳይገኝ ስለሚያደርግ በተቀናጀ መልኩ ስራዎችን መስራት እንዳለበት ገልፀዋል።

የኑሮ ውድነቱን ከማረጋጋት አኳያም የተጀመሩት የሰንበት ገበያዎችን በማጠናከርና ሌሎች ተጨማሪ ማዕከላትን በማብዛት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የመጣውን የኑሮ ውድነት ላይ በትኩረት መስራት ይገባል ብለዋል።

የቡኢ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባና የገቢዎች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዘላለም ባህሩ በበኩላቸው በከተማዋ ላይ የህገወጥ ንግድ ቁጥጥር እንዳይስፋፋ ሰፊ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀው በዚህም ዘርፍ ተሰማርተው የተገኙት አካላትም እርምጃ እንደተወሰደባቸው ገልፀዋል ።

አክለውም መምሪያው በተደራጀ መልኩ ላደረጉት ድጋፍ እና ክትትል አመስግነው ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር የተነሱት ሀሳቦችን በመውሰድ ጥሩዎቹን በጥሩ ጎን በማስቀጠል መሻሻል ያለባቸውን ነጥቦች በማሻሻል፣ የተሻለ አፈፃፀም ለማሳየት እንደሚተጉ ተናግረዋል።

የምስራቅ ጉራጌ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ቢሮ ወ/ሮ ቤተልሔም ታደሰ በሰጡት ማጠቃለያ የድጋፍ እና ክትትሉን ዓላማ በመረዳት በጋራ በመሆን መስራት እንዳለባቸው እና ህገ-ወጥ ንግድ በተስፋፋ ቁጥር የከተማን ገቢ ስለሚያሳጣ ቀጥታ ወደ እርምጃ ከመገባቱ ቀደም ብሎ ለነጋዴው የህብረተሰብ ክፍል የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በማዘጋጀት አብዛኛውን ህገ-ወጥ ንግድ መቀነስ የሚቻልበት ሁኔታ ስላለ በቀጣይ ጊዜያት ይህን ተልዕኮ በመውሰድ መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።

በመድረኩ የምስራቅ ጉራጌ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ቤተልሔም ታደሰ ፣ የምስራቅ ጉራጌ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ማኔጅመንት አካላት ፣ የቡኢ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የገቢዎች ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ዘላለም ባህሩ፣የከተማው ንገድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ ባሩዳን ጨምሮ የህገወጥ ንግድ ቁጥጥር ግብረ ሀይል ዓብይ ኮሚቴዎች ተገኝተዋል ።

ለተጨማሪ መረጃዎች ገፆቻችን ይከታተሉይ

0 0 votes
የመረጃው አጥጋቢነት
0 አስተያየት መስጫ
ቆየት ያሉ
የቅርብ ጊዜ Most Voted
Inline Feedbacks
View all comments
0
Would love your thoughts, please comment.x
()
x