የተቋሙ ኃላፊ የአቶ እንዳሻው አለማየሁ መልዕክት
ወጣቶች በሀገራችንና በከተማችን በሚካሄደው ልማት ንቁ ተሳታፊና ከሚገኘው ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ እድገት እኩል ተጠቃሚ መሆናቸውን በማረጋገጥ ስፖርትን ባህሉ ያደረገ ጤናማና አምራች ዜጋን በመፍጠር በተሰማራበት የሙያ ዘርፍ ምርታማነትን ለማሳደግ፣ ስፖርት በኢኮኖሚ ልማት ግንባታ ሂደት ውስጥ የሚኖረውን ሚና እንዲወጣ ለማስቻል እንዲሁም ከአጠቃላይ የህብረተሰብ ተሳትፎ በመነሳት በመልካም ስብዕና የታነፁ ወጣቶችንና ምርጥ ስፖርተኞችን በማፍራት በሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ውድድር መድረክ ተሳታፊ፣ ተፎካካሪ፣ ተወዳዳሪና ተጠቃሚ በመሆንና ውጤት በማስመዝገብ በሀገር ገጽታ ግንባታ የወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት የበኩሉን ድርሻ ለመወጣት እንቅስቃሴ ጀምሯል፡፡
በመሆኑም የዓመቱ የልማት ዕቅድ በዘርፉ የሚታየውን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም ፖለቲካዊ የልማት እንቅስቃሴን በማጠናከር፣ ሁለንተናዊ ጥቅም ለማረጋገጥ የወጣቶች ስብእናና አመለካከት በማጎልበት፣ የወጣቶችን ሁለንተናዊ ብቃት በመገንባት ብቁና ተወዳዳሪ ዜጋ በማፍራት፣ በማህበረሰብ ስፖርት በየደረጃው እንዲስፋፋ በማድረግ፣ ጤናው የተጠበቀ አምራች ዜጋንና ብቁ ስፖርተኞችን በማፍራት እና በክልልና በአገር አቀፍ መድረኮች ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ ዘርፉ ለሰላም፣ ለአንድነትና ለብልጽግና የሚኖረውን ፋይዳ ለማጎልበት የ10 ዓመት የስፖርት ልማት ስትራቴጂክ ዕቅድ ተነድፎ እየተሠራ ይገኛል፡፡ በዚሁ መነሻ የጽ/ቤታችን የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡