ተልእኮ
በከተማው የነፃ ገበያ መርህ የተከተለ ንግድና ግብይት በማስፋፋት፤ በማዘመን፤ ህጋዊነትና ፍትሃዊነት በማስፈን የሸማቹ ህብረተሠብና የንግዱን ማህበረሠብ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ፤የንግድ ግብይቱ የመሪነት ሚና እንዲኖረው ማድረግ፡፡
ራዕይ
በ2020 በሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ ምርቶች በዓይነትና በመጠን፤በጥራት አድገው በቀጣይ ዕድገት ላይ የተመሰረተና በዓለም ተወዳዳሪ የሆነ ዘመናዊ ህጋዊና ፍትሃዊ የንግድና ግብይት ዘርፍ ተፈጥሮ ማየት ፡፡
እሴቶች
- ሥራዎችን በጋራና በተጠናከረ ቲምፕሪት መስራት ፤
- በዕቅድ መመራት ፤
- የማያቋርጥ ለውጥና መሻሻል ላይ መድረስ ፤
- ጊዜ እና የሰው ሀይልን በአግባቡ መጠቀም ፤
- መረጃን ለልማት ማዋል ፤
- ውጤት ያሸልማል፤
ዓላማ
-
- ንግድና ኢንቨስትመንት እንዲስፋፋ የተመቻቹ ሁኔታዎች እንዲፈጠሩ ያደርጋል፣
- በከተማው ውስጥ ንግድን ለማስፋፋትና ለማጠናከር ቀልጣፋ የግብይት ስርዓትና ተገቢ የንግድ አሰራር እንዲሰፍን ያደርጋል፣
- አግባብ ባለው ህግ መሰረት የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት ይሰጣል፣ ይቆጣጠራል፣ ይሰርዛል፣ የንግድ መዝገብ ያደራጃል፣
- በህግ በልዩ ሁኔታ ለሌላ አስፈፃሚ አካል የተሰጠው እንደተጠበቀ ሆኖ ህገ-ወጥ የግብርና ምርቶች ዝውውር ይቆጣጠራል፣ ይከታተላል፣ በህግ አግባብ እርምጃ ይወስዳል፣
- በህግ በልዩ ሁኔታ ለሌላ አስፈፃሚ አካል የተሰጠው እንደተጠበቀ ሆኖ የግብይት ሥርዓትን በበላይነት ይመራል፣ ይከታተላል፣ ድጋፍ ይሰጣል፣
- ተገቢ ያልሆነ የንግድ አሰራርን ለመከላከል የሚያስችል የተሟላ ስርዓት ይዘረጋል፣ የንግድ ህጎች መከበራቸውን ያረጋግጣል፣ አፈፃፀማቸውን ይከታተላል፣
- በሕግ መሰረት ለሸማቾች ጥበቃ ያደርጋል፣ የንግድ እቃዎችንና አገልግሎቶችን ሥርጭት ይቆጣጠራል፣
- አግባብ ባለው አካል የዋጋ ቁጥጥር የተደረገባቸውን መሰረታዊ የንግድ ዕቃዎችና አገልግሎቶች መተግበራቸውን ይቆጣጠራል፣
- አስገዳጅ የኢትዮጵያ ደረጃ ያላቸው የንግድ እቃዎችና አገልግሎቶች የደረጃውን መስፈርት ማሟላታቸውን ይቆጣጠራል፣ ከተዘጋጀላቸው ደረጃ በታች ሆነው በተገኙት ላይ እርምጃ ይወስዳል፣
- የሀገሪቱን ህጋዊ ስነ-ልክ ስርዓት በአግባቡ መተግበሩን ይቆጣጠራል፣
- የንግድ የዘርፍና የሙያ ማህበራት እንዲቋቋሙ ያበረታታል፣የተቋቋሙትንም እንዲጠናከሩ ያደርጋል፣
- ንግድን በማስፋፋት ረገድ የከተማና የገጠር፣ የከተሞች የእርስ በርስ ትስስር እንዲጠናከር ስትራቴጂ ይቀይሳል፣ ተግባራዊ ያደርጋል፣
- የግብርና ምርት ውጤቶች ጥራታቸው ተጠብቆ ተገቢውን ገበያ በሀገር ውስጥና በውጭ እንዲያገኙ ያደርጋል፣
- ዓላማውን ለማስፈፀም የሚችሉ ሌሎች ተዛማጅ ተግባራትን ያከናውናል፡፡
የቀጣይ አስር ዓመት መሪ የልማት ዕቅድ በዞናችን ብሎም በከተማችን የተጀመረውን የሕዳሴ ጉዞ በማፋጠን የከተማውን ህዝብ እኩል የልማት ተሳታፊና ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ከማረጋገጥ ረገድ የላቀ አስተዋጽኦ ያለው በመሆኑ የአስር ዓመት መሪ የልማት ዕቅድ፤ በሀገር አቀፍ እና በክልል ደረጃ የተዘጋጁ ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎች፣ የትኩረት አቅጣጫዎች፣ የሪፎርም ፕሮግራሞች፣ የተፈጠሩ አደረጃጀቶች እና ባለፉት ዓመታት የተመዘገቡ ውጤቶች፣ በአፈጻጸም ሂደት ያጋጠሙ ችግሮችና የተገኙ ተሞክሮዎች ለዕቅዱ እንደ መነሻ ተወስደዋል፡፡ ከዚህም ሌላ በአራቱ አመታት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመናት የተጀመሩና በግንባታ ሂደት ላይ ያሉ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ የልማት ፕሮጀክቶች በ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ ውስጥ ተካተው የሚከናወኑ በመሆናቸው የዕቅዱ መነሻ ተደርገው ተወስደዋል፡፡