ለትምህርት ዘርፍ የተመደበው ሀብት ለታለመለት ዓላማ ብቻ እንዲዉል እና በዘርፍ የተቀመጡ ግቦችን እንዲሳኩ በማድረግ የትምህርት ጥራትና ውጤት መሻሻል እንዲመጣ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ ተገለፀ።
ጥር 22/2018 ዓ.ም
በምስራቅ ጉራጌ ዞን የቡኢ ከተማ አስተዳደር ትምህርትቤቶች ፅ/ቤት በድጎማ በጀት አጠቃቀምና በጠቅላይ ሚንስትሩ የትምህርት ግቦች ዙሪያ ያተኮረ የምክክር መድረክ አካሂዷል።
የቡኢ ከተማ አስተዳደር ረዳት የመንግስት ተጠሪና የብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ደምሰው ተሰራ ለትምህርት ዘርፍ የተመደበው ሀብት ለታለመለት ዓላማ ብቻ እንዲዉል እና በዘርፍ የተቀመጡ ግቦችን እንዲሳኩ በማድረግ የትምህርት ጥራትና ውጤት መሻሻል እንዲመጣ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።
በዘርፉ የተቀመጡ የመቀነስ ግቦች ለማሳካት ትምህርት ቤቶች ያላቸውን አቅሞች በተገቢው ለይቶ መስራት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።
የትምህርት ጥራት ለማምጣት ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር ሁሉም ባለድርሻ አካል የድርሻውን ወስዶ በተገቢው መስራት ይገባዋል ብለዋል።
የቡኢ ከተማ አስተዳደር ትምህርትቤቶች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አርጋዬ ወልዴ የትምህርት አመራሩ የተቀመጡ የመቀነስ ፣የዜሮ እና የመቶ ፐርሰንት ግቦችን በተገቢው በመለየት ውጤት ለማምጣት ትኩረት ሰጥቶ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል ።
የከተማ ትምህርት ቤቶች ያላቸው ውስን ሀብት ለትምህርት ጥራት ብቻ እንዲዉል በማድረግ የተማሪዎች ውጤት እንዲሻሻል ማድረግ ይገባል ብለዋል።
በትምህርት ቤት ብቻ መተግባር የምንችላቸው ኢኒሼቲቮችን በመተግበር ውጤት ለማምጣት በትኩረት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።
በመድረኩ ላይ የድጎማ በጀት አጠቃቀም እና የጠቅለይ ሚንስትሩ የተቀመጡ የትምርት ዘርፍ ግቦች በተመለከተ በዝርዝር ቀርቧል።
የመድረኩ ተሳታፊዎች የተቀመጡ ግቦች እንዲሳኩ የተጀመሩ ስራዎች አጠናክሮ መቀጠል ያስፈልጋል ብለዋል።
በተማሪ ውጤት መሻሻል የተማሪው ስነ ምግባር ከፍተኛ ሚና ያለው ስለሆነ የተማሪ ስነ ምግባር በተመለከተ ወላጆች ኃላፊነታቸው መወጣት እንደመገባቸው ተናግረዋል።
የተመደበው በጀት ለታለመለት ዓላማ እንዲውል የትምህርት አመራሮች በትኩረት መስራት እንደሚጠበቅባቸው ጠቁመዋል።
በመድረኩ ላይ የከተማው አመራሮች፣የትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራንና የሒሳብ ባለሙያዎች እና የትምህርት ቤት የወላጆችና ተማሪዎች ህብረት ተጠሪዎች ተገኝተዋል።
ዘገባው የቡኢ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሚዩኒኬሽ ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው!!
ለተጨማሪ መረጃዎች ገፆቻችን ይከታተሉይ




