Slide 1

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ትምህርት ሚኒስቴር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አዳሪ ትምህርት ቤት ሲጎበኙ

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ትምህርት ሚኒስቴር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አዳሪ ትምህርት ቤት ሲጎበኙ

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ትምህርት ሚኒስቴር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አዳሪ ትምህርት ቤት ሲጎበኙ

Slide 2

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ መንግስት ዶ/ር እንዳሻው ጣሰው ቡኢ ከተማ አስተዳደር ተገኝተው በምስራቅ ጉራጌ ውስጥ ለሚገኙ ወጣቶች ሲያወያዩ

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ መንግስት ዶ/ር እንዳሻው ጣሰው ቡኢ ከተማ አስተዳደር ተገኝተው በምስራቅ ጉራጌ ውስጥ ለሚገኙ ወጣቶች ሲያወያዩ

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ መንግስት ዶ/ር እንዳሻው ጣሰው ቡኢ ከተማ አስተዳደር ተገኝተው በምስራቅ ጉራጌ ውስጥ ለሚገኙ ወጣቶች ሲያወያዩ

Slide 3
Slide 3
Slide 3
previous arrow
next arrow

ቡኢ ከተማ አስተዳደር


በ1942 ዓ.ም አካባቢ እንደተቆረቆረች ይነገርላታል ከሀገሪቱ ዋና ከተማ አዲስ አበባ በስተደቡብ አቅጣጫ በ100 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች የሶዶ ክስታኔ ማህበረሰብ የኢኮኖሚ የፖለቲካና የማህበራዊ ጉዳዬች ማሳለጫ እና መናገሻ  ናት። በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምስራቅ ጉራጌ ዞን ውሰጥም የአስተዳደር መገኛዋ ነው ከክልሉ መስተደድር መቀመጫ ሆሳዕና በ120 ኪሎ ሜትር ከዞኑ ዋና መቀመጫ ብታጅራ በ35 ኪሎ ሜትር ርቀት በስተሰሜን አቅጣጫም መገኛዋ ነው ።
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በምስራቅ ጉራጌ የቡኢ ከተማ አስተዳደር መንግስት የመንግስት መቀመጫ ከተማ= ቡኢ የስራ ቋንቋ = አማርኛ እና ክስታኒኛ የብሔር ስብጥር=  ሶዶ ክስታኔ ቤተ ጉራጌ   ኦሮሞ ፣ወላይታ ፣ሀዲያ፣አማራ እና ሌሎችም ሀይማኖት = ክርስቲያን ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ : ወንጌል አማኞች  እስልምና ጆባ (የህዋ ምስክር) እና ሌሎችም አስተዳደራዊ መንግስት ምስረታ =========  ነሐሴ 28/2010 ዓ.ም ህዝብ ብዛት የ 2017 ዓ.ም ግምት 50,000 (ሀምሳ ሺ) የ 1999 ዓ.ም ቆጠራ==+===== 18,000 ( አስራ ስምንት ሺ) የመሬት ስፍት፡ የአስተዳደር ወሰን 8698 ሄክታር የፕላን ወሰን 6171 ሄክታር የበጀት መጠን በ 2017 208,00,000

የቡኢ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ በለጠ ጫካ

ቡኢ ከተማ አስተዳደር ከአ.አ በ100 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የምትገኝ ሲሆን ለማዕከላዊና ደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች መግቢያ በር ናት ስለሆነም ከተማዋ ካላት ማዕከልነትና በከተማውና በዙርያው ፍፁም ሰላማዊ እና እንግዳ ተቀባይ ህዝብና ወጣት ያለበት በመሆኑ ሀገር አቋራጭ መንገደኞች ቱሪስቶች ከተማዋን በመምረጥ ለቁርስ፣ለምሳና ለማደሪያነት ይጠቀሟታል፡፡ ይህ ብቻ ሲሆን የትኛውንም ኢትዮጵያዊያን ለመኖር፣ለመነገድ እና ኢንቨስት ለማድረግ ብዙዎች ይመርጥዋታል፡፡ የውጭ ኢንቨስትመንቶች ባለሃብቶች ትላልቅ ካፒታል ያላቸው ፕሮጀክቶት እያሳረፈ ይገኛል፡፡

በመሆኑም ከተማዋ ለኢንቨስትመንት እጅጉኑ ተመራጭ የሆነች ከተማ ናት፡፡ የፋብሪካ ምርቶችን ለዋናው የሃገሪቱ ገበያ ለማቅረብ፣ከውጭ ለሚገቡ ግብኣቶች ለማቅረብ ከሞጆ ደረቅ ወደ ግብና ለፍጥነት መንገድ በአቅራቢያ መኖሩ፣በአካባቢው የኢንቨስትመንት ጥሬ እቃዎች፣የከበሩ ማዕድናት መኖሩ፣በግብርናው ዘርፍ አካባቢው አመቱን ሙሉ አምራችና ትርፋማ መሆኑ፣በቱሪዝሙ ዘርፍ በዩኔስኮ የተመዘገቡ ቅርሶችና ልዩ ልዩ መስህቦች መገኛ ከመሆኑ በተጨማሪ ኢንቨስትመንቱ የሚፈልጋቸው መሰረተ ልማቶች ተሟልተው የሚገኙ በመሆናቸው ተመራጭ ያደርገዋል፡፡ ይኸውም ከተማው የ24 ሰዓት የመብራት እና የኃይል ማከፋፈያ (substation) ባለቤት መሆን፣የከርሰ ምድር ውሃ በቅርበት ማግኘት የሚቻልበትና በአሁኑ ደረጃ ደግሞ አስተማማኝ የውሃ አቅርቦት መኖሩ፣ለፕሮጀክቶች ማሳረፊያ የኢንደስትሪ ዞን መካለሉና ተመጣጣኝ የመሬት አቅርቦት መኖሩ፣እንዲሁም ስራ ወዳድና የሰለጠነ ወጣት የሰው ሃይል በሰፊው መኖሩ ለኢንቨስትመንት ተመራጭ የሆነ ከተማ ነው፡፡

በመሆኑም ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የኢንቨስትመንት አማራጮች በማሰማራት ሀገርንም እራስን ተጠቃሚ ማድረግ ይቻላል፡፡

  1. በግብርና ኢንቨስትመንት በተለያዩ የአግሮ ፕሮሰሲንግና ተያያዥ ስራዎች
  2. በተለያዩ የማኑፋክቸሪን ኢንደስትሪዎች

3.በተለያዩ የማዕድን ፕሮሰሲንግና ምርት

  1. በሆቴል ቱሪዝምና ሆስፒታሊቲ ዘርፍ
  2. በትምህርት፣በጤና እና ልዩ ልዩ አገልግሎት ዘርፎች ላይ እንዲሰማሩ እንመክራለን ፡፡

ከተማዋ በአሁኑ ጊዜ በፈጣን የእድገት ግስጋሴ ላይ የምትገኝ ሲሆን አስተዳደሩም የህዝቡን ፍላጎትና የከተማዋን እድገት ቀጣይነት ሊያረጋግጡ በሚችሉ ዘርፎች ላይ እቅድ በመጣል ርብርብ እያደረገ ይገኛል፡፡

አስተዳደሩ የከተማዋን ደረጃ ከፍ ሊያደርጉ በሚችሉ መሰረተ ልማቶች ላይ በማቶከር በመንገድ ደረጃ ማሻሻል፣በውሃ ዝርጋታ ተደራሽነት፣በመብራ ኃይል አቅርቦት፣በአረንጓዴ ልማት፣በትምህርትና ጤና ተቋማት ግንባታና ደረጃ ማሻሻያ ላይ ስራዎች እየተሰሩ ሲሆን ቀጣይም የከተማዋን ፈርጅ ሊያሸጋግሩና እድገቷን ሊያረጋግጡ በሚችሉ የኮሪደር ልማት፣የወጣቶች ማዘውተሪያ ልማቶች እንዲሁም ሰፋፊ የመሰረተ ልማት ዝርጋታና ተደራሽነት ያላቸው ስራዎች የሚሰሩ ሲሆን መላው የከተማችን ህዝብ እንደወትሮው ሁሉ ድጋፋችሁና ተሳትፎአችሁ እንዲጠናከር ከወዲሁ መልዕክት እናስተላልፋለን፡፡      

አስተዳደሩ  የከተማው ተጨባጭ ሁኔታ መሰረት ያደረገ ዕቅድ በማዘጋጀት ላለፉት ሁለት የስትራቴጂክ ዕቅድ ዘመናት ተግባራዊ ሲያደርግ የቆየ ሲሆን በርካታ ውጤቶችም መመዝገባቸውን ከተደረጉ የእቅድ አፈጻጸም ግምገማዎች ማረጋገጥ ተችሏል፡፡

ሴክተሩ ተልዕኮውን እና የሚጠበቅበትን ውጤት ቀጣይነት ባለው መልኩ ለማሳካትና የላቀ አፈጻጸም ለማስመዝገብ የነደፋቸውን ግቦች ስኬት በየጊዜው በመፈተሽ ማሻሻያዎችን ከማድረግም በተጨማሪ በየዕቅድ ዘመኑ መጨረሻ የማጠቃለያ ግምገማዎችን በማድረግ ለቀጣይ አመታት አፈጻጸም መሻሻል የሚረዱ አዳዲስ ስልቶችን መንደፍ ይጠበቅበታል፡፡

ቡኢ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ን/ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ደበበ አዳነ

ከተማ አስተዳደሩ የታዳጊ ከተማ አስተዳደርነት እውቅና አግኝቶ ከ04/03/2011 ዓ/ም ጀምሮ ባልተሟላ የሰው ሃይልና የበጀት አቅም ወደ ስራ የገባ ቢሆንም በርከት ያሉ የልማት እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ስራዎች ሲያከናውን ቆይቷል፡፡ በ2012 ዓ/ም የተጓደለ የመንግስት አደረጃጀት በማሟላት የከተማ ፍትህ ጽ/ቤትና ፍርድ ቤት ወደ ስራ እንዲገቡ በማድረግ ከተማ አስተዳደሩ ሙሉ የመንግስት አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡ በሂደትም እንደ አዲስ መዋቅር የሚጎሉ ነገሮችን ወጧቱን፣ ባለሀብቱንና ነጋዴውን እንዲሁም መላው ማህበረሰብን በማስተባበር ቢሮ ከመገንባት ጀምሮ ያሉ ጉድለቶችን ለማሟላት ጥረት ተደርጓል፡፡ በሂደትም የገቢ አቅሙን ከአመት አመት በማሳደግና በየተቋማቱ አገልግሎት የሚሰጡና የከተማዋን እድገት ማፋጠን በሚችል አግባብ የሰው ሃይል ማሟላት ተችሏል፡፡ ይህን ተከትሎ ከተማ አስተዳደራችን በርካታ የተሞክሮ ምንጭ የሚሆኑ ተግባራት መፈፀም በመቻሉ ከተለያዩ  የክልሉ አካባቢዎች በመምጣት ከተሞች ልምድ ወስደዋል፡፡

ባጠረ ጊዜ በውስን የሰው ሃይልና በጀት በከተማችን ይህ ውጤት መመዝገቡ የብልፅግና ጉዟችን እውን እየሆነ መምጣቱን ያሳያል፡፡ ቀጣይነት ያለው ብልፅግና ለማረጋገጥ ከተማችን ለነዋሪዎቿ ሳቢና ማራኪ ለማድረግ፣ ሰላሟና ደህንነቷ ለማረጋገጥ ፣ማህበራዊ ፍትህ የሰፈነባት ለማድረግ የከተማችን ማህበረሰብና የመንግስት ቅንጅት ካሳለፍነው የስራ ጊዜ የበለጠ አጠናክሮ ማስቀጠል ያስፈልጋል፡፡ ሁሉአቀፍ ብልፅግናን ለማረጋገጥ በከተማችን የህዝብ ተሳትፎን ማረጋገጥ፣ ከተማዋን የአገልግሎት ማእከል ማድረግ፣ የሀገርና የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት አሁን ካለበት ይበልጥ ማስፋፋትና ወጣቱ በዚህ ዘርፍ ስራ እንዲፈጠርለት በሚያስችል አግባብ ለመምራት ጥረት እየተደረገ ይገኛል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በከተማው ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ የመጣውን ስራ አጥ ወደስራ ለማስገባት መጠነ ሰፊ ስራ እየተሰራ የሚገኝ ሲሆን በዋናነት ለብድር የሚሆን ሀብት በተለያዩ ጊዜያት የተሰራጩ ብድሮችን በማስመለስ ዳግም ለብድር በማመቻቸት፣ ከመንግስት ካዝና በመቀንስ ጭምር መመደብ የተቻለበት ሁኔታ ሲታይ ለጉዳዩ የተሰጠውን ትኩረት የሚያሳይ ነው፡፡ ሌሎች ሼድ ፣መሸጫና ማምረቻ ቦታ እንደዚሁም የገበያ ትስስር በመፍጠርም ለመደገፍ ጠረት እየተደረገ ነው፡፡ ከዚህ ውጪ ወጣቱ በፖለቲካው እንዲሳተፍና የመወሰን እድሉም እንዲጨምር እየተሰራ ይገኛል፡፡

ልዩ ልዩ ልማቶችን በተመለከተ የከተማው ማህበረሰብ ላለፉት ስድስት ዓመታት ሲጠይቀው የነበረው የከተማው ውሃ ፕሮጀክት ወደ አገልግሎት ያስገባን ሲሆን በስርጭት ሂደት እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችም እየፈታን እንገኛለን በዚህ አጋጣሚ ህዝባችን ላሳየው ትእግስት ያለንን ላቅ ያለ ምስጋና ማቅረብ እፈልጋለሁ!! ሌላኛው በከተማ የገንዘብ አቅም የሚገነባው ጤና ጣቢያ ሲሆን አሁን ላይ አብዛኛው ስራ የተጠናቀቀ ሲሆን በአመቱ መጨረሻ ወደ ስራ ይገባል ተብሎ ይገመታል፡፡ ከዚህ ውጪ በፌዴራል ትምህርት ሚኒስቴር እየተገነባ የሚገኘው አዳሪ ትምህርት ቤት ሲሆን ለዚህ የሚሆን ቦታ አርሶ አደሩን በውይይት ከማሳመን አንስቶ ለቦታው የሚያስፈልግ ከ9 ሚሊየን ብር በላይ ለካሳ በማመቻቸት ፕሮጀክቱ እውን እንዲሆን አድርጓል፡፡ ቀሪ የመሰረተ ልማት ስራዎች ከማፋጠን አኳያም የውስጥ ለውስጥ የጠጠር መንገድ ግንባታ፣ የዲች ግንባታና ኮብል ስራዎች በማፋጠን ላይ የምንገኝ ሲሆን እነዚህንና መሰል ማህበረሰቡን የሚያስጠቅሙ ስራዎች የፓርቲያችን እሳቤ ምንጮች ሲሆኑ ይበልጥ እየተጠናከሩ የሚቀጥሉ ይሆናሉ።

በመጨረሻም አሁን የገጠመንን የጸጥታ ችግር በጋራ በመከላከልና አላስፈላጊ እንቅስቃሴዎች በመቆጣጠር አጠቃላይ በፖለቲካው፣ በማህበራዊና በኢኮኖሚ ጉዳዮች ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግና የከተማውን እድገት ለማፋጠን በምናደርገው ርብርብ አባላችን፣ ወጣቱ፣ ደጋፊዎቻችንና መላው ማህበረሰብ ከጎናችን ሆኖ እንዲያግዘን እጠይቃለሁ አመሰግናለሁ!!

ወቅታዊ መረጃዎች