የቡኢ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት

selam_tsetita_zergaw (Small)

የተቋሙ ኃላፊ የአቶ ዘርጋው ንጉሴ መልዕክት

ሠላምና ፀጥታ ጽ/ቤት በከተማው ዘላቂ ሰላምና ፀጥታ ለማረጋገጥ በህዝብና በመንግስት የተጣለበትን ተልዕኮ ለመወጣት በሚደረገው እንቅስቃሴ በየደረጃ በርካታ ትግባራትን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡በዚህም በከተማው አስተዳደር መንግስት የተጀመረውን የልማት የመልካም አስተዳደርና የዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ የከተማው አስተዳደር ህዝብ በሙሉ አቅሙ ተጠቃሚ እንዲሆን ምቹ ሁኔታ በመፍጠር የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ለማሳካት ሰላምና ፀጥታ የማስጠበቅ ስራ በተሻለ ሁኔታ ማከናወን ይገባል፡፡ተገልጋዩ ህዝብ በአሁኑ ወቅት ከመንግስት የሚሰጠው አገልግሎት ውጤታማ፣ቀልጣፋ፣ፍትሃዊና ተደራሽ እንዲሆንለት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ሠላምና ፀጥታ ጽ/ቤት የከተማውን ሰላምና ደህንነት የማስጠበቅ ስራ ቀልጣፋና ተደራሽ ለማድረግ የመሰረታዊ ተቋማዊ ለውጥ በማድረግ ስራዎች የተሟላ ሆኖ እንዲተገበር የለውጥ ስራዎች በመተግበር የውጤት ተኮር ዕቅድ አፈፃፀም ምዘና ስርዓት በመከተል ማለትም ማሳኪያ ባላንስድ ስኮር ካርድ (BSC) በጽ/ቤትና በዋና ዋና በስራ እና ደጋፊ የስራ ሂደቶች እና ፈፃሚዎችንም ጭምር በስራ ተግባራቸው እየመዘንን ውጤታማ ስራዎችን በመፍጠር የተጠቃሚዎችን ፍላጎት እንዲረካ ማድረግ፡፡

ከ2016 ዓ.ም በጀት ዓመት አፈፃፀም እነዚህን የለውጥ/የቲም ስራዎች አጠናክሮ በመቀጠል የተሻለ አፈፃፀም እንዲኖረውና የሚፈልገውን ውጤት ለማምጣት ስትራቴጂውን የዕለት ተዕለት ስራ በማድረግ ቅድሚያ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን ለይቶ ለማከናወን ይህ የ2017 በጀት ዓመት ከዋናው መሪ ዕቅድ ከ7 ዓመቱ መነሻ የተወሰደ ዕቅድ ነው፡፡

በመሆኑም በከተማው በ7 ዓመቱ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ለማሳካት የሴክተሩን የ2017 ዓ/ም የቀጣይ አቅጣጫ እንደሚከተለው ተዘጋጅቷል፡፡

የመ/ቤቱ አጠቃላይ ገፅታ

ተቋሙ ከፍትህና ፀጥታ ጽ/ቤት ስር እራሱን ችሎ በአዋጅ ከተቋቋመ ወዲህ የከተማውን ህዝብ ሰላምና ፀጥታ በማስጠበቅ በኩል ከፍተኛ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ በዚህም የህ/ሰቡን ተሳትፎ ያረጋገጠ  የግጭት አፈታትና አስተዳደር ከዘመናዊ የግጭት መከላከልና አስተዳደር ስርዓት ጋር በማቀናጀት የከተማውን ሰላምና ፀጥታ አስተማማኝ ደረጃ ማድረስ ሲሆን ከመዋቅር አደረጃጀት ጀምሮ የፀጥታ ሀይሉን በማደራጀትና በማሰማራት ከአሁን በፊት ግጭት ተከስተው ያልተፈታባቸውን አካባቢዎች በመለየት እንዲሁም አልፎ አልፎ የተከሰቱ ግጭቶችና አለመግባባቶች በራሱ በከተማው እና ከአጎራባች ወረዳዎች ጋር በመቀናጀት ሰላምና ፀጥታ አስተማማኝ ደረጃ ላይ ለማድረስ በሚደረገው እንቅስቃሴ ሂደት ግጭቶችን በብቃት ለመከላከል ህ/ሰቡን ያሳተፈ የግጭት አፈታት ስልት በባህላዊና በዘመናዊ መልኩ ለመፍታት እንዲሁም የሰለጠነ የሰው ሀይልና ቁሳቁስ አደራጅተው መንቀሳቀስ ከጀመረ ወዲህ በርካታ ለውጦች መታየት ጀምሯል፡፡

እነዚህ ስራዎች ከከተማው ልዩ ባህሪ አንፃር በርካታ ፍላጎቶች የሚንፀባረቅበት ከመሆኑም ጋር ተያይዘው በተለያየ ምክንያት በህዝቦች መካከል የሚከሰቱ አለመግባባቶች ወደ ግጭት ሊያመሩ ስለሚችሉ ቀጣይ በከተማ አስተዳደራችን በሁሉም ሰፈሮች ሰላምና ፀጥታ ለማስፈን ጽ/ቤቱ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን ለመፈፀም አቅዶ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡

selam_tsetita_zergaw (Small)

የቡኢ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዘርጋው ንጉሴ

ተልእኮ

የከተማ አስተዳደሩ አስራርና አደረጃጀት ዘመናዊ በማድረግ ግጭትን፣የሀይማኖት አክራሪነት በብቃት ለመከላከል የሚያስችል የፀጥታ መረጃ ስርዓት በመፍጠር በህ/ሰቡ ንቁ ተሳትፎ የሚታገዝ የፀጥታ አስከባሪ ሀይል እንዲኖር በማድረግ የህግ ታራሚዎችንና የዜጎችን ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን በማስጠበቅ ሰላምና ፀጥታን ማስከበር፡፡

ራዕይ

የዜጎች ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችና ነፃነቶች ማስከበር፣ሰላምና ፀጥታ ማስፈን፣የህግ የበላይነትና መልካም አስተዳደር የተረጋገጠበት ከተማ አስተዳደር እንዲሆን የበኩሉን ከፍተኛ አስተዋፆ የሚያበረክት ተቋም ሆኖ ማየት፡፡

እሴቶች

  1. የሕብረተሰቡን ፀጥታና ደህንነት ማስጠበቅ ተግባራችን ነው
  2. ለህግ የበላይነት ቆመናል
  3. ፍትሀዊነት ታማኝነት መለያችን ነው
  4. የህዝብ አገልጋይነት መርሀችን ነው
  5. ግልፅነትና ተጠያቂነት መታወቂያችን ነው
  6. አሳታፊነት መርሀችን ነው
  7. ሚስጥር መጠበቅ ቃል ኪዳናችን ነው

ተልእኮ

የከተማ አስተዳደሩ አስራርና አደረጃጀት ዘመናዊ በማድረግ ግጭትን፣የሀይማኖት አክራሪነት በብቃት ለመከላከል የሚያስችል የፀጥታ መረጃ ስርዓት በመፍጠር በህ/ሰቡ ንቁ ተሳትፎ የሚታገዝ የፀጥታ አስከባሪ ሀይል እንዲኖር በማድረግ የህግ ታራሚዎችንና የዜጎችን ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን በማስጠበቅ ሰላምና ፀጥታን ማስከበር፡፡

ራዕይ

የዜጎች ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችና ነፃነቶች ማስከበር፣ሰላምና ፀጥታ ማስፈን፣የህግ የበላይነትና መልካም አስተዳደር የተረጋገጠበት ከተማ አስተዳደር እንዲሆን የበኩሉን ከፍተኛ አስተዋፆ የሚያበረክት ተቋም ሆኖ ማየት፡፡

እሴቶች

  1. የሕብረተሰቡን ፀጥታና ደህንነት ማስጠበቅ ተግባራችን ነው
  2. ለህግ የበላይነት ቆመናል
  3. ፍትሀዊነት ታማኝነት መለያችን ነው
  4. የህዝብ አገልጋይነት መርሀችን ነው
  5. ግልፅነትና ተጠያቂነት መታወቂያችን ነው
  6. አሳታፊነት መርሀችን ነው
  7. ሚስጥር መጠበቅ ቃል ኪዳናችን ነው

የተቋሙ ተግባርና ሃላፊነት

በከተማችን ሰላምና ፀጥታ በማስፈን መሰረታዊ የህዝባዊ እሴቶቻችን ተቋማዊና በተደራጀ መንገድ ከዘመናዊ አሰራሮች ጋር አቀናጅቶ የመምራትና የማስተባበር ስልጣን በአዋጅ የተሰጠው ለሠላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ነው፡፡

ተግባር ፡- ጽ/ቤቱ የተቋቋመለትን ዋና ዓላማ ለማሳካት የከተማውን ሰላም፣ፀጥታና ደህንነት አስተማማኝ ደረጃ ለማድረስና የዜጎች ሰብሀዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች እንዲከበሩ በማድረግ ቀጣይነት ያለው ልማትና የመልካም አስተዳደር  ለማስፈን የተለያዩ ተግባራትን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡

አደረጃጀት ፡- አደረጃጀቱም የከተማ አስተዳደር የፖሊስ ጽ/ቤት እና በጽ/ቤቱ በስር ያሉ ዋና ዋና የስራ ሂደቶች እና በመንደር ደረጃ ያሉ የሠላምና ፀጥታ አደረጃጀቶች እና ደጋፊ ስራ ሂደቶችን ጨምሮ የተቋቋመ ተቋም ነው፡፡