ተልእኮ
የሥራ ስምሪት አገልግሎት እንዲስፋፋ፣ የኢንዱስትሪ ሠላም እንዲሰፍን፣ የሠራተኛው ጤንነትና ደህንነት እንዲጠበቅ፣ የሥራ አካባቢዎች እንዲሻሻሉና የዜጐች ማህበራዊ ጥበቃ አገልግሎት (የአካል ጉዳተኞች ዕኩል እድልና ሙሉ ተሳታፊነት እንዲረጋገጥ፣ አረጋውያን ድጋፍና እንክብካቤ እንዲያገኙና ተሳትፎአቸው እንዲጐለብት፣ በልዩ ልዩ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች ምክንያት በድህነት፣ ተጋላጭነትና መገለል ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች የተለያዩ ድጋፎች) እንዲያገኙ ማድረግ የሴክተሩ ተልዕኮዎቹ ናቸው፡፡
ራዕይ
በ2022 የኢንዱስትሪ ሠላም ያሰፈነ፣ የሥራ ዕድሎች ፍትሃዊ ተጠቃሚነትና የማህበራዊ ደህንነት ልማትን ያጐለበተ ሞዴል ሴክተር ሆኖ ማየት
እሴቶች
- የኢንዱስትሪ ሰላም ማስፈን
- ማህበራዊ ደህንነትን ማስጠበቅ
- ለጾታ እኩልነትና ለአካል ጉዳተኞች ሙሉ ተሳትፎ ጠንክረን መስራት
- ለአረጋውያን እንክብካቤና ድጋፍ ትኩረት መስጠት
- የትብብር፤ የጋራ መግባባት የተቀናጀ አሰራርና የአሳታፊነት መርህ መከተል
- ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን መከላከልና መቆጣጠርን የሁሌም ስራዎቻችን አካል አድርገን መስራት
- የላቀ አገልግሎት
- የአካባቢ ጥበቃና ለተመጣጠነ የህዝብ ቁጥር እድገት መኖር ትኩረት ሰጥተን መስራት