የቡኢ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮምኒኬሽን ጽ/ቤት

የተቋሙ ኃላፊ የአቶ ዳንኤል ታዬ መልዕክት

ኮሙኒኬሽን በባህሪው መረጃን አውጥቶ መናገር፣ ስሜትን፣ ፍላጎትን፣ ሃሳብንና አመለካከትን በቃላት፣ በምስል ወይም በጽሁፍ መልክ ለሌላው መግለፅ የሌላውንም ሃሳብ መቀበል፣ አብሮነትን ፈጥሮ መጎዳኘት  "በእኛነት" መንፈስ የሚነገር  "እኛ" የሚል ሀሳብ የሚቀርብበት የተግባቦት ስርዓት ነው፡፡ ባለንበት የሉዓላዊነት፣ የመረጃና የባህል ዘመን ኮሙኒኬሽን ይበልጥ ተፈላጊ ነዉ። ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣው የአለም ሚዲያን በብቸኝነት ከመቆጣጠር እስከ ሰብዓዊ መብት ጉዳዮች፣ የጤናና የግብርና ልማት ዘመቻዎች፣ የንግግር ነጻነት እስከ የህብረተሰብ አንጋቢገቢ ጉዳዮች ድረስ ኮሙኒኬሽን እጅግ ተፈላጊ እንዲሆን አድርገዉታል፡፡

በታሪክ ከአንድ ክፍለ ዘመን በላይ ረጅም ርቀት የተጓዘው የዛሬዉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ተልእኮ ቀልጣፋና ዉጤታማ መረጃና የተግባቦት ሥርዓት በመዘርጋት ሀገራዊና የከተማ አስተዳደሩ የመንግስት አጀንዳዎች የተሻለ ተቀባይነትና ተፈፃሚነት እንዲኖራቸው ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃን በማቅረብ፣ ህዝቡ በዋና ዋና  ሀገራዊ ክልላዊ፤ ዞናዊና ከተማዊ ጉዳዮች ላይ መግባባት እንዲፈጥርና የሀገሪቱ መልካም ገጽታና ተሰሚነት እንዲጎለብት ስትራቴጂካዊ አመራር መስጠት ነዉ፡፡ የተቋሙ የተግባቦት ስራ ዘመነ ግሎባላይዜሽን የደረሰበትን የዲጂታል ሚዲያን፣ ፈጣን የመረጃ ስርጭትና የነቃ ህብረተሰብን መረጃ ፍላጎት ጥማት ለማርካት ከየትኛዉም ወቅት ልቆና ቀልጥፎ በመገኘት የዘርፉን ስራ መምራትና መከወን ተቋማችን ይጠበቅበታል፡፡ ዓለም አቀፋዊና ሀገራዊ ነባራዊና ተለዋዋጭ ሁኔታ ዉስጥ ሆኖ ህብረተሰቡ ከደረሰበት የአስተሳሰብ ከፍታ፣ የለዉጥና የእድገት ልህቀት ጋር የሚራመድ ተቋም መሆን ይጠበቅታል፡፡

ተቋሙ ቁልፍ የመንግስት የመረጃ ምንጭነቱንና የብቁ ቃል አቀባይነት ሚናውን በአግባቡ መወጣት እንዲችል የተቀናጀና የተናበበ የመረጃ ፍሰት እንዲኖር ማድረግ፤ ብቁ ምላሽ ሰጪ፣ አሳታፊና ተደራሽ መሆን ይኖርበታል፡፡ ህገመንግስቱን መሰረት ባደረጉ አንኳር ጉዳዮች፤ በብሔራዊ ጥቅሞች፤ በሰላምና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ፤ የሀገሪቱን ገፅታ በመገንባት ረገድ ከሁሉም የሚዲያ አውታሮች ጋር በትብብርና በመደጋገፍ መስራትም ይጠበቅበታል፡፡

ከዚህም አኳያ ያሉንን የሚዲያ መሳሪያዎቻችንን እና የተለያዩ የሚዲያ አማራጮችን በመጠቀም የከተማው ህዝብ በሚኖርበት ከተማ ውስጥ ስለሚከናወኑ የመሰረተ ልማት የመልካም አስተዳደር፤ኢንቨስትመንትና የተለያዩ ሁነቶች ላይ ትኩረት በመስጠት ለህዝብ መረጃ የመስጠት ስራችንን አጠናክረን ቀጥለናል፡፡

ይህንን ተልዕኮዉን ለመወጣት፣ የተቀናጀና ውጤታማ ስራ ለማከናወን እንዲቻል በብቁ ተቋማዊ አደራጃጀት፣ የሰዉ ሃይል፣ ቁሳቁስና አሰራር ራሱን ማጠናከርና ማዘመን ይኖርበታል፡፡ ከሚዲያዎች ጋር በትብብርና መደጋገፍ አብሮ መስራትን፣ መረጃና ቴክኖሎጂ መጋራትን፣ የአቅም ክፍተቶችን በመለየት እዉቀትና ክህሎትን ለመገንባት መስራት ይገባናል፡፡

የተቋማችን መንግስት ኮሙኑኬሽን አገልግሎት አሰጣጥ ለማዘመን እና ከተማ አስተዳደሩ ከተዋቀረበት ጊዜ ጀምሮ በየዘርፉ የሚከናወኑ የከተማ አስተዳደሩ የልማትና መልካም አስተዳደር ተግባራትን በምስል(Photo)፤ በተንቀሳቃሽ ምስልና በድምፅ(Audio-Visual) ሰንዶ ለማቆየትና ለውሳኔ ሰጪነት በሚሰጥ መልኩ የመረጃ ማእከል (Data center) በማቋቋም ላይ እንገኛለን፡፡

በስተመጨረሻም ውድ የከተማችን ነዋሪዎች! ዘመኑን የዋጀና አውዱን የተረዳ ትውልድ ለመፍጠር መጽሐፍትን ማንበብ ባህሉ ያደረገ ዜጋ ማፍራት ያስፈልጋል፡ ስለሆነም የቡኢ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የከተማው ህዝብ የማንበብ ባህሉን ለማዳበርና ማንበብ እየፈለጉ መጽሐፍት ማግኘት ያልቻሉ አንባቢያን ችግር ለመቅረፍ የተለያዩ ይዘት ያላቸው የታሪክ፤ የፍልስፍና፤ የሳይንስ፤ የስነልቦናና የልብወለድ መጽሐፎችን ከተለያዩ በጎ አድራጊ ግለሰቦችና ተቋማት በቁጥር ከአንድ ሺህ በላይ መፅሐፍትን ያሰባሰብን ስለሆነ ከጽ/ቤታችን ተውሳችሁ ማንበብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

እንዲሁም ተቋማችን የአንባቢያን ፍላጎት ለማርካት በብዛትም ሆነ በዓይነት በርካታ ይዘት ያላቸው መፅሐፍትን በማፈላለግ ላይ የሚገኝ ሲሆን ማንኛውም ግለሰብም ሆነ ተቋም ከዚህ በፊት አንብቦ ወይም ተጠቅሞ ቤት/ቢሮ ውስጥ ያስቀመጣቸው መፅሐፍቶች እንዲሁም ገዝቶ ድጋፍ በማድረግ በእውቀት፤በክህሎትና በጥበብ የበለፀገ ዜጋ ለመፍጠር በምናደርገው ርብርብ ላይ የበኩላችሁን እንድትወጡ መልዕክታችን እናስተላልፋለን፡፡

በተጨማሪም የተገለጹት አንኳር ጉዳዮችንና የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ተልዕኮዎችን በማሳካት በኩል ጉልህ ሚና ይኖረዋል፡፡ በመሆኑም በጽ/ቤታችን ያሉ የተላያዩ የሚዲያ አማጭ በመጠቀም የምናሰራጫቸዉን መረጃዎች በማጋራት(Share)፣ በመዉደድ(like) እና ገንቢ አስተያያት(comment) በመጠስት መረጃዎችን ተደራሽ ለምታደርጉ ሁሉ ምስጋናችን ወደር የለዉም፡፡

ዓላማ

አገልግሎቱ በሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ በርካታ ዓላማዎችን እንደሚያሳካ የሚጠበቅ ሆኖ በዋናነት በሚከተሉት ዓላማዎች ላይ ትኩረት ያደርጋል፡፡እነሱም፡-

    1. በመንግሥት የመረጃና የተግባቦት ወይም ኮሙኒኬሽን ሥርአት የቃል አቀባይነትና ስትራቴጅካዊ የመሪነት ሚና መጫወት፤
    2. መንግሥት ፖሊሲዎች፣ መርሐ ግብሮች፣ ፕሮግራሞችና ዕቅድችን መሠረት ያደረጉ አጀንዳዎችን በማዘጋጀት ቀልጣፋና ውጤታማ የመረጃና የተግባቦት ሥርአትን በመፍጠር ምልዓተ ሕዝቡን ተደራሽ ማድረግና ተሳትፎዉን ማሳደግ፤
    3. በልዩ ልዩ መንግሥት ተቋማት፣ የሚዲያ አዉታሮችና በባለድርሻ አካላት መካከል ውጤታማና ቀልጣፋ የመረጃና የተግባቦት ሥርአትን በመፍጠር ኹሉም የኅብረተሰብ ክፍሎች ከመንግሥት መረጃ ዕኩል የሚያገኙበትና ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ምቹ ሁኔታ መፍጠር፤
    4. መንግሥትን ፖሊሲዎች፣ መርሐ ግብሮችና ፕሮግራሞችን መሠረት በማድረግ ኅብረ- ብሔራዊ አንድነትን፣ የሀገር ፍቅርን፣ ሀገራዊ ተግባቦትን፣ የዳሞክራሲ ባህልን ለማጎልበትና ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ የሚያስችል ቀልጣፋና ውጤታማ የመረጃና የተግባቦት ሥርአት ለመዘርጋት የሚያስችል ስትራቴጂካዊ አመራር መስጠትን ያካተተ ነው፡፡

 

{"remix_data":[],"remix_entry_point":"challenges","source_tags":[],"origin":"unknown","total_draw_time":0,"total_draw_actions":0,"layers_used":0,"brushes_used":0,"photos_added":0,"total_editor_actions":{},"tools_used":{},"is_sticker":false,"edited_since_last_sticker_save":false,"containsFTESticker":false}

የቡኢ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮምኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዳንኤል ታዬ

ተልእኮ

ከተማዊ፤ ዞናዊ ፤ክልላዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ህብረተሰቡን ለሁለንተናዊ ተሳትፎ የሚያነሳሳ ፤የሚያጎለብትና ተጠቃሚ የሚያደርግ የኮሚዩኒኬሽን ስርዓት በመዘረጋት ተአማኒ እና ጥራቱን የጠበቀ መረጃ ተደራሽ ማድረግ ነው፡፡

እሴቶች

    1. ግልጽነትና ክፍት፣
    2. ብዙኃንነትና እኩልነት፣
    3. ተደራሽነት፣ወቅታዊነትና ምላሽ ሰጭነት፣
    4. ሙያዊነትና ፈጠራ፣
    5. ተኣማንነትና ትክክለኛነት፣
  1. ራዕይ

በ2025 ዓም የከተማችን ህዝቦች በላቀ መረጃ በልፅገው የጋራ ውሳኔ ሰጪነታቸው ተረጋግጦ በመካከላቸው እኩልነት፤አንድነትና ወንድማማችነት ተጠናክሮ ማየት

የተቋሙ ተግባርና ሃላፊነት

ተቋሙ በደንብ ቊጥር 488/2014 ከተሰጡት ዋና ዋና ተግባርና ኃላፊነቶች ውስጥ የሚከተሉት ይገኛሉ፡-

    1. ከሕዝብ ሰላምና ደኅንነት፣ ከታላላቅ ሀገራዊ ክንዉኖች፣ ከተፈጥሮና ሰው ሠራሽ አደጋዎች፣ ከዘመቻ ሥራዎች ወዘተ ጋር በተያያዘ በየደረጃዉ መረጃዎችን መሰብሰብ፣ መተንተን፣ ተጨባጭ ሁኔታዎች ላይ የተመሠረቱ አጀንዳዎችን መቅረጽ፣ ማሰራጨትና በመሠረታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግባባትን መፍጠር፣
    2. መንግሥት አጀንዳና አፈጻጸሞችን ተደራሽ የሚያደርጉ በጠንካራ አደረጃጀትና ኔትዎርኪንግ የተደገፈ የዲጂታል ሚዲያ አሠራር መዘርጋት፣
    3. በሀገሪቱ እየተስፋፋ ባለዉ አካታች ሥርአት የተፈጠሩ መልካም እድሎች፣ በሀገራዊ ታሪካዊ ቅርሶችና ባህላዊ እሴቶች፣ የሀገሪቱን አህጉራዊና ቀጠናዊ ተሳትፎን የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እንዲገነዘብ መርዳትና በጎ አመለካከትን ማዳበር፣
    4. መንግሥት ፖሊሲዎችን፣ መርሐ ግብሮችን፣ አገልግሎቶችና አፈጻጸሞች እንዲሁም ዜጎችን በሀገራዊ ልማትና ዳሞክራሲ ሒደት ግንባታ ለማሳተፍ የሚያስችል የተቀናጀና የተናበበ የተግባቦት ሥራን ከፌዴራልና ከክልል የኮሙኒኬሽን ተቋማት ጋር በትብብር መሥራት፣
    5. የመንግሥትን ፖሊሲ፣ መርሕ እና ዕቅድ መሠረት በማድረግ ማኅበረሰብን ተደራሽ የሚያደርጉ አጀንዳዎችን ማዘጋጀት፤ እንዱሁም የማኅበረሰብን ሁለንተናዊ ተሳትፎ የሚያሳድጉ ንቅናቄዎችን መፍጠር፤
    6. በየጊዜው የሚፈጠሩ ሀገራዊ አጀንዳዎችንና ንቅናቄዎችን ውጤታማነት መገምገምና ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ማሳወቅ፣
    7. የመንግሥትን አጀንዳዎች ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ ኹሉንም ዓይነት የኢንፎርሜሽን ቴክኖልጂ ውጤቶችን በብቃት፣ በጥራትና በስፋት መጠቀም፤
    8. የመንግሥትን ፖሊሲ፣ መርሕና ዕቅድ መሠረት በማድረግ፤ እንዲሁም ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን፣ ሀገራዊ ተግባቦትን፣ የዳሞክራሲ ባህል መጎልበትን፣ ሁለንተናዊ ብልጽግና መፍጠርንና የመሳሰሉትን መሠረት በሚያደርግ ማዕቀፍ ሚዲያዎችን መምራት፤
    9. ለፌዳራል መንግሥት ተጠሪ በኾኑ መሥሪያ ቤቶችና ተቋማት የሚገኙ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊዎችን ከየመሥሪያ ቤቶቹና ተቋማቱ የበላይ ኃላፊዎች ጋር በመመካከር መመደብ፣ መከታተልና ሥራቸውን መቆጣጠር፤ አቅማቸዉን መገንባት፣
    10. ለመንግሥት ተጠሪ የአሥር መሥሪያ ቤቶችና ተቋማት ለሚመድቡ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊዎችና ለሥራቸው የሚኾን የአሠራር መርሕ፣ ደረጃና ሥርአት ማውጣትና ተግባራዊ እንዲደረግ ማስቻል፤
    11. ለክልል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን መሥሪያ ቤቶች የኹለትዮሽ የተግባቦት ሥራን ለማከናወን የሚያስችል አቅምን መገንባት፣
    12. ከሕዝብ ሰላምና ደኅንነት፣ ከታላላቅ ሀገራዊ ክንውኖች፣ ከተፈጥሮና ሰው ሠራሽ አደጋ፣ ከዘመቻ ሥራዎች፣ ከግጭቶች እና ከመሳሰለት ጋር በተያያዘ በሚዲያ አዝማሚያዎች ዳሰሳና በሕዝብ አስተያየት ጥናቶች መረጃዎችን በመሰብሰብ፣ በመተንተን፣ ድምዳሜዎችን ለባለድርሻ አካላት ማሳወቅና አገልግሎት ላይ እንዲውሉ ማድረግ፣
    13. በተተነተኑ፣ በተደራጁና ይዘታቸዉ በታወቀ መረጃዎች ላይ በመመሥረት ጋዜጣዊ መግለጫዎችን፣ ጋዜጣዊ ጉባኤዎችንና ምላሾችን እንደአስፈሊጊነቱ ማዘጋጀት፤
    14. የቅድመ ቀውስ ትንተና በመሥራት እንዲሁም ድንገት በሚፈጠሩ አደጋዎችና ግጭቶች ዙሪያ መረጃዎችን በፍጥነት በማሰባሰብና በማደራጀት ትክክለኛዉን መረጃ በፈጣን መንገድ ለባለድርሻ አካላትና ለዜጎች ማቅረብ፤
    15. የመንግሥትን አጀንዳዎች ወደ ሕዝብ ለማስረጽ የሚረዳ የሙዚቃ፣ የፊልም፣ የቴአትር፣ የባህላዊ ክንውኖችና የመሳሰሉትን ዝግጅቶችን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ማዘጋጀት ወይም ዝግጅቶችን መደገፍ፤
    16. በብሔራዊ ጥቅም፣ የሀገር ሉዓላዊነት፣ ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች፣ ሰላም፣ ደኅንነትና የመሳሰሉት ጉዳዮች ላይ ከግል ሚዲያዎች ጋር ተቀራርቦ መሥራት፤
    17. የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች በመንግሥት ዋና ዋና የትኩረት አጃንዳና አፈጻጸም በሚወጣላቸው የይዘት መርሐ ግብር መሠረት ለሕዝብ ጋዜጣዊ መግለጫዎችን እንዲሰጡ ማድረግ፤
    18. በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ኢትዮጵያን በሚመለከት የሚወጡ የሚዲያ መረጃዎችን ዳሰሳ በመሥራት ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ያቀርባል፡፡ ከዳሰሳው መረጃዎች በመነሣትም አስፈሊጊዉን የኮሙኒኬሽን ስትራቴጂ ይቀርጻል፣
    19. በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ የሀገር ሽማግላዎችን፣ ታዋቂ ሰዎችን፣ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎችን፣ ጋዜጠኞችን፣ ታዋቂ ነጋዴዎችን፣ ስፖርተኞችን፣ ማኅበራዊ አንቂዎችን እና የመሳሰሉትን በልዩ ልዩ የቴክኖሎጂ መንገዶች በመመዝገብና መረብ በመዘርጋት (ኔትወርክ) ሀገራዊ መረጃዎች፣ ሐሳቦች፣ አጀንዳዎችና ሌሎችም እንዲደርሷቸው በማድረግ፣ በመንግሥት አጀንዳዎች ላይ መግባባት እንዲፈጠር ማድረግ፣
    20. የተለያዩ የኮሙኒኬሽንና ሚዲያ ፎረሞችን በማቋቋም እና ሌሎች የግንኙነት መድረኮችን በመፍጠር ወጥነት ያለው የተግባቦት ዕቅድ፣ ክትትልና ግምገማ ሥርአት በመፍጠር የሀገሪቱን ገጽታ መገንባት፡፡

 

 

photo_2025-06-13_14-29-26
photo_2025-06-13_14-29-27