ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 08/2017 በአራት ዙር ሲሰጥ የነበረውን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ የበይነ መረብ (Online) ፈተና ያለምንም ችግር በስኬት መጠናቀቁን የቡኢ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት አስታወቀ።

ቡኢ ፤ ሀምሌ 08/2017 (መንግስት ኮሚዩኒኬሽን)፦ በምስራቅ ጉራጌ ዞን በቡኢ ከተማ አስተዳደር በሶዶ ቡኢ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ2017 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 08/2017 ዓ/ም በተፈጥሮ ሳይንስና በማህበራዊ ሳይንስ በጥቅሉ በአራት ዙር ወንድ 204 እና ሴት 263 ድምር 467 በይነመረብ ( online) ሲሰጥ የነበረውን ፈተና ያለምንም ችግር በስኬት መጠናቀቁን የቡኢ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አርጋዬ ወልዴ ገልፀዋል።

ኃላፊው አክለውም ፈተናው ተጀምሮ በስኬት እንዲጠናቀቅ ላቅ ያለ አስተዋፅኦ ላደረጉ አካላት ምስጋናቸውን ያቀረቡ ሲሆን በተለይም ከስድስት ወር በላይ ተግባሩ በስኬት እንዲጠናቀቅ ላደረጉት የ/ቤቱ የአይቲ መምህራን፣ የቡኢ ከተማ አስተዳደር ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ጽ/ቤትና ባለሙያዎች ፣ ለሶዶ ወረዳ እና ለቡኢ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ተቋማት ፣ ለአጋር ድርጅቶች ፣ ለፀጥታ አካላት ፣ ለመብራት አገልግሎትና ኢትዮ ቴሌኮም ቡኢ ቅርጫፍ እንዲሁም ለከተማው ለመላው የትምህርቱ ማህበረሰብ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በዕለቱም ተፈታኝ ተማሪዎች የተማሩበትን ዩኒፎርም ለቀጣይ አቀም ለሌላቸው ተማሪዎች መማሪያ ይሆናል በሚል ዩኒፎርማቸውን ለትምህርት ቤቱ አስረክበዋል።

ዘገባው የቡኢ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው ።

ለተጨማሪ መረጃዎች ገፆቻችን ይከታተሉይ

0 0 votes
የመረጃው አጥጋቢነት
0 አስተያየት መስጫ
ቆየት ያሉ
የቅርብ ጊዜ Most Voted
Inline Feedbacks
View all comments
0
Would love your thoughts, please comment.x
()
x