የተቋሙ ኃላፊ የአቶ አዳነ ጌቱ መልዕክት
የ2ዐ17 በጀት ዓመትየቡኢ ከተማ ፍትህ ጽ/ቤት ዕቅድ ተግባራዊ ለማድረግ ከሰባት አመት እቅድ ጋር /2ዐ16-2ዐ22/ በማናበብ መነሻ ተደርጐ የተዘጋጀ ሲሆን የከተማው የትኩረት አቅጣጫዎችን በመለየት የነበሩትን የአመራሩንና የፈጻሚ ሁለንተናዊ የአቅም ክፍተት ለመገንባትና ቁልፍ ጉዳዩች ላይ በማተኮር በጥናት ላይ የተመሰረተ ስልጠናዎችን መስጠት፣ ተቋሙን ለስራ ምቹና የተደራጀ እንዲሆን ማድረግ፣ በከተማው መልካም አስተዳደር ማስፈን እንዲቻል የሚከሰቱ የወንጀል ጉዳዩችን በማጣራት፣ ክስ በማቅረብና በመከራከር እንዲሁም የከተማው መንግስት የሚከሰስባቸውን የፍ/ሔር ጉዳዩችን በመከታተል የመንግስትና የሕዝብ ጥቅም ማስጠበቅና ፍትህን ተደራሽ ማድረግ በተጠረጠሩበት ወንጀል በህግ ጥላ ስር በማረፊያና በማረሚያ ቤቶች እንዲቆዩ የተወሰነባቸው ዜጐች ሰብዓዊ መብት አጠባበቅን በሚመለከት ተገቢውን ክትትል በማድረግ አያያዛቸው በህግ አግባብ መሆኑን የማረጋገጥ እና አምራች ዜጋ እንዲሆኑ ማድረግ ነው፡፡
ሰነዶችን መመርመር፣ ማረጋገጥ እና መመዝገብ፣ የዲስኘሊን ጉዳዩቻቸውን በመከታተል እንዲወሰን ማድረግ፣ ለፍትህ ስርዓቱ ውጤታማነት አጋዥ ማድረግ እና በተቋቋሙበት ዓላማ መሰረት መንቀሳቀሳቸውን መከታተልና ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታና ልማታዊ አስተዋጽኦ የበኩላቸውን እንዲወጡ ማድረግ የትኩረት አቅጣጫዎች ናቸው፡፡
እነዚህን ተግባራዊ ለማድረግ ያሉን ምቹ ሁኔታዎች በመለየት የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ እና የህዝብ ንቅናቄ መድረክ በየደረጃው ባሉ የአስተዳደር ዕርከን የሚገኙ የጎን መዋቅሮች በሚሰጡት አገልግሎቶች ላይ ውይይት በማድረግ በሴክተሩ ውስጥ ያለውን የመልካም አስተዳደር ችግሮች፣ መንስኤዎችና መፍትሔዎች መለየት የሚያስችል መድረኮች በመፈጠራቸው አበረታች ውጤት ተመዝግቧል፡፡ በመሆኑም በ2ዐ16 ዓ.ም 9 ወራት ጊዜ ውስጥ የተገኙ ውጤቶች አጠናክሮ ለማስቀጠል የ2ዐ17 በጀት ዓመት ዕቅድ እንደሚከተለው ተዘጋጅቷል፡፡