በሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት የክልሉን ገቢ አሁን ካለበት ወደ 55 ቢሊዮን ብር ለማድረስ ታቅዶ እየተሰራ ነው :- ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር )

በሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት የክልሉን ገቢ አሁን ካለበት ወደ 55 ቢሊዮን ብር ለማድረስ ታቅዶ እየተሰራ ነው :- ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር )

(ሆሳዕና፣ጥር 22/2018 )በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ለታማኝ ግንባር ቀደም ግብር ከፋዮች የእውቅናና የሽልማት መርሐ ግብር በሆሳዕና ከተማ ተካሂዷል

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር) በመርሐ ግብሩ ማጠቃለያ በሰጡት የስራ መመሪያ እንደገለጹት ዜጎች በላባቸው ሰርተው ከሚያገኙት ገቢ ለመንግስት የሚገባውን ማበርከት የስልጣኔ መገለጫ ነው።

በክልሉ የልማት ፕሮጀክቶችን ጀምሮ የማጠናቀቅ ስራ ስኬታማ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ የህብረተሰቡን ኑሮ ማሻሻል ላይ ትኩረት መደረጉን ጠቁመዋል።

ሰላም የሁሉም ነገር መሰረት ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ዜጎች 24 ሰዓት ሰርተው የሚለወጡበት ክልል መፍጠር ተገቢ ስለመሆኑም አብራርተዋል።

የንግዱ ማህበረሰብና የክልሉ አርሶ አደሮች የክልሉን ልማት በላቀ ደረጃ ለማገዝ እያደረጉት ለሚገኘው ጥረት ርዕሰ መስተዳድሩ ምስጋና አቅርበዋል።

‎ጠንካራ የገቢ አሰባሰብ ስራዎችን በመስራት ማዕከላዊ ኢትዮጵያንና አገራችን ኢትዮጵያ ተሸላሚ ለማድረግ መስራት ተገቢ ነው ብለዋል ርዕሰ መስተዳደሩ።

‎ትላልቅ ፕሮጀክቶችን በማቀድ ክልሉን የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ በሁሉም ዘርፍ ተግባራዊ ለሚደረጉ ስራዎች ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ገቢ በአግባቡ መሰብሰብ እንደሚገባም አጽንኦት ሰጥተዋል።

አርሶ አደሮች ለክልሉ ልማት ከ13 ቢሊዮን ብር በላይ እገዛ ማድረጋቸውንም ርዕሰ መስተዳድሩ በአብነት ጠቅሰዋል።

‎በሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት በሰባቱም ክላስተሮች መሰረታዊ የልማት ስራ እውን ለማድረግ እየተሰራ ስለመሆኑም ርዕሰ መስተዳድሩ አመላክተዋል።

‎በክልሉ የስራ ባህልን ለማሳደግ እየተሰራ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ለዚህም መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማስፋፋት ላይ ትኩረት መደረጉን አብራርተዋል።

‎የክልሉን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ የተጠናከሩ ስራዎች ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል።

‎በክልሉ ያለውን የአገልግሎት ደረሰኝ በአግባቡ በመሰብሰብ ከደረሰኝ ገቢ በየዓመቱ እስከ ሶስት ቢሊዮን ብር መሰብሰብ እንደሚቻል ተናግረዋል።

‎በሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት የክልሉን ገቢ አሁን ካለበት ወደ 55 ቢሊዮን ብር ለማድረስ ታቅዶ እየተሰራ እንደሚገኝም ርዕሰ መስተዳድሩ አስታውቀዋል።

0 0 votes
የመረጃው አጥጋቢነት
0 አስተያየት መስጫ
ቆየት ያሉ
የቅርብ ጊዜ Most Voted
Inline Feedbacks
View all comments
0
Would love your thoughts, please comment.x
()
x