የቡኢ ከተማ አስተዳደር ፍርድ ቤት

BUEE2911 (Small)

የቡኢ ከተማ አስተዳደር ፍርድ ቤት ፕሬዝንዳንት ክብርት የትናየት እንዳለ መልዕክት

ፍ/ቤቶች ከሶስቱ የመንግስት አካላት መካከል አንደኛው ሲሆን ስራቸውም ህግን መተርጎም ነው፡፡ ስለሆነም የቡኢ ከተማ/አስ/ የመ/ደ/ፍ/ቤት የከተማ አስተዳደሩን ተከትሎ እንደ ሌሎቹ የመንግስት አካላት የተቋቋመ ሲሆን ፍ/ቤቱ ከተቋቋመበት ከሰኔ 17 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ ከሶዶ ወረዳ ፍ/ቤት ለመነሻ ስራ ሊያስጀምር በሚችል መልኩ ውስን የሰው ሀይልና ቁሳቁስ በተደረገለት ድጋፍ መሰረት ስራውን በመጀመርና ቀጥሎም የራሱን በጀት በማስበጀት አዲስ ሰራተኛ እንዲቀጠር በማድረግ ተቋሙ በአሁኑ ሰዓት 14 ሰራተኞች ይገኛሉ፡፡ በፍ/ቤቱ ቅልጥፍናን ለማረጋገጥ ባለፉት ተከታታይ አራት አመታት በርካታ ስራዎችን በማከናወን ላይ እንገኛለን ፡፡ ከዚህም ውጪ የስራ ቦታን ለሰራተኞችም ሆነ ለባለ ጉዳዮች ምቹ ከማድረግ አንፃር ከከተማው ቦታ ተቀበለን   ጊዜያዊ  ሰባት ክፍሎች ሰርተን አገልገሎት እየሰጠን እንገኛለን ፡፡ ፤በየወሩ የቀጠሮ ፋይሎችን የያዙት ዳኞች ሪፖርት ለፍ/ቤቱ ፕሬዝዳንት እና ለከፍተኛ ፍ/ቤት ሪፖርት እያደረጉ ሲሆን በዚህ ሪፖርት ላይ መዝገቦች የወሰዱትን ጊዜና መዝገቡ ላይ ያጋጠመው የውስጥና የውጪ ችግሮች ጭምር በመለየት ከስታንዳርድ ውጪ ጊዜ የወሰዱ ፍያሎችን ተገምግመው ለውስጥ ችግሮች በግብረ መልስ መዝገቡን ለያዘው ዳኛ በመስጠት እና ለውጫዊ ችግሮች ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በጥምር ከፍትህ ማሻሻያ እና በዜጎች ቻርተር በውይይት መድረኮች በመቀናጀት እና በመነጋገር ችግሮችን በመፍታት ቅልጥፍናን ለማረጋገጥ ጥረት እያደረግን እንገኛለን የተሻለ አመርቂ ውጤትም አስመዝግበናል፡፡   የዳኝነት ጥራትን ለማረጋገጥ የከተማ ቦታ ይዞታ ነክ ክርክሮችን ጉዳዩን በያዙት ዳኞች እስከ ቦታው በመሄድ ተመልክቶ አጣርቶ የመወሰንና ወጥነትን ለማረጋገጥ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ነው ፡፡ በተጨማሪም ውስብስብና የህዝብ ጥቅም ባለባቸው አከራካሪ ጉዳዮች ላይ በዳኞች ፓናል ውይይት እያደረግን የተጣራ ውሳኔ ለመስጠት በትኩረት እየተሰራ ይገኛል፡፡ በተጨማሪም ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ባለጉዳዮች አቤቱታ ሲያቀርቡ እንዳይቸገሩ በቀላሉ ተደራሽ እንዲሆን የተለያዩ ማመልከቻዎችን ለመፃፍ ያወጡት የነበረውን ወጪ ለመቀነስ የተለያዩ ማመልከቻ ተኪ ፎርሞችን በባለሙያ አዘጋጅተን በነፃ እየሰጠን በመሆኑ ተገልጋዮች ይህን አገልግሎት ከባለሙያ ለማግኘት ያወጡት የነበረውን ከፍተኛ ወጪ ማስቀረት ተችሏል፡፡በተጨማሪም የዜጎች ፍትህ የማግኘት መብት ገንዘብ በማጣት ምክንያት እንዳይገደብ ለማድረግ የድህነት ማረጋገጫ ላቅረቡ የተከላካይ ጠበቃ በመወከል አቅመ ደካማ ለሆኑና ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች የህግ ድጋፍ እና ምክር አገልግሎት በነፃ መስጠት የአገልግሎት አሰጣጡን የበለጠ ተደራሽ ለማድረግ ጥረት በማድረግ እና ተገልጋዬችን ከገንዘብ አቅም ማጣት ጋር ተያይዞ ፍትህ እንዳይዛባ ነፃ ጥብቅና እንዲያገኙ ለማድረግ እየሰራን እንገኛለን ፍ/ቤታችን የመንግስት እና የህዝብ ጥቅም የሚነሱ ለወንጀል እና የፍታብሔር ጉዳዮች ማለትም በተለይ የሴቶች እና ህፃናት መብት ጥሰት የህፃናት ቀለብ ጥያቄ የግብዓት /ብድር /እዳዎች አመላለስ እና የሸማቾች መብት ጥሰት የሚመለከቱ ጉዳዮችን በአጠቃላይ ፍ/ቤቱ ከማንኛውም ተፅዕኖ ነፃ እና ገለልተኛ በሆነ መንገድ ስራውን ለማከናውን እና ለተገልጋዮች ቀልጣፋና ተደራሽ እንዲሆን እና ጥራቱን የጠበቀ የዳኝነት አገልግሎት መስጠት እንዲችል ህብረተሰቡን ከብልሹ አሰራር እራሱን በመጠበቅ መብቱን በህግና በህግ ብቻ ለማስከበር ለፍርድ የሚያቀርባቸው ማንኛቸውም አቤቱታዎች ጉቦ በመክፈል እና በዘመድ አዝማድ በመተማመን ሳይሆን የጠራ ማስረጃ እና እውነታውን ይዞ በመቅረብ እና መብቱን በህግ   አግባብ ብቻ   እንዲያስከብር መልህክቴን ለማስተላለፍ እወዳለው፡፡

ፍርደ ቤት የትናየት

የቡኢ ከተማ አስተዳደር ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክብርት የትናየት እንዳለ

ተልእኮ

ከማናቸውም ተጽዕኖ ነፃ በመሆን ፣ ሕግን በመተርጐም ፣ ክርክሮች ላይ እልባት በመስጠት በሕግ ብቻ የሚመራ የዳኘነት አካል በመፍጠር በገለልተኝነት ፣ በሕዝብ አገልጋይነት ስሜት ፣ በቅልጥፍና እና በሚዛናዊነት ለሕብረተሰቡ ጥራት ያለው የዳኝነት አገልግሎት በመስጠት የሕግ የበላይነት እንዲረጋገጥ ማድረግ፡፡

ራዕይ

በ2022 ዓ.ም የቡኢ ከተማ የመ/ደ/ፍርድ ቤት ገለልተኛና ነፃ በመሆን ፍትህን ለሁሉም ህብረተሰብ በሁሉም ቦታ እና በተፈለገው ጊዜ እና ጥራት በመስጠት መልካም ስምና ዝና ያተረፉ ሆኖ ማየት ነው፡፡

እሴቶች

  1.  ነፃነትና ተጠያቂነት (independence and accountability)
  2. ገለልተኝነት (neutrality/independence
  3. እኩልነት (equality)
  4. ሚዛዊነት (fairness)
  5. ብቃት (competence and professionalism)
  6. ምላሽ ሰጪነት (responsiviness)
  7. የአገልግሎት ጥራት (quality in service)
  8. ግልጽነት (transparency)
  9. ሀቀኝነትና ታማኝነት (honesty and loyality

ተልእኮ

ከማናቸውም ተጽዕኖ ነፃ በመሆን ፣ ሕግን በመተርጐም ፣ ክርክሮች ላይ እልባት በመስጠት በሕግ ብቻ የሚመራ የዳኘነት አካል በመፍጠር በገለልተኝነት ፣ በሕዝብ አገልጋይነት ስሜት ፣ በቅልጥፍና እና በሚዛናዊነት ለሕብረተሰቡ ጥራት ያለው የዳኝነት አገልግሎት በመስጠት የሕግ የበላይነት እንዲረጋገጥ ማድረግ፡፡

ራዕይ

በ2022 ዓ.ም የቡኢ ከተማ የመ/ደ/ፍርድ ቤት ገለልተኛና ነፃ በመሆን ፍትህን ለሁሉም ህብረተሰብ በሁሉም ቦታ እና በተፈለገው ጊዜ እና ጥራት በመስጠት መልካም ስምና ዝና ያተረፉ ሆኖ ማየት ነው፡፡

እሴቶች

    1.  ነፃነትና ተጠያቂነት (independence and accountability)
    2. ገለልተኝነት (neutrality/independence
    3. እኩልነት (equality)
    4. ሚዛዊነት (fairness)
    5. ብቃት (competence and professionalism)
    6. ምላሽ ሰጪነት (responsiviness)
    7. የአገልግሎት ጥራት (quality in service)
    8. ግልጽነት (transparency)
    9. ሀቀኝነትና ታማኝነት (honesty and loyality

የተቋሙ ተግባርና ሃላፊነት

የቡኢ ከተማ አስተዳደር ፍርድ ቤት ዋና ዋና ተግባራት