“በቀጣይ በፓርቲ መሪነት የሚተገበሩ ስራዎች በላቀ ደረጃ በመፈፀም የከተማው ማህበረሰብ ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት እንሰራለን ።”አቶ ደበበ አዳነ ፦የቡኢ ከተማ አስተዳደር የብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ
የቡኢ ከተማ አስተዳደር የብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የ2017 ዓ.ም የፓርቲ ስራዎች ማጠቃለያ ፣የ2018 ዓ.ም የዕቅድ ዝግጅት ኦረንቴሽን እና የእውቅና መድረክ አካሂዷል።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የቡኢ ከተማ አስተዳደር ዋና የመንግስት ተጠሪና የብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደበበ አዳነ በ2018 ዓ.ም በፓርቲ መሪነት የሚተገበሩ ስራዎች በላቀ ደረጃ በመፈፀም የከተማው ማህበረሰብ ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት እንሰራለን ብለዋል።
2017 ዓ.ም በፓርቲ መሪነት በከተማ አስተዳደሩ ውስጥ በርካታ የልማት ስራዎች የተሰሩበት፣ አመራሩ የመሪነት ሚናው እንዲወጣ የተደረገበት ፣ውጤታማ ሰው ተኮር ስራዎች የተሰሩበት ፣በሁሉም ግንባር ያሉ አደረጃጀቶች እንዲጠናከሩ እና ሚናቸውን እንዲወጡ የተደረገበት የትጋትና የስኬት ዓመት እንደነበረ ተናግረዋል።
ውጤታማ የሆነ የኢኒሼቲቭ እና የአቅመ ደካሞች ቤት እድሳት እና ማዕድ ማጋራት በማካሄድ ውጤታማ ሰው ተኮር ስራዎች የተሰሩበት ዓመት እንደሆነ አመላክተዋል።
የተለጠጠ የገቢ አሰባሰብ ዕቅድ በማዘጋጀት የተሻለ አፈፃፀም በማምጣት በርካታ የልማት ስራዎች የተሰሩበት ዓመት እንደነበረ ተናግረዋል።በጤና ዘርፍ ወረርሽኞችን በመከላከልና የጤና ጣቢያ ግንባታ ማከናወን መቻሉንም አመላክተዋል።
በአንድ ከተማ አንድ ፕሮጀክት መርህም የቡኢከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ፅ/ቤት የአገልግሎት አሰጣጥ ማዘመን ስራ መሰራቱን እና በ40/60 የተሻለ የህበረተሰብ ተሳትፎ የታየበት እንደሆነ አመላክተዋል።
በትምህርት ዘርፍም የቅድመ አንደኛ ክፍል የተማሪዎች ምገባ ማካሄድ እና እየተሰራ የሚገኘው አዳሪ ትምህርት ቤት ግንባታ ክትትል የተደረገበት እንደሆነ አመላክተዋል።
በቀጣይ የፓርቲ ተቋም ግንባታ ፣አደረጃጀቶችን ማጠናከር፣የአመራርና የአባላት ጥራት ፣ሀብትን አመጦ መሰብሰብና መጠቀም ፣ የተማሪ ምዝገባ ፣ኢኒሼቲቮች እና ማታገያ አጀንዳዎች ላይ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ አመላክተዋል።
የቡኢ ከተማ አስተዳደር ረዳት የመንግስት ተጠሪ እና የብልፅግና ፓርቲ የአቅም ግንባታ እና የሪዖት ዓለም ዘርፍ ኃላፊ አቶ ደጀኔ ነመራ የ2018 ዓ.ም ዕቅድ አቅርበዋል።
በ2017 ዓመት በፓርቲ መሪነት የተለያዩ አደረጃጀቶችን በመጠቀም በርካታ ስራዎችን በመስራት ህዝቡን ተጠቃሚ ማድረግ እንደተቻለ ተናግረዋል።
በቀጣይም የተሰጠውን ተልዕኮ መፈፀም የሚችል እና ህዝብን ማስጠቀም የሚችል ጠንካራ አደረጃጀት ለመፍጠር ትኩረት ተሰጥቶ መስራት ያስፈልጋል።
የከተማ አስተዳደሩን ሰላም ለማረጋገጥ እና በዘላቂነት ለማስቀጠል መላው የከተማ ማህበረሰብ ርብርብ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።
የመድረኩ ተሳታፊዎች በበጀት ዓመቱ በርካታ የሚታዩ ውጤታማ ስራዎች የተሰሩ እንደሆነ በቀጣይም ተጠናክረው መሄድ እንደሚገባቸው ተናግረዋል።
መላው የፓርቲ አባላት በፌክ አካውንት የማህበረሰባችን አንድነት የሚሸረሽሩ አሉባልታዎች የሚያራግቡ አካላትን መታገል መቻል እንዳለበት ተናግረዋል።
በቀጣይም የአመራሩና የአባሉ የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት እንዲኖረው የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ያስፈልጋል ብለዋል።
በመጨረሻም የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ አደረጃጀቶች የእውቅና ሽልማት በመስጠ እና የብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ጋር የ2018 ዕቅድ ግብ ስምምነት በመፈራረም ፕሮግራሙ ተጠናቋል።
መረጃው የቡኢ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው።
ለተጨማሪ መረጃዎች ገፆቻችን ይከታተሉይ