በክረምቱ ወራት ልዩ ተሰጥኦ ያላቸው ታዳጊ ወጣቶችን ታሳቢ ያማድረግ በሶዶ ቡኢ ከፍተኛ 2ኛ ደረጃ መሰናዶ ትምህርት ቤት በስፔስ ሳይንስ ፣ መሰረታዊ የኮምፒውተር ክህሎት እና የአድቫንስድ ዌብሳይት ዴቨሎፕመንት ስልጠና እየተሰጠ እንደሚገኝ ተገለፀ።

በምስራቅ ጉራጌ ዞን በቡኢ ከተማ አስተዳደር ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት የሚመራው የክረምት ወራት የበይነ መረብ ስልጠና በሶዶ ቡኢ ከፍተኛ 2ኛ ደረጃ መሰናዶ ትምህርት ቤት ልዩ ተሰጥኦ ያላቸው ታዳጊ ወጣቶችን ታሳቢ ያደረገ 6ኛ ዙር የክረምት የበይነ መረብ ስልጠና በእስፔስ ሳይንስ ፣ በመሠረታዊ የኮምፒውተር ክህሎት እና አድቫንስድ ዌብ ዲቨሎፕመንት ለተማሪዎች ስልጠና አየተሰጠ እንደሚገኝ ተገልጿል።

ተማሪዎች በቴክኖሎጂ የዳበሩ በብቃትና በክህሎት የበቁ እንዲሆኑ ለማድረግ የተዘጋጀ ስልጠና ሲሆን ስልጠናው ከሌሎች የክረምት ወራት በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከሚሰጡት ከትምህርት ጋር አቀናጅቶ የሚሠጥ በመሆኑ በአግባቡ ለሚያጠናቅቁ ሠልጣኞች በኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦ እስፓሻል ኢንስትቲዩት አማካኝነት ሀገር አቀፍ ሠርተፍኬት እንደሚሰጥም ተገልጿል።

በክረምቱ ወራት ልዩ ተሰጥኦ ያላቸው ታዳጊ ወጣቶች የስፔስ ሳይንስና እና መሰረታዊ የኮምፒውተር እንዲሁም የአድቫንስድ ዌብሳይት ዴቨሎፕመንት ዕውቀት እንዲኖራቸው ስልጠናው ታሳቢ ተደረጎ መዘጋጀቱን የገለፁት የቡኢ ከተማ አስተዳደር ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ቴዎድሮስ ከበደ መሰረታዊ ኮምፒውተር አጠቃቀም ክህሎት እንዲዳብር እና የተለያዩ ክንዋኔዎችን በቀላሉ ለመፈፀም ፈጣንና ቀልጣፋ የስራ እንቅስቃሴ እንዲኖር እንደዚህ አይነት መሰል ስልጠናዎች ወሳኝ ሚና እንደሚኖራቸው ገልፀዋል።

የሶዶ ቡኢ ከፍተኛ 2ኛ ደረጃ መሰናዶ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር መ/ር ታሪኩ የማነ እንዳሉት በ3 መሰረታዊ ዘርፎች እየተሰጠ የሚገኘው ስልጠና የተማሪዎችን ዕውቀትና አቅም እንዲጎለብት ለማድረግ ትልቅ ሚና እንዳለው አንስተው በተለይ በክረምት ወራት ትምህርት ቤት ዝግ የሚሆንበት ጊዜ በመሆኑ ተማሪዎች በተለያየ አልባሌ ቦታ እንዳይውሉ አስተዋጽኦ ያደረገ በመሆኑ በቀጣይም ጊዜያት ጽ/ቤቱ ይህን ተግባር በእቅድ ይዞ በዚሁ አግባብ እንዲቀጥል መልዕክት አስተላልፈዋል ።

የስልጠናው ዋና አስተባባሪ ዶ/ር ፍቅሬ ጂዳ እንዳሉት የተማሪዎችን ዝንባሌ ታሳቢ ያደረገ ስልጠና በመሆኑ በትልቅ መነሳሳት እየተማሩ መሆናቸው ገልፀው ወደፊት ሀገሪቱን አንድ ደረጃ ከፍ ማድረጉ አይቀሬ መሆኑን አንስተዋል።

ያነጋገርናቸው የስልጠናው ተካፋይ ተማሪዎች እየወሰዱት ያለው በስፔስ ሳይንስ ፣ መሰረታዊ የኮምፒውተር ክህሎት እና የአድቫንስድ ዌብሳይት ስልጠና ከዚ በፊት የነበራቸውን እውቀት እንዳሳደገላቸው እና በ በይነ መረብ ለሚሰጠው ሀገር አቀፍ ፈተና ለመዘጋጀት እያገዛቸው እንደሆነ ገልጸውልናል ።

ተማሪዎችና መምህራኖችም የኢትዮጵያ ኮደርስ ኢኒሼቲቭ ያዘጋጀውን የ በይነ መረብ ስልጠና በመሰልጠን የምስክር ወረቀት በመውሰድ ላይ ይገኛሉ።

መረጃው የቡኢ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው።

ለተጨማሪ መረጃዎች ገፆቻችን ይከታተሉይ

0 0 votes
የመረጃው አጥጋቢነት
0 አስተያየት መስጫ
ቆየት ያሉ
የቅርብ ጊዜ Most Voted
Inline Feedbacks
View all comments
0
Would love your thoughts, please comment.x
()
x