“ያሉ የገቢ አማራጮችን አሟጦ ተጠቅሞ ሀብት በመሰብሰብ የህዝቡ የልማት ፍላጎት ለማሟላት በትኩረት ይሰራል።” አቶ በለጠ ጫካ

የቡኢ ከተማ አስተዳደር አማካሪ ምክር 4ኛ ዙር 7ኛ ዓመት 24ኛ መደበኛ ጉባዔውን አካሄዷል።

የቡኢ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ በለጠ ጫካ ያሉ የገቢ አማራጮችን አሟጦ ተጠቅሞ ሀብት በመሰብሰብ የህዝቡ የልማት ፍላጎት ለማሟላት በትኩረት እንደሚሰራ እና ምክር ቤቱም ሊያግዝ እንደሚገባ በምክር ቤቱ አባላት ለተነሱ ጉዳዮች ማብራሪያና ምላሽ በሰጡበት ወቅት ተናግረዋል።

ከተማው ላይ አሁን ያለው የመንገድ መሠረተ ልማት የከተማውን ዕድገት የማይመጥን እንደሆነ እና በቀጣይ በትኩረት የሚኬድባቸው ጉዳዮች እንደሆኑም አመላክተዋል።

ሰላም የሁሉም ነገር መሠረት ስለሆነ የከተማው ዘላቂ ሰላም እንዲጠበቅ የምክር ቤቱ አባላት ሊያግዝ ይገባል ብለዋል።

በቀጣይ በ2018 በጀት ዓመት እንደከተማ አስተዳደር ያደሩ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ የቅድሚያ ቅድሚያ ተሰጥቶ የሚሰራ እንደሆነም አመላክተዋል።

ቡኢ ከተማ አስተዳደር በ2018 በጀት ዓመት ሁለገብ ህንፃ ግንባታ መሠረት ለመጣል በዕቅድ የተያዘ መሆኑን አመላክተዋል።

በእንዲሁም በበጀት ዓመቱ የከተማዋ የኮሪደር ልማት ስራ ለመጀመር ዕቅድ እንደተያዘም ጠቁመዋል።

የተጀመረው የፌድራል ዋና መንገድ ግንባታ የከተማችን ዕድገትና ፕላን ታሳቢ ያደረገ እንዲሆን ከተማ አስተዳደሩ ክትትል እያደረገ እንደሚገኝም አመላክተዋል።

በ2017 በጀች ዓመት የተጀመረው የትራንስፖርት ዘርፍ ለማዘመን የኢቲኬቲንግ የክፍያ ስርዓት ውጤታማ እንዲሆንና ተግባራዊነቱ ህብረተሰቡ የሚጠበቅበትን ግዴታ ሊወጣ ይገባል ብለዋል።

በበጀት ዓመቱ የተከናወኑ ተግባራት ተስፋ ሰጪ እንደሆኑ እና በቀጣይም የበለጠ ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ የምክር ቤቱ አባላት ሀሳብ ሰጥተዋል።

ከትምህርት ቤቶች ደረጃ ማሻሻል፣የመምህራን አቅም ከማጎልበት፣ ስታዲየም ግንባታ፣ክስታኒኛ ቋንቋ ከማልማትና ከተማው የቱሪዝም ማዕከል እንዲሆን የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ከመከታተልና ከመደገፍ አንፃርም የተሰሩ ስራዎች በቀጣይ የበለጠ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ አመላክተዋል።

የመሬት ካሳ አሰጣጥን፣ከማህበራትና ከኢንቨስትመንት መሬት ትልልፍ ፣ቀደም ሲል የተሰሩ የመሠረተ ልማት ስራዎች አገልግሎት እንዲሰጡ የጥገና ስራዎች ፣ ከገቢ አሟጦ ከመሰብሰብና ደረሰኝ አሰጣጥ ጋር ክትትል ሊደረግ እንደሚገባም አንስተዋል።

የከተማው ዘላቂ ሰላም ከማረጋገጥ አንፃርም የማታ ሮንድ ስራ እንዲጠናከርና ህዝቡ ከማንቃት አኳያም ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል።

ማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀም የሶዶ ክስታኔ ማህበረሰብ አንድነት የሚሸረሽሩ ሀሳብ የሚያራምዱ አካላት ተገቢውን ክትትል በማድረግ እንዲታረሙ መደረግ መቻል እንዳለበትም የምክር ቤቱ አባላት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

የምክር ቤቱ አባላትም የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ መሻሻል የሚገባቸው ነጥቦች ላይ ማሻሻያ እንዲደረግባቸው ሀሳብ በመስጠት ዕቅዱን በሙሉ ድምፅ አፅድቀዋል።

ዘገባው የቡኢ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው ።

ለተጨማሪ መረጃዎች ገፆቻችን ይከታተሉይ

✅

0 0 votes
የመረጃው አጥጋቢነት
0 አስተያየት መስጫ
ቆየት ያሉ
የቅርብ ጊዜ Most Voted
Inline Feedbacks
View all comments
0
Would love your thoughts, please comment.x
()
x