እንኳን ደስ አላችሁ!! የቡኢ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ፅ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት ተግባር አፈፃፀም በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በፈርጅ ሶስት ከተሞች አንደኛ ወጣ።

በምስራቅ ጉራጌ ዞን የቡኢ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙሉቀን ቱጂ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በገቢዎች ቢሮ በተደረገው የ2017 በጀት ዓመት ምዘና የተገኘውን ውጤት አስመልክቶ የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።

አቶ ሙሉቀን ቱጂ አክለውም ጽ/ቤቱ በ2017 በጀት ዓመት አጠቃላይ ከተቋሙ እንቅስቃሴና አፈፃፀም አንፃር ከክልሉ ካሉ ፈርጅ 3 ከተሞች 1ኛ ደረጃ በመያዝ የዋንጫ እና የሰርተፊኬት ተሸላሚ መሆኑን ገልፀዋል ።

ይህ እውቅና ከተቋሙ ዕቅድ አፈፃፀም አንፃር የገቢ አሰባሰብ ፣የፊስካል ስራዎች ፣የትምህርትና ስልጠና ፣ከግብር ህጎች አተገባበር ፣የቴክኖሎጂ ስራዎችን ከማስፋፋት እና በሌሎች ተግባራት ተመዝኖ ከክልሉ ፈርጅ 3 ከተሞች አንደኛ ደረጃ በመውጣት እውቅና እንዳገኘ ገልፀው ህይንን ውጤት የመላው የከተማችን አመራር፣ የንግዱ ማህበረሰብ እና የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራር ውጤት ነው ብለዋል።

አክለውም ኃላፊው በዘንድሮው በጀት ዓመት የተገኘው ውጤት በተመሳሳይ ሁኔታ በ2016 በጀት ዓመት እንደተመዘገ አስታውሰው ይህንም ውጤት በቀጣይ በጀት ዓመት ለማስቀጠል ቅንጅታዊ አሰራርሮችን በማጠናከር ከዚህም የበለጠ ውጤት ለማስመዝገብ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

በተለይም ከጽ/ቤቱ ሰራተኞች ጀምሮ የከተማው አመራር አካላት፣ የንግዱ ማህበረሰብ፣ ማዘጋጃቤታዊ አገልግሎት ጽ/ቤት፣ ንግድናገበያ ልማት ጽ/ቤት እና ትራንስፖርት ዩኒት በተለያየ መንገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርገዋል ብለዋል።

በአጠቃላይ ውጤቱ በ2018 በጀት አመትም ከፍ ብሎ እንዲደገም የከተማው ማህበረሰብ የከተማው አመራር እና ባለ ድርሻ አካላት ከተቋሙ ጋር በጋራ በመስራትና ሁሉን አቀፍ ድጋፍና ክትትል በማድረግ የበኩላቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።

ዘገባው የቡኢ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው ።

ነሐሴ 16-2017 ዓ.ም

=====ቡኢ=====

0 0 votes
የመረጃው አጥጋቢነት
0 አስተያየት መስጫ
ቆየት ያሉ
የቅርብ ጊዜ Most Voted
Inline Feedbacks
View all comments
0
Would love your thoughts, please comment.x
()
x