ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር )የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የተመሰረተበትን ሁለተኛ ዓመት በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

የመልዕክቱ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር )የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የተመሰረተበትን ሁለተኛ ዓመት በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

የመልዕክቱ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል

ለመላዉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሕዝቦች፣

ክልላችን ለተመሠረተበት ሁለተኛ ዓመት እንኳን አደረሳችሁ!አደረሰን !

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የተመሠረተበት ፣ ነሐሴ 13 ቀን 2015 ዓመተ ምህረት እነሆ ሁለት

ዓመት ሆነዉ።

እነዚህ ሁለት የትግልና የስኬት ዓመታት ፦በሁሉም መስኮች ተጨባጭ ዉጤቶች የተመዘገቡባቸዉ ፣በየምዕራፉ ካገጠሙ ፈተናዎች ትምህርት የተወሰደባቸዉ፣ የሕዝቦች ተሳትፎና ተጠቃሚነት እያደገ የመጣባቸዉ፣ ሠላማዊ ፣ ጠንካራና ምሳሌ ሊሆን የሚችል ክልል ለመፍጠር የሚያስችሉ ምቹ መደላድሎች እዉን የሆኑባቸዉ፣

በአጠቃላይ ክልላዊ ቁመናችን እያደገና እየደረጃ ብሎም በፈጠራና በፍጥነት መርህ ታግዞ ‘ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር ! በማራመዱ ሂደት ክልሉ የበኩሉን እያበረከተ የተጓዘባቸዉ ናቸዉ ማለት ይቻላል።

_ ዉለዉ ያደሩ የመዋቅር ጥያቄዎች በክልል ምስረታዉ ማግስት ምላሽ እንዲያገኙ ተደርጓል፣ የመዋቅር ጥያቄዉ መመለስም ህዝቡ ትኩረቱን በልማትና በሠላም ግንባታ ላይ እንዲያደርግ ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል።

_አዎንታዊና ዘላቂ ሠላምን በህዝቦች ተሳትፎ እዉን ለማድረግ በተጀመረው ጥረት የህግ የበላይነትን ከማረጋገጥ ፣ የህብረተሰቡን ሠላምና ደህነት እዉን ከማድረግ ፣ ለልማትና ለአብሮነት አደናቃፊ የሆኑ ችግሮችን ከማቃለል አኳያ ዉጤታማ ሥራዎች ተሰርተዋል።የተረጋጋና ሠላማዊ ከባባዊ ሁኔታም ተፈጥሯል ፣

_ክልላዊ ፀጋዎችን እና አቅሞችን መሠረት ያደረጉ የልማት ንቅናቄዎችን በማጠናከር የምግብ ሉዓላዊነትን እዉን ለማድረግ እና ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር አጋዥ የሆኑ አበረታች ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች ተጠናክረዉ ቀጥለዋል፤አበረታች ዉጤቶችም ተመዝግበዋል።

_በከተሞችና በገጠር የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት ፣ የኑሮ ዉድነትን ለማቃለል ጥረት ተደርጓል ።

_የየደረጃዉን አመራር የአስተሳሰብና የድርጊት ዉህደት፣ ትጋት፣ ሕዝባዊነትና ዉጤታማነት ለማሳደግ በተደረገዉ ተከታታይ ድጋፍና ክትትል በአመራር ስርዓቱ ላይ እድገት እየታየ መጥቷል፤ የህዝቦችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማሻሻል በፀና አቋም ላይ ተመስርቶ በተሠራዉ ሥራም ዉጤቶች ተገኝተዋል።

_ በብዙ ቢሊዬን ብር የሚቆጠሩ ከቀድሞ ክልል የተሸጋገሩ ያደሩ ዕዳዎችን መክፈል ተችሏል ፣

_ነባር ፕሮጄክቶችን ለማጠናቀቅ ጥረት ከማድረግ ባሻገር አዳዲስ ፕሮጀክቶችን ጀምረናል፣ ለአብነትም በሰባቱም የክልል ማዕከላት የቢሮዎች ሕንፃዎችን እየገነባን እንገኛለን።

በአጠቃላይ በፖለቲካው ፣ በኢኮኖሚው እና በማህበራዊ ዘርፎች የተሠሩ ሥራዎች እና የተገኙ አበረታች ዉጤቶች ለቀጣዩ ጉዟችን መደላድል እና ሰንቅ ሆነዉ የሚያገለግሉ ፣ የህዝቦችን ተሳትፎ በማጠናከር ለህዝቦች ተጠቃሚነት በታደሰ መንፈስ እንድንተጋ የሚያነሳሱ ናቸዉ። በመሆኑም በቀጣይ ጉድለቶችን እያረምን፣ ስኬቶችን እያፀናን፣ የህዝቦችን የመልካም አስተዳደርና የልማት ጥያቄዎችን ለመፍታት በትኩረት እንሠራለን ።

የተከበራችሁ መላዉ የክልላችን ሕዝቦች!

ያለፉት ሁለት ዓመታት ጉዞ በሚያስደንቅ የሕዝቦች ተሳትፎ የታጀበ ነበር፤ ይህ ሕዝባዊ ድጋፍ የየደረጃዉ አመራር ይበልጥ እንዲተጋ፣የሠላም፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ተግባራት ደግሞ እንዲሳለጡ ጉልህ ሚና ተጫዉቷል።

የክልሉ መንግስት በሁሉም መስኮች ፈጣን መሻሻልና ለዉጥ እንዲረጋገጥ በላቀ ትጋት ለመሥራት ያለዉን ቁርጠኝነት በዚህ አጋጣሚ እያረጋገጥኩ ፤ የክልሉ ሕዝቦች ላደረጋችሁት ሁለንተናዊ ድጋፍ ምስጋናዬን እያቀረብኩ ፣ ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አደራ እላለሁ ።

አመሠግናለሁ !

0 0 votes
የመረጃው አጥጋቢነት
0 አስተያየት መስጫ
ቆየት ያሉ
የቅርብ ጊዜ Most Voted
Inline Feedbacks
View all comments
0
Would love your thoughts, please comment.x
()
x