ከቡኢ ከተማ አስተዳደር የተሰጠ መግለጫ።

በከተማ አስተዳደሩ በተያዘው በጀት ዓመት ብቻ ከተሰሩት በርካታ የመሰረተ ልማት ስራዎች መካከል አንዱ እና ዋነኛው የከተማው ማህበረሰብ ለረዥም ጊዜ ሲጠይቁትና ሲቸገሩበት የነበረው እና እነደዚሁ ከተጀመረ በኃላ እንኳ ለ7 ዓመታት በተለያዩ ችግሮች ምክንያት ሲንጓተት የነበረው ነገር ግን በተያዘው በጀት ዓመት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት በክልላችን ፕሬዝዳንት ክብር ዶ/ር እንዳሻው ጣሰው በተገኙበት መርቀን ለአገልግሎት ክፍት ካደረግናቸው ካፒታል ፕሮጀክቶች መካከል የቡኢ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ተጠቃሽ ነው።

ይህ ፕሮጀክት ከተመረቀበት ከሚያዚያ 28/2017 ጀምሮ በተሟላ መልኩ አገልግሎት እየሰጠ እንደንበረም ይታወቃል። ሆኖም ግን ወቅቱ የክረምት ወቅት እንደመሆኑ መጠን ሐምሌ 25-2017 ዓ.ም በጣለው ከባድ ዝናብ የውሀ ፕሮጀክቱ ካስቆፈራቸው ሁለት የውሃ ጉድጓዶች መካከል አንዱና ትልቁ በፍርሺ ቀበሌ ወልድያ ወንዝ አካባቢ የሚገኘው እና ውሃውን በከፋተኛ ሀይል ወደ ሪዘርቫየር እየገፉ የሚልከው ትራንስፎርመር በመብረቅ ተመቶ ከአገልግሎት ውጭ ሆኗል።

በዚህም በተፈጥሮ አደጋ ምክንያት ከተማ አስተዳደሩ ጉዳቱ ከደረሰበት ቀን ጀምሮ ትራንስፎርመሩ ጠግኖ ወደ ተሟላ አገልገሎት ለመመለስ ከፍተኛ ርብርብ ሲያደርግ ቆይቶ የከተማው የመብራት ሃይል ባለሙያዎች ችግሩን ለይተው በክልል ባለሙያ እንዲፈተሽ ተደርጎ ትራንስፎርመሩ ሙሉ በሙሉ ከአገልግሎት ውጭ መሆኑንና ሌላ ትራንስፎርመር እንደሚያስፈልግ አሳውቀዋል።

በዚህም የከተማው መንግስት ከሚመለከታቸው ከዞን እና ከክልል አካላት ጋር በመነጋገር ችግሩን ለመቅረፍ ከፍተኛ ርብርብ እያደረገ ይገኛል።

በዚህም የተፈጠረውን ችግር ተፈትቶ ወደቀድሞ አገልግሎት እስኪመለስ በመጠኑም ቢሆን በነባሩ መስመር እንደተለመደው በፈረቃ የውሃ ስርጭት የሚደረግ ይሆናል።

መላው የከተማችን ማህበረሰብ የተፈጠረውን ችግር ተቀርፎ ወደ ተሟላ አገልግሎት እስኪመለስ በትዕግስት እንድትጠብቁ ሲል ከተማ አስተዳደሩ መልእክቱን ያስተላልፋል።

#ቡኢ ከተማ አስተዳደር

0 0 votes
የመረጃው አጥጋቢነት
0 አስተያየት መስጫ
ቆየት ያሉ
የቅርብ ጊዜ Most Voted
Inline Feedbacks
View all comments
0
Would love your thoughts, please comment.x
()
x