#በጎነትና አብሮነት ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ቃል የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ የንቅናቄ ፕሮግራም በቡኢ ከተማ አስተዳደር ተካሄደ።

‎በምስራቅ ጉራጌ ዞን የቡኢ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ”በጎነትና አብሮነት ለኢትዮጵያ ከፍታ ” በሚል መሪ ቃል የ2017 የበጋ ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መዝጊያና የ2017/18 ዓ.ም የክረምት ወራት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ ፕሮግራም ተካሂዷል። የማስጀመርያ መርሃ ግብሩ “በጎነትና አብሮነት ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ቃልን ታሳቢ በማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በወጣቶች መዝናኛ ማዕከል ግቢ ውስጥ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በማካሄድ ፕሮግራሙ ተጀምሯል። በመድረኩም የቡኢ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ት ቤት ኃላፊ አቶ እንዳሻው አለማየው በ2017 በጀት ዓመት የተከናወኑት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አፈፃፀም ሪፖርት እና እንደዚሁም የከተማው ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ወጣቶች ዘርፍ ኃላፊ አቶ ጌታነህ ሙሉጌታ የ2017/18 ዓ.ም የክረምት ወራት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ ሰነድ አቅርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል። በ2017 በበጋ ወራት በማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ ፣ በአካባቢ ጥበቃና ግብርና ዘርፍ፣ በመንገድ ደህንነት ዘርፍ፣ በጤና ዘርፍ፣ በስፖርትና ኪነጥበብ ዘርፍ በድምሩ ከ26ሺህ በላይ ወጣቶችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በማሳተፍ በርካታ የበጎ ፈቃድ ስራዎች በማከናወን በመንግስት ይወጣ የነበረን ከ8.3 ሚሊየን ብር በላይ ማዳን እንደተቻለም ተገልጿል። በ2017/18 በክረምት ወራት ከ12ሺህ በላይ ወጣቶችና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በ14 በተመረጡ ዘርፎች ላይ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት እንዲሳተፉ በማድረግ በመንግስት ካዝና የሚወጣ ከ10 ሚሊየን ብር በላይ ለማዳን ግብ መጣሉንም ተገልጿል።

‎የቡኢ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ በለጠ ጫካ ባለፈው በ2016/17 በጀት አመት በክረምትና በበጋ ወራት በበጎ ፈቃድ ተግባራት የተመዘገበውን ስኬት በማስታወስ፣ በቀጣይም የማህበራዊ ችግር ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን መርዳት የአንድ ወቅት ተግባር ብቻ ሳይሆን ባህል ሆኖ መቀጠል እንዳለበት አንስተዋል። አክለውም ክቡር ከንቲባው በዘላቂነት ሰርተው መኖር የማይችሉት አቅም የሌላቸው ዜጎች በተገቢው በመለየት ቤት የመስራት የማደስና የመንከባከብ ስራ በትኩረት መስራት አለብን ብለው ነገር ግን በዓል በመጣ ቁጥር ዶሮና ዱቄት ይሰጠኛል ብሎ መስራት እየቻለ የተረጂነት ስሜት ተላብሰው የሚኖሩት ዜጎን ለይተን ሰርተው መኖር እንዲችሉ ለማድረግ የግንዛቤ ስራ ልዩ ትኩረት አድርገን መስራት መቻል አለብን ብለዋል። የከተማችን ሰላምና ደህንነት አስተማማኝ ደረጃ ላይ ለማድረስ የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አካል አድርገን ሮንድ በመጠበቅ፣ አከራይ ተከራይ ልየታ ላይ በመሳተፍና ከፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅት ሆነን የከተማችን እድገት ዘላቂነት እንዲኖረው አድርገን መስራትም ይጠበቅብናል ብለዋል። የቡኢ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደበበ አዳነ በበኩላቸው የበጎ ፈቃድ ስራዎች መንግስት ተደራሽ በማይሆንባቸው ዘርፎች ተደራሽ በመሆን ለመንግስት አጋዥ በሚሆን መልኩ በርካታ ተግባራት እየተሰሩ እንደመጡ ገልፀው። አክለውም የሀገራችን ብልጽግና ማረጋገጥ የሚቻለው አንዱ ተርቦ፣ ታርዞና ተቸግሮ አንዱ ደግሞ ጠግቦና ደልቶት ሳይሆን ካለን ማካፈል፣ አብሮ መብላትና መጠጣት፣ መረዳዳትና መተጋገዝ ስንችልና አብሮነታችን ስናጠናክር ብቻ ነው ብለው እኔ እያለው አንድም ዜጋ ማጣትና መቸገር የለበትም በሚል ዕሳቤ በመተባበርና ከጎናቸው በመቆም እንደዚሁም በተመረጡ ዘርፎች ብቻም ሳይሆን ድንበር ተሻጋሪ ስራዎች በመስራት ሀገራችን የያዘችውን የብልጽግ ጉዞ እውን ማድረግ አለብን ብለዋል። ‎የቡኢ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ እንዳሻው አለማየው እንደገለጹት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት የመረዳዳትና የመደጋገፍ ባህልን የሚያጠናክር በመሆኑ የዘውትር ተግባራችን ሊሆን ይገባል ብለዋል። ‎በ2017 ዓ/ም በበጋ ወራት በተደረገው በጋራ ጥረት አኩሪ ውጤት መመዝገብ ተችሏል ያሉት ኃላፊው ይህን መልካም ተግባር ከወትሮ በላይ ትኩረት ሰጥተን በክረምት ወራት በወጣቶች በጎ ፍቃድ አገልግሎት ሥራ ላይ ጠንክረን በመስራት ሰው ተኮር የሆነውን የብልጽግና እሳቤን ማረጋገጥ ይገባል ሲሉም አስገንዝበዋል። በ2017/18 በክረምት ወራትም በአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር፣ በሰላምና ፀጥታ ዘርፍ፣ በግብርና ልማት ዘርፍ፣ በትምህርት፣ በጤና ፣ በመሰረተ ልማት ዘርፍ ፣ በመንገድ ደህንነት ዘርፍ፣ በአካባቢ ጥበቃና እንክብካቤ,ፅዳትና ውበት መስክ፣ በጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችና ፆታዊ ትንኮሳ በመከላከል ዘርፍ፣ በወጣት ስብዕና ግንባታ ማዕከላት ዘርፍ፣ በህገወጥ ዝውውር ስራውች መስክ፣ በሙያ አገልግሎት እና ማህበራዊ ሚዲያ ለበጎ ዓላማ በመጠቀም ዘርፍ እንደሚከናወንም አስገንዝበዋል። ‎አክለውም አቶ እንዳሻው አለማየው በ2017/18 ዓ.ም በክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ላይ በተመረጡ በ14 መስኮች የሚከናወን ሲሆን ከ12ሺ በላይ ወጣቶችና መላው ባለድርሻ አካላት በማሳተፍ ከ18ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ይሰራልም ብለዋል። በማስጀመሪያ ፕሮግራሙ ላይም የከተማው አስተባባሪዎች ፣ ጠቅላላ አመራሮች፣ ለከተማው ተጠሪ የሆኑ ቀበሌዎች እና የሁሉም የሰፈር አመራሮች ፣ርዕሳነ መምህራን ፣የወጣት አደረጃጀቶችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተው ከባለድርሻ ተቋማት ጋር የግብ ስምምነት በመፈራረም ፕሮግራሙ ተጠናቋል።

ዘገባው የቡኢ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው ።

‎ሐምሌ ፣17/2017 ዓ.ም

=====ቡኢ======

0 0 votes
የመረጃው አጥጋቢነት
0 አስተያየት መስጫ
ቆየት ያሉ
የቅርብ ጊዜ Most Voted
Inline Feedbacks
View all comments
0
Would love your thoughts, please comment.x
()
x