በ2.2 ሚሊየን ካፒታል በጀት በቻይናው ላንዩ ፕሌይውድ ማኒፍክቸሪንግ የገንዘብ ድጋፍና በቡኢ ከተማ አስተዳደር መንግስት ትብብር የተገነባው የቡኢ ጉቺ-ሞተቢ መንደር ማሻገሪያ ድልድይ ግንባታ ተመረቀ።

በምስራቅ ጉራጌ ዞን በቡኢ ከተማ አስተዳደር በቻይናው ላንዩ ፕሌይውድ ማኒፋክቸሪንግ የገንዘብ ድጋፍና በከተማው መንግስት ትብብር ከ2.2 ሚሊየን ብር በላይ ወጭ ተደርጎ የተገነባው የጉቺ-ሞተቢ መሻገሪያ ድልድይ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል። በምረቃ ፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት ቡኢ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ በለጠ ጫካ ቡኢ ከተማ የከተማ አስተዳደርነት መዋቅር ካገኘ ሰባተኛ ዓመት ያስቆጠረ እንደሆነ አመላክተው በርካታ የመሰረተ ልማት ስራዎች ሲሰራ እንደቆየ አብራርተዋል። ለአብነትም በኢንቨስትመይት ዘርፍ፣ በመብራት ውሃ እና በመንገድ መሰረተ ልማት ዘርፍ እጅግ የሚደነቅ ለውጥ እየተመዘገ እንደሚገኝ አመላክተው በዋናነትም ከተማዋ በስትራቴጂክ ማፕ በመመራት በአራቱም ዘርፍ ለማስፋፋት በርካታ ተግባራት እየተሰሩ እንደሚገኝ አመላክተዋል። አክለውም ክቡር ከንቲባው ዛሬ ላይ መርቀን ለአገልግሎት ክፍት ያደረግነው ድልድይ በከተማው በኢንቨስትመንት መሬት ተረክበው እያለሙ የሚገኙት በቻይናዊያን ባለሀብት 1.5 ሚሊየን ብር ድጋፍ እና በከተማው መንግስት ድጋፍ በድምሩ ከ2.2 ሚሊየን ብር በላይ ወጭ ተደርጎ የተገነባ የመሻገሪያ ድልድይ እንደሆነ ገልፀዋል። ድልድዩ የከተማውን መጋቢ መንገድ ከሚባሉት ዋነኛው መንገድ ሲሆን ማህበረሰቡ በየትኛውን ወቅት ወደከተማው ገብተው ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊ ክዋኔን ለመከወን ሲቸገሩበት እንደነበረ ገልፀው ለቀጣይም ማህበረሰቡ የሚጠይቁትን የመሰረተ ልማት ጥያቄ መሰረት አድርገን የምንሰራ ይሆናልና ለዚህም የነጌሳ ቀቀሌ የመብራት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴ ማሳያ ነው ብለዋል። ድርጅቱ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት የከተማውን መንግስት እያገዘ የሚገኝ ድርጅት እንደሆነ ገልፀው ዛሬ ላይም ተመረቅ ለአገልግሎት ክፍት የሆነው የጉቺሞተቢ መሻገሪያ ድልድይ ግንባታ ከፍተኛው ድርሻ የሚወስድ ነው ብለው ላደረጉላቸው ድጋፍና ትብብር በከተማው ማህበረሰብና መንግስት ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የቡኢ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የማዘጋጃቤታዊ አገልግሎት ኃላፊ አቶ ዘላለም ባህሩ በበኩላቸው ከተማው በከተማ አስተዳዳርነት ከተዋቀረ ጊዜ ጀምሮ የዙሪያው ቀበሌ ለማስተሳሰር በርካታ መንገድና የመሸጋገሪያ ድልድይ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል። ለአብነትም የወላሳ መሻገሪያ ድልድይ እና የምድረገነት መሻገሪያ ድልድይ ተጠቃሽ ነው ብለው ለዚህም መሰረተ ልማት ስራዎች የከተማው መንግስት ከረጂ ድርጅቶችና ከማህበረሰቡ ጋር በቅንጅት እየተሰሩ እንደሆነ አመላክተዋል። ዛሬላይም መርቀን ለአገልግሎት ክፍት ያደረግነው መሻገሪያ ድልድይ በቻይናዊያን ድርጅት የገንዘብ ድጋፍና በከተማው መንግስተ በትብብር እንደተገነባ ገልፀው ለዚህም ድጋፍ ላደረጉት የላንዩ ፕሌይውድ ማኒፋከሰቸሪንጅ ድርጅት ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ምክትል ከንቲባው አክለውም ከተማችን በተለያዩ ጎርጅ እና ሸለቆዎች የተከበበች እንደመሆኗ መጠን በቀጣይም የማህበረሰብ ተሳትፎ አርባ በስልሳ ፕርግራም በማስፋት ለከተማውንም በዙሪያ ያሉት ቀበሌያትም ቅድሚያ ሰጥተን የምንሰራ ይሆናል ብለዋል። የቻይናው ላንዩ ፕሌይውድ ማኒፋክቸሪንግ ባለቤት ሚስተሪ ው ቡኢ ከተማ ከሀገራቸው ቀጥሎ ሁለተኛ ከተማዬ ናት ብለው ከመጡ ስድስት አመታት እንዳስቆጠሩ ገልፀው የከተማውን ማህበረሰብ ለማገዝ ዝግጁ ነን ብለዋል። አክለውም ሚስተር እንደ አንድ ቤተሰብና ማህበረሰብ የትኛውንም ችግሮች ሲፈጠሩ በቤተሰባዊነት በመነጋገር መፍታት እንችላለን ብለዋል። በምረቃ ፕሮግራሙ ላይም የከተማው አስተባባሪ አካላት፣ የከተማው ጠቅላላ አመራር፣ የቀበሌው አመራር እና ነዋሪዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ዘገባው የቡኢ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው ።

0 0 votes
የመረጃው አጥጋቢነት
0 አስተያየት መስጫ
ቆየት ያሉ
የቅርብ ጊዜ Most Voted
Inline Feedbacks
View all comments
0
Would love your thoughts, please comment.x
()
x