ከቻይናው ላን ዩ ፕሌይ ውድ ማኑፋክቸሪንግ ከ 234,000 ብር በላይ ግምት ያላቸው ዕቃዎች የሰረቀው ተከሳሽ በ 8 ዓመት ከ 5 ወር መቀጣቱን ተገለፀ።

የቡኢ ከተማ አስተዳደር ፓሊስ ፅ/ቤት ከላን ዩ ፕሌይ ውድ ማኑፋክቸሪንግ ከ234,000 ብር በላይ ግምት ያላቸውን ዕቃዎች የሰረቀውን ተከሳሽ ፍርድ ማሰጠቱን የቡኢ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አዛዥ ምክትል ኮማንደር መለሰ ተሰማ ገለፁ።

ረዳት ኢንስፔክተር አብርሃም ኢብራሂም የቡኢ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ፅ/ቤት የግድያና የትራፊክ አደጋ መርማሪ ቲም ኃላፊ እንደገለፁት ስንታየሁ ደጀኔ የተባለው ግለሰብ የላን ዩ ፕሌይ ውድ ማኑፍክቸሪንግ የፎር ክሊፍት ተሽከርካሪ አሽከርካሪ ሲሆን በድርጅቱ ውስጥ ያለውን ታማኝነት ተጠቅሞ በሰኔ 22-2017 ዓ.ም ለሰኔ 23 ማንጊያ ላይ ወደ አዲስ አበበ ልሄድ ነው በማለት በተለያየ ጊዜ ለድርጅቱ ተገዝተው የመጡ የማሽን መለዋወጫ ዕቃዎች ወደ መጋዘን አስገባ ሲባል አሳቻ ሁኔታ ጠብቆ ቀንሶና ደብቆ በስውር ቦታ በመደበቅ በድርጅቱ አጥር ወርውሮ በማስወጣት ይዞ ሊያመልጥ ሲል የድርጅቱ የጥበቃ ሰራተኞች ባደረጉት ብርቱ ክትትል ከያዛቸው ሁለት የግንድላ መቁረጫ የሞተር መጋዞች ጋር መያዙን ተናግረዋል ።

የቡኢ ከተማ አስተዳደር የፖሊስ አባለት በቦታው በመገኘት ወደ ፖሊስ ጣቢያ ተጠርጣሪውን ከወሰዱት በኃላ ፖሊስ ተጨማሪ ሰፋ ያለ ምርመራ አስፈላጊ መሆኑን በማመን ተጠርጣሪ ስንታየው ደጀኔ ይኖርበታል ተብሎ በተገመተው የወላጅ ቤተሰቦቹ በተደረገው ብርበራ 2 የፎር ክሊፍት ጎማና 3 ፍሬን ሸራ ወይም ዲስኮች መገኘታቸውን መርማሪ ፖሊስ ረ/ኢንስፔክተር አብርሀም ኢብራሂም አብራርተዋል ።

ፖሊስ የምርመራ መዘገቡን በማደረጃት ወደ ቡኢ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ፅ/ቤት ዓቃቤ ህግ ልኳል እንደ ወንጀል አፈፃፀሙ ሂደት አንቀፅ ጠቅሶ ክስ አቅርቧል፡ክሱ የቀረበለት የቡኢ ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድቤት የቀረበለትን ክስ ተመልክቶ ተጠርጣሪ ስንታየሁ ደጀኔን ጥፋተኛ ብሎታል የቡኢ ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድቤትም ዛሬ ባስቻለው ችሎት ወንጀለኛውን ያስተምራል ያለውን 8 ዓመት ከ 5 ወር እስራት በይኖበታል።

ዘገባው የቡኢ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው ።

ለተጨማሪ መረጃዎች ገፆቻችን ይከታተሉይ

ሐምሌ 11-2017 ዓ.ም

==========ቡኢ==========

0 0 votes
የመረጃው አጥጋቢነት
0 አስተያየት መስጫ
ቆየት ያሉ
የቅርብ ጊዜ Most Voted
Inline Feedbacks
View all comments
0
Would love your thoughts, please comment.x
()
x