ሐምሌ 08/2017 ዓ/ም
በምስራቅ ጉራጌ ዞን በቡኢ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ከትላን ጀምሮ ሲሰጥ የነበረው የአመራር አቅም ማጎልበቻ ስልጠና በዛሬው ዕለትም እየተሰጠ ይገኛል።
በትናትናው ዕለትም በከሰዓቱ ክፍለጊዜ ”#ትንተናዊ ክህሎት ለአዳጊ አመራር” በሚል ርዕስ ተሰጥቶ በዛሬው ዕለትም የቡኢ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ደጀኔ ነበራ ”የብልፅግና ፓርቲ የአደረጃጀትና የአሰራር መመሪያዎች” በሚል ርዕስ የተዘጋጀው የስልጠና ሰነድ እያቀረቡ ይገኛል።
ዝርዝር መረጃው ይዘን የምንመለስ ይሆናል።
ዘገባው የቡኢ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው ።
ለተጨማሪ መረጃዎች ገፆቻችን ይከታተሉይ