ሐምሌ 7-2017 ዓ.ም
====ቡኢ======
የቡኢ ከተማ አስተዳደር ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ቴዎድሮስ ከበደ እንደገለፁት በክረምቱ ወራት ልዩ ተሰጥኦ ያላቸው ፈላጊ ያላቸው ታዳጊ ወጣቶች የስፔስ ሳይንስና መሰረታዊ የኮምፒውተር ዕውቀት እንዲኖራቸው ስልጠና ለመስጠት መዘጋጀቱን አስታውቀዋል።
አቶ ቴዎድሮስ ከበደ አክለውም ታዳጊ ወጣቶች ከሐምሌ 8-2017 ዓ.ም ጀምሮ በፅ/ቤቱ በመገኘት መመዝገብ የሚችሉ መሆኑን አስታውቀው ስልጠናው ከሐምሌ 15 እስከ ነሐሴ 30-2017 ዓ.ም ለተከታታይ ለ45 ቀናት እንደሚሰጥ ገልፀዋል።
በተጨማሪም ከታች በተቀመጠው ሊንክ ኦንላይን መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን ጽ/ቤት ያስታውቃል👇
www.bueecityadmin.gov.et
ዘገባው የቡኢ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው ።
ለተጨማሪ መረጃዎች ገፆቻችን ይከታተሉይ