=======ቡኢ=====
የኬር ህፃናትና ቤተሰብ ለኢትዮጵያ በጎ አድራጊ ድርጅት የህፃናትና ወጣቶች ፎረም 17ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ በመትከል ማንሰራራት በሚል መሪ ቃል በዘንድሮ ዓመት የሚከናወነውን የ7 ቢልዮን የአረንጓዴ አሻራ ኢንሼቲቭ የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብር በቡኢ ከተማ አስተዳደር በቡኢ ዙሪያ ቀበሌ በመቂ ወንዝ ዳርቻ ላይ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር አከናውኗል።
በኬር ህፃናትና ቤተሰብ ለኢትዮጵያ ድርጀት የወጣቶች ልማት ኦፊሰር አቶ መህዲን ሱልጣን የህፃናትና ወጣቶች ፎረምን 17ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ምክንያት በማድረግ የተለያየ ጥቅም ያላቸው ለአፈርና ውሀ ጥበቃ እንዲሁም ለምግብነት የሚሆኑ ችግኞችን በመቂ ወንዝ ዳርቻ በተራቆቱ ቦታዎች ላይ መትከል መቻሉን ተናግረዋል ።
የህፃናትና ወጣቶች ፎረም ምስረታውን ካደረገበት ጊዜ ጀምሮ ድርጅቱ በሚሰራባቸው ቀበሌዎች ፎረሙ በመንገድ ግንባታ ፣ የአቀመ ደካማ ቤቶች ግንባታ፣የምግብ ዕጥረት ለገጠማቸው አረጋውያን ምግብ ድጋፍ ማድረግና የተለያዩ የበጎ ፍቃድ ስራዎች ላይ እንደሚሳተፍ አቶ መህዲን ሱልጣን ተናግረዋል።
በችግኝ ተከላ መርሀ -ግብሩ የኬር ህፃናትና ቤተሰብ ለኢትዮጵያ ስራ አስኪያጅ አቶ አማን እንየው፣የድርጀቱ ሰራተኞችና፣ድርጅቱ ከሚሰራባቸው ቀበሌዎች የመጡ የፎረሙ አባላትና ጥሪ የተደረገላቸው አካላት ተገኝተዋል።
ዘገባው የቡኢ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው ።
ለተጨማሪ መረጃዎች ገፆቻችን ይከታተሉይ