በቡኢ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት ከንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት በጋራ የክረምት ወራት የገቢ አሰባሰብ እና የንግድ ስራ ፍቃድ እድሳት የንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
====ቡኢ=====
በምስራቅ ጉራጌ ዞን የቡኢ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት እና የከተማው ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት በጋራ በመሆን የ2017/18 የግብር ዘመን የክረምት ወራት የግብር አሰባሰብና የንግድ ስራ ፍቃድ እድሳት አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር የውይይት መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
በንቅናቄ መድረኩም የቡኢ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ በለጠ ጫካ፣ የቡኢ ከተማ አስተዳደር አማካሪ ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ ንጉሴ ተክሌ፣ የቡኢ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊና ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ደበበ አዳነ፣ የቡኢ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ኃላፊ አቶ ሙሉቀን ቱጂ፣ የቡኢ ከተማ አስተዳር ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ ባሩዳ፣ የከተማው ጠቅላላ አመራር አካላት፣ የቡኢ 01 ቀበሌ፣ የቡኢ ዙሪያ እና የነጌሳ ቀበሌ አመራር፣ የ12ቱም የከተማው የሰፈር አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
የንቅናቄ መድረኩን ያስጀመሩት የቡኢ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙሉቀን ቱጂ ግብር ከፋዮች የሚጠበቅባቸውን ግብር/ታክስ በወቅቱና በታማኝነት እንዲከፍሉ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች መሰራት እንዳለበት ጠቁመው በተለይም የደረጃ “ሐ” ግብር ከፋዮች የመክፈያ ጊዜያቸውን አውቀው መክፈል እንደሚጠበቅባቸው ታሳቢ ተደርጎ ከባለድርሻ አካላት ጋር የተደረገ የግንዛቤ ማስጨበጪያ የንቅናቄ መድረክ እንደሆነ አመላክተዋል።
በመድረኩ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የቡኢ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ በለጠ ጫካ የገቢ አሰባሰብ ስራ ላቅ ያለና ልዩ ትኩረት የሚሰጠው አጀንዳ እንደሆነ ገልፀው ግብር በወቅቱ እና በአግባቡ በመክፈል የከተማው ሁሉ አቀፍ ልማት እንዲፋጠን ሁሉም ባለድርሻ አካላት አሻራውን ማኖር ይጠበቅበታል ብለዋል።
አክለውም ክቡር ከንቲባው የምንገኝበት የክረምት ወቅት የገቢ አሰባሰብ ተግባር ሚፈፀምበት እንደመሆኑ መጠን የደረጃ “ሐ” ከሐምሌ 1-30 ቢሆንም እስከ ሀምሌ 10/2017 ዓ/ም ባጠረ ጊዜ ውስጥ በሞቢላይዜሽን በመክፈል እና ግዴታችንን በመወጣት የሚጠበቅብንን ኃላፊነት እንወጣ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ዝርዝር መረጃው ይዘን እንመለሳለን።
#ዘገባው የቡኢ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው ።
ለተጨማሪ መረጃዎች ገፆቻችን ይከታተሉይ