የቡኢ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃቤታዊ አገልግሎት ጽ/ቤት
የማዘጋጃቤታዊ አገልግሎት ጽ/ቤት ኃላፊ መልዕከት
በከተማችን የበላይነት ይዞ የሚገኘውን የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባር በአሰራርና በአመለካከት ቀረጻ በመናድ ለልማታዊነት ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ህዝብን ያሳተፈ ትግል ተደርጓል፡፡ ከዚህ አንጻር የኪራይ ምንጮችን በማድረቅ ረገድ በጅምር ደረጃ የሚወሰድ ውጤት ማየት የተቻለ ቢሆንም በሴክተርና በከተማ የተለዩ የኪራይ ምንጮች ላይ በአመለካከት ቀረጻ፣አሰራርን በማሻሻልና መረጃን ማዕከል ያደረገ የፀረ-ኪራይ ሰብሳቢነት ትግል በሁሉም አካባቢዎች ተመጣጣኝ ደረጃ ያልደረሰ በመሆኑ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫችንም ይህን የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባር መግታት ይሆናል፡፡ ከዚህ አንጻር በሴክተሩና በከተሞች በተለያየ ደረጃ የሚስተዋል የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባር ላይ የተጠናከረ ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ ይወሰዳል፡፡በመሆኑም የተጀመረውን የጸረ-ኪራይ ሰብሳቢነት ትግል በግንባር ቀደሞች መሪነትና በህዝብ ተሳትፎ ማድረቅ ዋና ትኩረታችን ሆኖ ይቀጥላል፡፡
ለ. በከተማው መልካም ልማታዊ አስተዳደር የማስፈን አቅጣጫ፡-
የበጀት ዓመቱ ሌላው መሰርታዊ አቅታጫችን የሚሆነው የከተማ የልማታዊ መልካም አስተዳደር አጀንዳዎችን ውጤታማነት በማፋጠንና የልማት ጥያቄዎችን በመመለስ የተገልጋይ እና የህዝብ እርካታን ማረጋገጥ ነው፡፡ ለዚህም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን፣መንሰዔያቸውንና መፍትሄዎቻቸዉን በመለየትና ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ የድርጊት መርሃ-ግብር በማዘጋጀት እልባት እንዲያገኙ የማድረግ አቅጣጫ በዚህ በጀት አመትም የምንከተል ይሆናል፡፡በመሆኑም የምንሰጣቸውን አገልግሎቶች ለዜጎች በምንገባው የአገልግሎት አሰጣጥ ስታንዳርድ መሰረት በመፈጸም ውጤታመነቱ በተገልጋዩና በህዝብ እርካታ እንዲመዘን ይደረጋል፡፡
ከዚህ አንጻር በመሰረታዊ አገልግሎት አቅርቦትና በአገልግሎት አሰጣጥ የተገልጋየችን የእርካታ ደረጃ በመለካት በሚገኘው ውጤት መሰረት ፈጣን ማስተካከያ የሚደረግ ይሆናል፡፡ መልካም አስተዳዳርን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ህዝቡ ግንባር ቀደም ተዋናይ እንዲሆን በከተሞች የተጀመረው የህዝብ ንቅናቄ መድረክና በአጀንዳዎች ላይ የሚደረግ የህዝብ የልማት ተሳትፎ አደረጃጀቶች እንቅስቃሴ ከምንጊዜውም በላቀ ደረጃ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ይደረጋል፡፡
ሐ. የልማት ሠራዊት የመገንባት አቅጣጫ፡-
ከሁለገብ ከሠራዊት ግንባታ አንጻር አደረጃጀቶችን በማነቃነቅ ዕቅድን አሟጦ ለመፈጸም የሚያስችል አቅም ለመፍጠር ጥረት ይደረጋል፡፡ ከዚህ አኳያ በመንግስትና በህዝብ ክንፍ በተፈጠሩት አደረጃጀቶች የማቀድ፣የመተግበርና አፈጻጸሙን የመገምገም ስራ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡ ከዚህ አንጻር የልማት ሠራዊት የተሟላ ቁመና ኖሮት ተግባራትን በብቃት እንዲፈጽም ለማስቻል የዕቅድና ፈጻሚ ዝግጅት፣ የትግበራ ክትትልና ግምገማ እንዲሁም የእቅድ አመራር ዑደት ውጤታማነት ለማረጋገጥ በሚያስችል አግባብ በትኩረት ይፈጸማል፡፡
2.2 የከተማ ማስፈጸም አቅም ግንባታ
ሀ. የከተማ አካባቢ ልማትና የህብረተሰብ ተሳትፎ
በዞናችን ከተሞች 17ቱ የልማት አጀንዳዎች ተግባራዊ እንዲሆንና በምዘና ደረጃ እየሰጡ አሰራሩም ተጠናክሮ ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑና እንዲሁም የተሻለ አፈጻጸም ያላቸውን ሰፈሮች ዕውቅና እንዲሰጣቸው ይደረጋል፡፡ በከተማዉ በሚገኙ ሁሉም መንደሮች የሕዝብ ንቅናቄ መድረኮች በቋሚነት የሚቀጥል መሆኑን፣ መልካም ተሞክሮ መቀመርና ወደሌሎች አከባቢዎች ማስፋት፣ ከልማት ጋር በተያያዘ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ፍትሃዊ ምላሽ እንዲያገኙ ማድረግ፣እንዲሁም ለነዋሪው ሕብረተሰብ ማህበራዊ መሰረተ ልማቶች ተደራሽ በማድረግ፣የፍትህና ፀጥታ አጀንዳዎች በማስተግበርና በመፍጠር መልካም አስተዳደርን ማስፈን የትኩረት አቅጣጫችን ይሆናል፡፡ ከዚህ ጎን ለጎን የህብረተሰቡ በገንዘቡ፣በእውቀቱና በቁሳቁስ የሚያደርገውን አስተዋጽኦ ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ትኩረት የሚሰጠው ተግባር ይሆናል፡፡
ለ. የተቀናጀ የመሰረተ ልማት አቅርቦትና አስተዳዳር
የተቀናጀ መሰረተ-ልማት በወቅቱ ለማቅረብ የሚያስችል የቅንጅት፣ የጥራት እና ፋይናንስ አቅጣጫ መከተል ዋናው አቅጣጫ ሲሆን የከተሞችን እድገት ለማስመዝገብ የሚያስችሉ መሰረተ-ልማቶች ስታንዳርድ ወጥቶላቸው በተቀናጀ አኳኋን ለዜጎች ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍልን በሚያረጋግጥ አግባብ የፋይናንስ ምደባ በማድረግ የሚቀርብበትን አግባብ የምንከተል ይሆናል፡፡ ከዚህ ጎን ለጎን የዞኑ መንግስት ድጎማ ልማት አጋዥ ተገማች እና ማዘጋጃ ቤታዊ መሰረተ-ልማቶችን ያገናዘበ እና የልማታዊ ቁልፍ ሚና ያላቸውና የተመረጡ ከተሞች ላይ ያተኮረ እንዲሆን ይደረጋል፡፡ በሌላ አንፃር የልማት ኃይሎችን የማንቀሳቀስ ብቃት ማሳደግ ያስፈልጋል፡፡ በዚህም ህዝብ ለልማት ሙሉ ባለድርሻ በማድረግ በጉልበቱ፣ በገንዘቡና በቁሳቁስ አቅርቦት የሚደግፍበትና የራሱን ቅደም መሰረት አድርጎ የሚሰራበት አሰራር መከተል የትኩረት አቅጣጫዎች ናቸው፡፡
ሐ. የከተሞች ጽዳት አስተዳደርና አረንጓዴ ልማት
የከተማ ጽዳትና አረንጓዴ ልማት ስራ በዋናነት በህ/ሰቡ በራሱ የሚሰራ ከመሆኑ ጋር ገተያይዞ ነዋሪዎችን በአደረጃጀታቸው አማካይነት የ1ለ5፣የጣቢያ/ብሎክ/፣የሰፈር/መንደር/አደረጃጀቶችን ትኩረት በማድረግ ዋና አንቀሳቃሽ የሆነውን ግንባር ቀደሙን ኃይል በመጠቀም የከተማ ጽዳትን ለማስጠበቅ በንቅናቄ ይፈፀማል፡፡
በታሪክ ከአንድ ክፍለ ዘመን በላይ ረጅም ርቀት የተጓዘው የዛሬዉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ተልእኮ ቀልጣፋና ዉጤታማ መረጃና የተግባቦት ሥርዓት በመዘርጋት ሀገራዊና የከተማ አስተዳደሩ የመንግስት አጀንዳዎች የተሻለ ተቀባይነትና ተፈፃሚነት እንዲኖራቸው ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃን በማቅረብ፣ ህዝቡ በዋና ዋና ሀገራዊ ክልላዊ፤ ዞናዊና ከተማዊ ጉዳዮች ላይ መግባባት እንዲፈጥርና የሀገሪቱ መልካም ገጽታና ተሰሚነት እንዲጎለብት ስትራቴጂካዊ አመራር መስጠት ነዉ፡፡ የተቋሙ የተግባቦት ስራ ዘመነ ግሎባላይዜሽን የደረሰበትን የዲጂታል ሚዲያን፣ ፈጣን የመረጃ ስርጭትና የነቃ ህብረተሰብን መረጃ ፍላጎት ጥማት ለማርካት ከየትኛዉም ወቅት ልቆና ቀልጥፎ በመገኘት የዘርፉን ስራ መምራትና መከወን ተቋማችን ይጠበቅበታል፡፡ ዓለም አቀፋዊና ሀገራዊ ነባራዊና ተለዋዋጭ ሁኔታ ዉስጥ ሆኖ ህብረተሰቡ ከደረሰበት የአስተሳሰብ ከፍታ፣ የለዉጥና የእድገት ልህቀት ጋር የሚራመድ ተቋም መሆን ይጠበቅታል፡፡
ተቋሙ ቁልፍ የመንግስት የመረጃ ምንጭነቱንና የብቁ ቃል አቀባይነት ሚናውን በአግባቡ መወጣት እንዲችል የተቀናጀና የተናበበ የመረጃ ፍሰት እንዲኖር ማድረግ፤ ብቁ ምላሽ ሰጪ፣ አሳታፊና ተደራሽ መሆን ይኖርበታል፡፡ ህገመንግስቱን መሰረት ባደረጉ አንኳር ጉዳዮች፤ በብሔራዊ ጥቅሞች፤ በሰላምና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ፤ የሀገሪቱን ገፅታ በመገንባት ረገድ ከሁሉም የሚዲያ አውታሮች ጋር በትብብርና በመደጋገፍ መስራትም ይጠበቅበታል፡፡
ከዚህም አኳያ ያሉንን የሚዲያ መሳሪያዎቻችንን እና የተለያዩ የሚዲያ አማራጮችን በመጠቀም የከተማው ህዝብ በሚኖርበት ከተማ ውስጥ ስለሚከናወኑ የመሰረተ ልማት የመልካም አስተዳደር፤ኢንቨስትመንትና የተለያዩ ሁነቶች ላይ ትኩረት በመስጠት ለህዝብ መረጃ የመስጠት ስራችንን አጠናክረን ቀጥለናል፡፡
ይህንን ተልዕኮዉን ለመወጣት፣ የተቀናጀና ውጤታማ ስራ ለማከናወን እንዲቻል በብቁ ተቋማዊ አደራጃጀት፣ የሰዉ ሃይል፣ ቁሳቁስና አሰራር ራሱን ማጠናከርና ማዘመን ይኖርበታል፡፡ ከሚዲያዎች ጋር በትብብርና መደጋገፍ አብሮ መስራትን፣ መረጃና ቴክኖሎጂ መጋራትን፣ የአቅም ክፍተቶችን በመለየት እዉቀትና ክህሎትን ለመገንባት መስራት ይገባናል፡፡
የተቋማችን መንግስት ኮሙኑኬሽን አገልግሎት አሰጣጥ ለማዘመን እና ከተማ አስተዳደሩ ከተዋቀረበት ጊዜ ጀምሮ በየዘርፉ የሚከናወኑ የከተማ አስተዳደሩ የልማትና መልካም አስተዳደር ተግባራትን በምስል(Photo)፤ በተንቀሳቃሽ ምስልና በድምፅ(Audio-Visual) ሰንዶ ለማቆየትና ለውሳኔ ሰጪነት በሚሰጥ መልኩ የመረጃ ማእከል (Data center) በማቋቋም ላይ እንገኛለን፡፡
በስተመጨረሻም ውድ የከተማችን ነዋሪዎች! ዘመኑን የዋጀና አውዱን የተረዳ ትውልድ ለመፍጠር መጽሐፍትን ማንበብ ባህሉ ያደረገ ዜጋ ማፍራት ያስፈልጋል፡ ስለሆነም የቡኢ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የከተማው ህዝብ የማንበብ ባህሉን ለማዳበርና ማንበብ እየፈለጉ መጽሐፍት ማግኘት ያልቻሉ አንባቢያን ችግር ለመቅረፍ የተለያዩ ይዘት ያላቸው የታሪክ፤ የፍልስፍና፤ የሳይንስ፤ የስነልቦናና የልብወለድ መጽሐፎችን ከተለያዩ በጎ አድራጊ ግለሰቦችና ተቋማት በቁጥር ከአንድ ሺህ በላይ መፅሐፍትን ያሰባሰብን ስለሆነ ከጽ/ቤታችን ተውሳችሁ ማንበብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
እንዲሁም ተቋማችን የአንባቢያን ፍላጎት ለማርካት በብዛትም ሆነ በዓይነት በርካታ ይዘት ያላቸው መፅሐፍትን በማፈላለግ ላይ የሚገኝ ሲሆን ማንኛውም ግለሰብም ሆነ ተቋም ከዚህ በፊት አንብቦ ወይም ተጠቅሞ ቤት/ቢሮ ውስጥ ያስቀመጣቸው መፅሐፍቶች እንዲሁም ገዝቶ ድጋፍ በማድረግ በእውቀት፤በክህሎትና በጥበብ የበለፀገ ዜጋ ለመፍጠር በምናደርገው ርብርብ ላይ የበኩላችሁን እንድትወጡ መልዕክታችን እናስተላልፋለን፡፡
በተጨማሪም የተገለጹት አንኳር ጉዳዮችንና የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ተልዕኮዎችን በማሳካት በኩል ጉልህ ሚና ይኖረዋል፡፡ በመሆኑም በጽ/ቤታችን ያሉ የተላያዩ የሚዲያ አማጭ በመጠቀም የምናሰራጫቸዉን መረጃዎች በማጋራት(Share)፣ በመዉደድ(like) እና ገንቢ አስተያያት(comment) በመጠስት መረጃዎችን ተደራሽ ለምታደርጉ ሁሉ ምስጋናችን ወደር የለዉም፡፡

የቡኢ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃቤታዊ አገልግሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዘላለም ባህሩ
ተልእኮ
ከተማችን ለዜጎች የስራ ዕድል በመፍጠር፣ኢንተርፕራይዞችን በማብቃት፣ የአካባቢ ልማት በማስፋፋት፣መልካም ልማታዊ አስተዳደር በማስፈን፣ ከተማችን በፕላን በመምራት፣ የመሬት አቅርቦትን ግልጽ ቀልጣፋና ፍትሃዊ በማድረግ፣ ቤትና መሠረተ ልማት አቅርቦት በማሳደግ፣ አረንጓዴ ኢኮኖሚ በማረጋገጥ ከተሜነት ተስፋፍቶ የኢንዱስትሪውን ልማት ማገዝና ማስተናገድ ወደሚያስችል የዘመነ ደረጃ እንዲደርሱ ማድረግ፡፡
ራዕይ
በከተማችን ሰፊ የስራ ዕድል የሚፈጥሩ ተቋማት ተስፋፍተው፣ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መሰረተ ልማቶች ተዘርግተው፣ የመሬት ልማታዊነት ሰፍኖ ፣ ጽዱ ውብና ለኑሮ ተስማሚ እንዲሁም ለኢንቨስትመንትና ለቱሪዝም ሳቢ ከተሞች ተፈጥረው በ2017 ከተማችን ብሎም ዞናችን የመጀመሪያ ደረጃ መካከለኛ ገቢ ያላት ሆና ማየት፡፡
እሴቶች
-
- ሥራዎቻችን ልማታዊና ዲሞክራሲያዊ የጋራ አመለካከትን ከመፍጠር ይጀምራሉ!
- የመልካም አስተዳደር መርሆዎች ማክበር መለያችን ነው፣
- በማያቋርጥ ለውጥና መሻሻል እናምናለን!
- የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባር እንፀየፋለን፣
- ተገልጋዮቻችን የሕልውናችን መሠረት ናቸው
-
-
ዓላማ
በከተማችን ሰፊና ተወዳዳሪ የስራ እድል በመፍጠር፣ የከተማ አካባቢ ልማት በማፋጠን የከተማ- ከተማና የከተማ-ገጠር ትስስርን በማጠናከር ለከተማ ልማት ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ከተሜነትን ማሳደግና መልካም ልማታዊ አስተዳደር ማስፈን ነው፡፡
-
በተቋሙ የተሰሩ የመሬት ዝግጅት



