ተልእኮ
ከተማዊ፤ ዞናዊ ፤ክልላዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ህብረተሰቡን ለሁለንተናዊ ተሳትፎ የሚያነሳሳ ፤የሚያጎለብትና ተጠቃሚ የሚያደርግ የኮሚዩኒኬሽን ስርዓት በመዘረጋት ተአማኒ እና ጥራቱን የጠበቀ መረጃ ተደራሽ ማድረግ ነው፡፡
ራዕይ
በ2025 ዓም የከተማችን ህዝቦች በላቀ መረጃ በልፅገው የጋራ ውሳኔ ሰጪነታቸው ተረጋግጦ በመካከላቸው እኩልነት፤አንድነትና ወንድማማችነት ተጠናክሮ ማየት
ራዕይ
በ2025 ዓም የከተማችን ህዝቦች በላቀ መረጃ በልፅገው የጋራ ውሳኔ ሰጪነታቸው ተረጋግጦ በመካከላቸው እኩልነት፤አንድነትና ወንድማማችነት ተጠናክሮ ማየት
እሴቶች
-
- ግልጽነትና ክፍት፣
- ብዙኃንነትና እኩልነት፣
- ተደራሽነት፣ወቅታዊነትና ምላሽ ሰጭነት፣
- ሙያዊነትና ፈጠራ፣
- ተኣማንነትና ትክክለኛነት፣
- ዓላማ
አገልግሎቱ በሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ በርካታ ዓላማዎችን እንደሚያሳካ የሚጠበቅ ሆኖ በዋናነት በሚከተሉት ዓላማዎች ላይ ትኩረት ያደርጋል፡፡እነሱም፡-
-
- በመንግሥት የመረጃና የተግባቦት ወይም ኮሙኒኬሽን ሥርአት የቃል አቀባይነትና ስትራቴጅካዊ የመሪነት ሚና መጫወት፤
- መንግሥት ፖሊሲዎች፣ መርሐ ግብሮች፣ ፕሮግራሞችና ዕቅድችን መሠረት ያደረጉ አጀንዳዎችን በማዘጋጀት ቀልጣፋና ውጤታማ የመረጃና የተግባቦት ሥርአትን በመፍጠር ምልዓተ ሕዝቡን ተደራሽ ማድረግና ተሳትፎዉን ማሳደግ፤
- በልዩ ልዩ መንግሥት ተቋማት፣ የሚዲያ አዉታሮችና በባለድርሻ አካላት መካከል ውጤታማና ቀልጣፋ የመረጃና የተግባቦት ሥርአትን በመፍጠር ኹሉም የኅብረተሰብ ክፍሎች ከመንግሥት መረጃ ዕኩል የሚያገኙበትና ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ምቹ ሁኔታ መፍጠር፤
- መንግሥትን ፖሊሲዎች፣ መርሐ ግብሮችና ፕሮግራሞችን መሠረት በማድረግ ኅብረ- ብሔራዊ አንድነትን፣ የሀገር ፍቅርን፣ ሀገራዊ ተግባቦትን፣ የዳሞክራሲ ባህልን ለማጎልበትና ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ የሚያስችል ቀልጣፋና ውጤታማ የመረጃና የተግባቦት ሥርአት ለመዘርጋት የሚያስችል ስትራቴጂካዊ አመራር መስጠትን ያካተተ ነው፡፡