ተልእኮ
በከተማ አስተዳደር የሚገኙ ሴቶችና ህፃናት ንቅናቄ በመፍጠር እንዲያደራጁ ምቹ ሁኔታዎችን በማመቻቸትና በማጠናከር፤ አቅማቸውን በማጎልበት ፤በሁሉም አካላት እቅድና ፕሮግራም ውስጥ ጉዳያቸው እንዲካተት በማድረግ ፤በመከታተልና በማስተባበር ፤የህፃናትን መብትና ደህንነት በማስጠበቅ በልማት ፤በሰላም በዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታና በመልካም አስተዳደር ጉዳዮች እኩል ተሳታፊና ተጠቃሚነታቸውን ማረጋገጥ፡፡
ራዕይ
ሴቶች በመልካም አስተዳደር የዲሞክራሲ ስርዓት ሰፍኖና በኢኮኖሚ እራሱን የቻለ ህብረተሰብ ና መካከለኛ ገቢ ያለው ለክልሉ ኢኮኖማዊና ማህበራዊ እድገት የበኩሉን አስተዋፆ የሚያደርግ ወጣት እውን ሆኖ
እሴቶች
- የሴቶችና ህፃናትን መብቶችን ለማስከበር በቁርጠኝነት እንሰራለን ፤እናስከብራለን፤
- የፆታ እኩልነትን ለማስፈፀም እንሰራለን፤
- በውጤት እናምናለን፤
- ግልፀኝነትን፤ ተጠያቂነትን ፍትሃዊነትን እናሰፍናለን፤
- ተሳታፊነትንና ቅንጅታዊ አሰራርን እናጠናክራለን፤
- ተገልጋዮችን ለማርካት እንሰራለን፤
የሴክተሩ የትኩረት አቀጣጫ
- የሴክተሩን ተገልጋዮች፣ አመራሮች፣ ፈፃሚዎችና ባለድርሻ አካላትን አቅም በማጎልበት የመፈፀምና የማስፈፀም ብቃታቸውን ማሳደግ፣
- ሶስቱን የልማት አቅሞች በመጠቀም፣ የተደራጅ የልማት ሰራዊት በመፍጠርና የለውጥ አስተሳሰብን በማጎልበት የሴክተሩን የልማት ግቦች ማከናወን፤
- የከተማ ሥራ አጥ ሴቶች ዘመናዊ ቴክኖሎጂን እንዲጠቀሙ በማብቃት በተሰማሩበት የስራ መስኮች ምርትና ምርታማነትን እያሳደጉበከተማ የቴክኖኖሎጂ ሽግግር ማዕከል እንዲሆኑ ማድረግ፤
- የከተማ ስራ አጥ ሴቶች በከተማ ግብርናና በ4ቱ ዘርፎች የሥራ ዕድሎች ራሳቸዉን እንዲችሉ፣ የኑሮ ደረጃቸውን ለማሻሻል ገበያ ተኮር በሆኑና እሴት የሚጨምሩ ምርቶች ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እንዲሰማሩ ማስቻል፤