የቡኢ ከተማ አስተዳደር ባህል ቱሪዝም ጽ/ቤት

የተቋሙ ኃላፊ ወ/ሮ ማሜ ጌታቸው መልዕክት

የቡኢ ከተማ አስተዳደር ባህል ቱሪዝም ጽ/ቤት የከተማችን ህዝቦች የባህል፣ ታሪክ፣ቋንቋና ሥነ-ጥበብ እሴቶችን በማጥናት በማልማትና በመጠበቅ የህብረተሰቡ ማንነት እንዲታወቅና ተጠቃሚም እንዲሆን ከማድረጉ በተጨማሪ ጽ/ቤቱ በአሁኑ ዘመን በዓለማችን በፍጥነት እያደገ የመጣውን የቱሪዝም  ዘርፍ በማጎልበት የከተማው የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ክትትልና ድጋፍ በማድረግ በሃገር አቀፍና ብሎም በዓለም አቀፍ በማስተዋወቅ በከተማው ገጽታ ግንባታ ላይ ተገቢውን ድርሻ እያበረከተና በቱሪዝም ዘርፍ የከተማው ገቢ በማሳደግ የማይናቅ ሚና በመጫወት በድህነት ቅነሳ ረገድ አስተዋጽዎ እያደረገ ይገኛል፡፡

የቡኢ ከተማ የባህል ቱሪዝም ጽ/ቤት እነዚህን ሀብቶች በይበልጥ በማጥናት በመለየት በማልማትና በመጠበቅ ለትውልድ እንዲተላለፉ ማድረግና ጠንካራ የማስተዋወቅና የገበያ ትስስር የመፍጠር ሥራ በመሥራት ሀብቶችን ለዓለም ህብረተሰብ በማስተዋወቅ ለከተማው ኢኮኖሚ ተገቢውን የገቢ ድርሻ እንዲያበረክት በተጣለበት ሃላፊነት በርካታ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል፡፡በዚህም መሰረት የ2017 በጀት ዓመት እቅድ እንደሚከተለው ታቅዷል፡፡

BUEE2975 (Small)

የቡኢ ከተማ አስተዳደር ባህል ቱሪዝም ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ማሜ ጌታቸው

ተልእኮ

የሶዶ ክስታኔ ቤተ-ጉራጌ ማ/ሰብ የባህል የታሪክ የቋንቋ የቅርስ የተፈጥሮና ሌሎች ባህላዊ ዕሴቶች እንዲጠኑ፤እንዲጠበቁ፣በዘላቂነት እንዲለሙና የአገልግሎት ሰጪ ተቋማትን የአገልግሎት አሰጣጥ ደረጃ በማሳደግ የቱሪስት መስቦችን በሀገር ውስጥና በውጭ የቱሪዝም ገበያ ለማስተዋወቅ የተቋሙን ልማታዊ ተሳትፎ ማሳደግና የህብረተሰብ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ እና በመንግስት ኢንፎርሜሽንና ኮሚኒኬሽን ስርዓት ውስጥ መሪ በመሆን በመንግስትና በህዝብ መካከል ቀልጣፋና ውጤታማ የኢንፎርሜሽን ፍሰት እንዲኖር ማድረግ፤

ራዕይ

በ2022 የባህልና ቱሪዝም ዘርፍን በማላቅ ቀዳሚ የከተማው ብልፅግና መሠረቶች አንዱ ማድረግ፣ተገንብቶ ማየት፤

እሴቶች

  1. ብዝሀነትን ማክበር
  2. እንግዳ ተቀባይነት
  3. ግልጽነት
  4. ተጠያቂነት
  5. ለለውጥ ዝግጁነት
  6. የላቀ አገልግሎት
  7. ህዝባዊነት
  8. ፈጠራን ማበረታታት
  9. ቅልጥፍናና ውጤታማነት
  10. የአገልግሎት ጥራት
  11. በቡድን መስራት 

ዓላማ

የተቋሙ ተግባርና ሃላፊነት